"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 20 September 2012

ሰይጣንን መልዓክ፣ ገዳይንና ጨካኝን የሰላም መልእክተኛ ለማድረግ ይህን ያህል መራወጥ ለምን አስፈለገ?
ከበቃና ኦብሴ
“… ዜሮ ስድስት (ባዶ ሹድሽተ) ተብሎ የሚጠራ እስር ቤት፤ ለትግራይ ሕዝብ የናዚ ስርዓት የሚፈጽሙበት ነበር፡፡ ይህ ከአደጉ በኋላ (ምስገበሉ) የተመለሱበት ሜዳ ስለነበር፤ ለሞት ተፈርዶ ወደዚሁ ሜዳ የሚላክ እስረኛ፤ ስጋውን በፍጹም አሞራ አልበላውም፡፡ የእስር ቤቱ ጭካኔና ስርዓት አጽረጋ ከተባለው ስፍራ እንደጀመሩት ዓይነት ነበር፡፡ የኢዲህ ደጋፊ ነህ፣ ልጅህ ወይም ወንድምሀ የኢዲህ ታጋይ ነው፣ ተብሎ ይያዝና፤ ወደዚሁ ዜሮ ስድስት “ባዶ ሹዱሽተ” እስር ቤት ይወሰዳል፤ … ለጥቂት ቀን ደህና ቀለብ እየተሰጠው በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ ከሌላ ተመሳሳይ እስረኛ ጋር እየተረዳዳ፣ ቢያንስ ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ እንዲቆፍር ይታዘዛል፤ የጉድጓዱ ስፋት ወይም ዓይነት የሰው መቃብር አይመስልም፤ እንደ ውሃ ጉድጓድ ጠበብ ብሎ እየተቆፈረ አፈሩ ዙሪያውን ይከመራል፤ እስረኛው የቁም መቃብሩን ጭሮ እንዳበቃ ይወጣና በገመድ እጅና እግሩ ታስሮ፣ ዓለም በቃኝ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ ይመልሱታል፡፡ ወያኔዎች እስረኛቸው ከመሞቱ በፊት ሲሰቃይ ማየት በጣም ያረካቸዋል፡፡ ቶሎ እንዳይሞት ትንሽ ቂጣና ጥቂት ውሃ በሜንጦ መሳይ በገመድ(በመገለል) ያቀብሉታል፡፡ ሽንትም ሆነ ዓይነ ምድር መፀዳጃው ከዚያችው ጉድጓድ ውስጥ ነው፡፡ አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በኋላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም:: እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋትና፤ በጎኑ መተኛት አይችልም:: ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር፣ ሌሊት በብርድ በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ድቁቋ)፤ ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም:: ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱቋዎች ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል:: … (ሙሉውን አስነብበኝ)
/ጥላቻንና ዘረኝነትን ዘርቶ እኔና እኔን የሚደግፉ ሁሉ ተመችቶናል አትንኩን
እያለ ሰለ ዴሞክራስ፣ ስለ ሰላም እየሰበከ፣ በተግባር ግን ሺዎችን ያሰገደለና  ሺዎችን
ያስደበደበ፣ ሺዎችን እንዲሰቃዩ ያስደረገ፣ ሺዎችን በእስር ቤት እንዲታጎሩ ያሰደረገው፣
የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊና የወያኔ መንግስት ነው::ለምን የወያኔ  አልክ
ለምን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አላልክም ብባል የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃና
ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ የመረጠው የህዝቡ መንግስት ስላልሆነና በመሳሪያ ሃይል
አፍኖ እየገዛ የሚገኝ ስለሆነ ነው::በእኔ እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስት
በኢትዮጵያ ምድር እስካሁን አልታየም::ከወያኔ በፊትም ሆነ አሁን በወያኔ ግዜ
የኢትዮጵያ መንግስት አልነበረም የለም::ምክንያቱም ዴሞከራሲያዊ አሰራር በተግባር
እንዲተረጎምና ህዝቡ በሚፈልገው መልክ የራሱን ሕግ ተወያይቶበት፣ በነፃ በተመረጡ
ተወካዮቹ እንዲፀድቅ የተደረገበት ሆኔታ እስከዛሬ አልታየም:: ህወሓት ወይም ወያኔ
የመከለያ ስሙን ኢሕአዴግ የሚለውን በመጠቀም የራሱን ፍላጎቶች በዋናነት
በመቆጣጠር የሚመራው የጥቂት አምባገነኖች መንግስት ነው:: የወያኔ መንግስት
የነደፈው ሕገ መንግስት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገ መንግስት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም::
ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ደሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ቀድሞም
አልተከበረም:: ዛሬም አልተከበረም::የሀዝቡ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች ሳይከበሩ፣
በወያኔ ካድሬዎች ግልምጫና ማስፈራሪያ ስር ነፃ የሆነ ውይይት ፈፅሞ
አይታሰብም::ስለዚህ ዛሬ የወያኔ ካድሬዎችና ሆድ አደሮች ሊሉን እንደሚሉት ሕገ
መንግስቱ የወያኔ ሕገ መንግስት እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገ መንግስት አይደለም::
አማራጩ ሁሉም በኢትዮጵያ ጥያቄ ያገባናል የሚሉ አካሎች በጋራ ቁጭ ብለው
የሽግግር መንግስት መስርተው፣ አዲስ ሕገ መንግስት በአዋቂዎች ተረቅቆ ሕዝቡ
ተወያይቶበት ሃሳቡን ካሰማ በሗላ በተወካዮቹ አማካይነት ነፃና ዴሞክራሲያዊ በሆነ
መልኩ እንዲፀድቅ መደረግ ይኖርበታል::ባለፉት 21 ዓመታት ራሱ የደነገገውን ሕገ
መንግስት የወያኔ መንግስት እንደፈለገው ሲንደው ተመልክተናል:: በተለይ የሪፖርተሩ
አዘጋጅ አቶ አማረ ከወያኔው መንግስት የበለጠ መፈክሮች እያስነበቡና የወያኔውን ሕገ
መንግስት የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት እንደሆነ ለማሳመን በተደጋጋሚ በቅስቀሳ መልክ
እንደ ርዕሰ አንቀፃቸው በማድረግ እየተሟሟቱ ነው:: አቶ አማረ ሕገ መንግስቱ የወያኔ
ሕገ መንግስት እንጂ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት እንዳልሆነ ከላይ የጠቀስኩትን
ይመልከቱት::
መለስ ዜናዊ የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ የህወሓት ሊቀ መንበርና የኢሕአዴግ
ሊቀ መንበር ነበር::ይሄ ራሱ ግለሰቡ በወያኔ ውስጥ እንደፈለገው ሲጋልብ የነበረና
ያልተስማማውን በማሰወገድ ለ38 ዓመታት ከትጥቅ ትግሉ ግዜ ጀምሮ የራሱን ጓዶች
እያስገደለ ወይም ራሱም እየገደለ ወደ ስልጣን የመጣ ነው::የአሜሪካው የስለላ ድርጅት
ሲ.አይ.ኤ. በነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ምክንያት የደርግን መውደቅ ይፈልግ ሰለነበረናSeite 2

ህወሓትና ሻዕቢያን  እንደ አማራጭ እጩ በመውሰዱና ከፍተኛ እርዳታ በማድረጉም
ጭምር ወደ ስልጣን እንደመጣ ይታወቃል::
መለስ ዜናዊ በአማራውና በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻ
ስለነበረው በአሜረካን የስለላ ድርጅት ወገንተኝነቱ የሚጠረጠረውን ካድሬ ጳውሎስን
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በጳጳስነት እንዲቀመጥና የጥፋት ጉዞውን
እንዲቀጥል አስችሎታል::በአማራው ላይም ብዙ በደሎች እንዲፈጸሙ አድርጓል::
የመለስን ወይም የወያኔ መንግስት ተቃዋሚ የሆኑት የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀመ
በጋምቤላ፣ በኦሮሞ፣ በአኝዋክ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በሲዳማ፣ በሐረር፣ በአዲስ
አበባ ...ወዘተ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን በእሱ ትዕዛዝ ወይም ስምምነት አሰፈጅቷል::
የወያኔው መለስ አሟሟትና የወያኔ መንግስት ፕሮፓጋንዳ ዝግጅት
ማንም ስው የተፈጥሮ ሞትን አንድ ግዜ እንደሚሞት "አፈር ነህና ወደ አፈር
ትመለሳለህ" የሚለው እምነታዊ አባባል በጣም ይገልፀዋል::ስለሆነም የወያኔው መለስ
እንደ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል::ይህ ለማንም የማይቀር ነው::የወያኔው መለስ
የብዙ ሺዎችን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ራሱ ያጠፋ ወይም በእሱ ትእዛዝ እንዲጠፉ
ያሰደረገ ጨካኝና ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ግለሰብ ነበር::የወያኔውን መለስ ሊወዱ የሚችሉት
በአገር ውስጥ የህወሓት ደጋፊዎችና ሆድ አደር ተጠቃሚዎች የሆኑ ብቻ
ናቸው::በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ነፍስ እንደ ውሻ ደም ከንቱ ሆኖ
እንዲቀር ተደርጓል::እነዚህ የወያኔ ደጋፊዎችና ሆድ አደሮቹ በወያኔ በጠራራ ፀሃይ
የተረሸኑትን ዜጎች "ዱርዬዎች፣ ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ነው" በማለት ሲያፌዙ ተደምጠዋል::
ለአስገዳዩና አምባገነኑ የወያኔው መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ
ዓለም በሞት መለየትን ዛሬም ወያኔ ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም አውሎታል::ይህም መለስ
ከሞተ የቆየ እንደሆነና የወያኔ ሰዎች ግን አስከሬኑን አሰቀምጠው ይህንን ለእነርሱ
የወደፊት ፖለቲካ ትርፍ እንዴት እንደሚጠቀሙ ከተወያዩ በሗላ፣ የኢትዮጵያን
ሕዝብ በትእዛዝ፣ በማስፈራራት፣ ገንዘብ በመስጠት፣ አልቃሾች በመቅጠር፣ የወያኔን
መንግስት ሚዲያዎች በሰፊው በመጠቀም ህዝቡ ለቅሶ በየቀበሌው እንዲደርሰና
እንዲያለቅስ ማሰደረግ፣ እስከዚያ ደግሞ የተለመደ የውጭ አገር መሪዎች ለወያኔው
ጠቅላይ ሚኒስትር የሃዘን መልእክት እንዲያደርጉ ሰፊ ግዜ በመስጠት፣ የወያኔ
ደጋፊዎችና ሆድ አደሮችን በማስፈራራት እስካሁን ያለው ሁኔታ ካልቀጠለ አደጋ
እንዳለው በማሰገንዘብ፣ የለቅሶ ድራማ ዎችን በሚዲያ በመቅረጽ የወያኔን የ21 ዓመት
ፖለቲካ ለመቀጠል መቀስቀሻ አድርጎ ወያኔ ተጠቅሞበታል::
በቀብሩ ስነ ስርዓትም የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችም ጨካኙንና አስገዳዩን
የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰላም ጳጳስ አድርገው ለማቅረብ ጥረዋል::ምክንያቱም
አምባገነን መሆን፣ የራስን ሕዝብ መግደልና ማፈን ይህን ያህል "ክብር" የሚያሰገኝ
ከሆነ፣ ለእነርሱም ወደፊት በዚህ መልክ መቀጠል የሚያስችላቸው ስለሚሆን ነው::ይህንን
መድረክ የአሜሪካዋ አምባሳደርም ለራሳቸው ፖለቲካ ለመጠቀም ሞክረዋል::ምክንያቱም
ያሁኑ የፕሬዚደንት ኦባማ መንግስት ባላፈው ምርጫ ወቅት የአሜሪካ ህዝብ ታክስ
ከእንግዲህ ወዲያ ለአምባገነኖች እንደማይሰጥ ገልፀዋል::መንግስታቸው ግን የአሜሪካንንSeite 3

ህዝብ የታክስ ገንዘብ በእርዳታ መልክ ለወያኔ አምባገነን መንግስት በመስጠት
ተግባራዊ አድርጓል:: ይህንን የወያኔን አምባ ገነናዊ መንግስት ሌላ ስዕል በመሳል
ሰይጣኑን መልዓክ ለማድረግ የሚደረግ የማያዋጣ ፖለቲካ ስለሆነ፣ ለዚህ ሽፋን
ለመስጠት የወያኔውን ጠቅላይ ሚንስትር አምባሳደሯ 6) መካብ ነበረባቸው::
የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትርና የህወሓት ሊቀ መንበር የነበረው መለስ ዜናዊ
ትግራይ ውስጥ በትጥቅ ትግሉ ወቅት የትግራይ ተወላጆችን በትግራይ ውስጥ እንዴት
እንዳስጨረሰና እንዳሰቃየ አቶ ግደይ ባሕሪሹም በ1985 ዓ.ም. በፃፉት መጽሐፍ ውስጥ
ጥቂት ነጥቦችን ማስነበቡ ጠቃሚ ይሆናል::
የወያኔ ሽብር በትግራይ
"ከሰላሳ ሁለት ጊዜ የወያኔና የኢዲህ ጦርነት እልቂት ሌላ፣ አገሩ በወያኔ ቁጥጥር
ስር ከዋለ በሗለ፣ የኢዲህ ደጋፊ ነበርክ፤ ነበርሽ ተብለው በወያኔ አፈሙዝ እየተረሸኑ፣
በየፈፋውና ጋምስቱ የተደፉት፣ አፈር ተነፍጎአቸው ፀረ ትግራይ "ኮራ ኹር አምሓሩ"
(የአማራ ቡችላ) እየተባሉ ለአሞራ ቀለብ የሆኑትን፣ የወለደና የተወለደ፤ ተሸማቆ ያዬ
ቤት ጎረቤት ይቁጠራቸው::"1)
በእርስ በእርስ ጦርነት ከአለቀው ይልቅ፣ በጥርጠራና በጥቆማ ተይዘው፣ ለዘርና
ለታሪክ እንዳይተርፍ፣ በስውር "በማዞር" 1) (በሻዕቢያ ባንዶች) ያለቀው የትግራይ
ሕዝብ እጥፍ ድርብ ነው::2)ከክፍለ ሃገርዋ ከተማ ከመቀሌ ጀምሮ፣ በስምንቱ
አውራጃዎችና በ አምሳ ሁለቱ ወረዳዎች ያለው ሕዝብ፤ ፈጠን ብሎ ለእነሱ (ለወያኔ)
በርከክ ከአላለና፣ ትግሬና አማራ ወይም ኢትዮጵያና ትግራይ በሚለው መሰረታዊ
መፈክራቸው ላይ፣ ጥያቄ ያቀረበ ሰው ሁሉ፣ ኢዲህ ነው፤ እየተባለ ወላጅ በልጁ
እንዲመታና እንዲረሸን ያደረጉት የሻዕቢያ ባንዶች፣ በግማሽ ከ ኤርትራ ክፍለ ሀገር
በመወለዳቸው፣ ለነገው ትውልድ ጥቁር ታሪክና የማይደርቅ ደም አተረፉ እንጂ፣
በተተኪው የትግራይ ትውልድማ ለልጆቻቸው ቂም አትርፈው፣ አመላቸውን ይዘው
በተራቸው ማለፋቸው አይቀርም::ከናዚ ጀምሮ የነበረ አረመኔ ሁሉ አላልፍም ብሎ
ዘላለም የኖረ ሰው የለም::ይህች የ አረመኔዎችና የከሃዲዎች፣ የትምክህተኞችና
የቂመኞች ዘመን በተራዋ ሳትወድ ታልፋለች::ትውልድና ታሪክ ግን ይቀራሉ::"2)
"ቆጥቋጦና ታሪክ ከመቃብር በላይ ነው" ተብሏል::ደርግ በቀይ ሽብር የከተማውን
ወጣት ሲጠርግ የሻዕቢያ ቅጥረኛ ወያኔም፣ ትግራይ ውስጥ በገጠሩ፣ ኢትዮጵያዊነቱን
ያልከዳና እምነታቸውን ያላመነ ገበሬውንና ወዝአደሩን  "ኾራኹር አምሓሩ፣ ሸዋዊያን
ተጋሩ"(የአማራ ቡችላ፣ ሸዋዊያን ትግሬዎች) እያለች፣ የኢዲህ ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና
አዝማድ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ፣ በሬና ላሙን፣ በግና ፍየሉን፣ አህያና በቅሎውን፣ ዶሮና
የጎተራ እህሉን፤ ማርና ቅቤውን፤ እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ለሐማሴኖች መደሰቻ
ተብሎ፣ ለሻዕቢያ ያልሰገደ፣ ምስኪን የትግራይ አራሽ ገበሬ፣ ዘር ምንዛሩ ከምድር
እንዲጠፋ እየረሸነች፤ ለሌሎች መቀጣጫ ተብሎም በወጉ በቤተዘመድን በጎረቤት
እንዳይቀበር፣ ለንቃተ ህሊና ትምህርት ወደ በረሃ ተልኳል እየተባለ፤ ሳይመለስ የቀረው
የቤትና ጎረቤት ሰው ታዝቦ ይቁጠረው::"2)Seite 4

የትግራይን ሕዝብ  ለፖለቲካ ትርፍ መጠቀም
"በትግራዊነቱ ወኔማ ቢሆን ኑሮ፣ በእውነቱ የወያኔ ትግራይ መሪዎች ሙሉ
በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ቢሆኑ ኖሮማ፤ ጀብሃን በቀጡበት ጅራፍ ሻዕቢያን እየላጡ
ወስዶ ከሰላ ከዘመዶቻቸው ከጀብሃ ሰራዊት ጋር ማቀላቀል ነበር::ምን ይሁን ታድያ
ትግራይ በስንዴውና በማሽላው ያሳደጋቸው ዘረኞች፤ ትግሬ መስለው ገብተው
እንደተባይ ከትግራይ ሕዝብ ራስ ላይ ሰፍረው፤ እንዲያውም የሚያማግጡበትን ገንዘብ
ለመለመን እንዲያመቻቸው፤ ገበሬውን ሕዝብ እርዳታ የምታገኝበት መንገድ ጥርጊያ
ጥረግ እያሉ በመለስ ዜናዊ መሐንዲስነት፤ በቀን ብርሃንና በሌሊትም በችቦ ጋራውን
ከመሀል ትግራይ ከተንቤን ጀምሮ ምዕራብ ትግራይን አቋርጦ፤ በገንደር ወልቃይት
ጠገዴና፤ አርማጭሆ በረሃ አቋርጦ፣ እስከ ምስራቃዊ ሱዳን በር ወዲ ኸውሊ ድረስ
ወስደው እንዳይሰጡት፤ሕዝቡ ራሱ በጠረገው ጥርጊያ በጅምላ ሱዳን በር ድረስ
እንዲሰደድ አስገደዱት::"3)
ላምና ፍየሉን እኛው እንጠብቅልሃለን ብለው፣ ያለ ፍላጎቱ ስደት የዳረጉት
ሕዝብ፤ ህፃን ሽማግሌ ወዲ ኸውሊ ከተባለው በረሃ በበሽታና በርሃብ በቁርጠትና
በተቅማጥ እየተነዳ፤ እንደ ቅጠል በጅምላ ሲረግፍ፤ የዓለም ጋዜጠኖችን ጋብዘው ለበጎ
አድራጊ ድርጅቶች፤ "ለሕዝባችን የሰጣችሁን የ እህል እርዳታ አልበቃ ብሎ፤ ይኸው
ህዝባችን በረሃብ ረገፈ ከዚሁ መጥታችሁ ማየት ትችላላችሁ::እያሉ መለመኛ አደረጉትና
በእርዳታ የሚሰጣቸው እህልም ሽታውን ብቻ ለሕዝቡ እየሰጡ በቶን ለሱዳን ሀብታም
ነጋዴዎች ሸጠው ተዝመነመኑበት::4)
የወያኔ ሲኦል በትግራይ
"ደደቢት ከወያኔ መሰረታዊ ሜዳ ላይ፣ ዜሮ ስድስት (ባዶ ሹድሽተ) ተብሎ
የሚጠራ እስር ቤት፤ ለትግራይ ሕዝብ የናዚ ስርዓት የሚፈጽሙበት ነበር::ይህ ከአደጉ
በሗላ (ምስገበሉ) የተመለሱበት ሜዳ ስለነበር፤ ለሞት ተፈርዶ ወደዚሁ ሜዳ የሚላክ
እስረኛ፤ ስጋውን በፍጹም አሞራ አልበላውም::የእስር ቤቱ ጭካኔና ስርዓት አጽረጋ
ከተባለው ስፍራ እንደጀመሩት ዓይነት ነበር::
የኢዲህ ደጋፊ ነህ፣ ልጅህ ወይም ወንድምሀ የኢዲህ ታጋይ ነው፣ ተብሎ
ይያዝና፤ ወደዚሁ ዜሮ ስድስት "ባዶ ሹዱሽተ" እስር ቤት ይወሰዳል፤ እንደደረሰም ስለ
ንብረቱ ብዛትና መጠን የትስ እንዳለ ይጠየቃል::መጠይቁ እንደበቃ ለጥቂት ቀን ደህና
ቀለብ እየተሰጠው በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ ከሌላ ተመሳሳይ እስረኛ ጋር እየተረዳዳ፣
ቢያንስ ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ 4) እንዲቆፍር ይታዘዛል፤ የጉድጓዱ
ስፋት ወይም ዓይነት የሰው መቃብር አይመስልም፤ እንደ ውሃ ጉድጓድ ጠበብ ብሎ
እየተቆፈረ አፈሩ ዙሪያውን ይከመራል፤ እስረኛው የቁም መቃብሩነ ጭሮ እንዳበቃ
ይወጣና በገመድ እጅና እግሩ ታስሮ፣ ዓለም በቃኝ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ
ይመልሱታል::ወያኔዎች እስረኛቸው ከመሞቱ በፊት ሲሰቃይ ማየት በጣም
ያረካቸዋል::ቶሎ እንዳይሞት ትንሽ ቂጣና ጥቂት ውሃ በሜንጦ መሳይ በገመድSeite 5

(በመገለል) ያቀብሉታል::ሽንትም ሆነ ዓይነ ምድር መፀዳጃው ከዚያችው ጉድጓድ ውስጥ
ነው::5)
አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በሗላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት
የለም::እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋትና፤ በጎኑ መተኛት
አይችልም::ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም
ብቻ ነው::ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር፣ ሌሊት በብርድ በጤዛ እየተሰቃየ፤
የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ
በሚፈጠሩት ትሎች (ድቁቋ)፤ ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት
የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም::ቆዳውን ሰርስረው፣
ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና
በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱቋዎች ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም
ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ
ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው
ቅብር ያድርጉታል::"5)
ሰላምና ዴሞክራሲ እውን ተትረፍረፏል?
በወያኔ መንግስት የዜና ማሰራጫ በኩል ሰላምና ዴሞክራሲ ተትረፍርፏል
የሚለው ሰው በአስተሳሰቡ የተለየ በመሆኑ የሚሰቃይበት፣ የሚደበደብበት፣
የሚታሰርበትና የሚገደልበት አገር ኢትዮጵያ ስለመሆኗ ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው::
ወያኔና ሆድ አደሮች ያደጉበትና የተካኑበት ሸፍጥ ስለሆነ እውነታውን መቀየር ግን
አይችሉም::ወያኔና የወያኔ መንግስት ዘረኛ፣ አምባገነንና ፀረ-ኢትዮጵያ ነው::ይህም
የወያኔ መሰረታዊ ማንነቱ ነው::
መከላከያና ደህንነቱን መቆጣጠር
የወያኔ መንግስት እስካሁን መከላከያና ደህንነቱን በወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር
እዝ ስር ነበር::ወደፊትም ከዚህ የተለየ ነገር ይኖራል ብሎ ማሰብ አሰቸጋሪ ነው::በምንም
መልኩ ከእነርሱ እጅ እንዲወጣ እንደማይፈልጉ በአዲሱ የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር
ምርጫ ላይ የተወሰኑ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው:: በረከት ስምዖን ሰሞኑን ተጠይቆ
መለስ የሚሊቴሬ ችሎታ ስለነበረው የመከላከያው እዝ በእሱ ስር እንደሆነ የሚጠቁም
አባባል ሰንዝሯል::ይህ ማንም እንደሚገባው የወያኔ ሰው ወይም ሰዎች የመከላከያውንና
ደህንነቱን እንደሚይዙ መጠርጠር ተገቢ ነው:: በተጨማሪም የ34 ብርጋዴር ጄነራሎች
ሹመት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ምርጫ በፊት ለምን ተቻኮለ የሚለውም ሊጠየቅ የሚገባ
ጥያቄ ነው::
ማጠቃለያ
በወያኔው ጠቅላይ ሚኒሰትር ሞት ምክንያት ሰውየውን መልዓክ ለማድረግ
በከፍተኛ ደረጃ ወያኔና ሆድ አደሮች እየተንቀሳቀሱ ነው::መልዓክ ገዳይ ከሆነ፣ መልዓክSeite 6

አምባገነን ከሆነ፣ መልዓክ ገዳይ ከሆነ፣ መልዓክ ሌሎችን የሚያሰቃይ ከሆነ፣ የወያኔውም
ጠቅላይ ሚንስትር መለስን መልዓክ ሊያደርጉት ይችላሉ::በሁላችንም የሚታወቀው
መልዓክ ግን የዚህ ሁሉ ተፃራሪውን ነው::ስለዚህ የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ሊሆን
የሚችለው መልዓክ ሳይሆን ዲያብሎስ ነው::ምክንያቱም ዘረኛ፣ አምባገነን፣ ጨካኝና ክፉ
በመሆኑ ነው::ወደፊትም በዚሁ በግፍ አገዛዝ ወያኔና የወያኔ መንግስት ለመቀጠል
ከፍተኛ የቅስቀሳ ፕሮፓጋንዳ እያካሄዱ ናቸው::
የወያኔ ደጋፊዎች በትግራይ ሕዝብ ስም ለመነገድ የምትሞክሩትንና ብብሄርና
ብሄረሰብ መብቶች ቀዳሚ አስከባሪነት ራሳችሁን አባ ወራ እንደሆናችሁ ለማስመሰል
የምታደርጉትን ሃቀኛ ያልሆነ አካሄድ ረጋ ብላችሁ በማሰብ፣ ከሌሎች ተቃዋሚ
ድርጅቶችና ሌሎችም ስለ ኢትዮጰያ ያገባናል ከሚሉ ተቅዋማት ጋር በጋራ
ተቀምጣችሁ ለሁሉም የሚስማማ ዴሞክራሲያ ስርዓት የሚፈጠርበትን ሁኔታ
ለማመቻቸት ጥረት ብታደርጉ መልካም አማራጭ ይሆናል::

No comments:

Post a Comment