"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 20 September 2012

በነ እስክንድር ላይ አስገራሚ ውሳኔ ተላለፈ።በውርስ ያገኘው ቤት እንዲነጠቅ ተብሏል ዘገባው የደረጀ ሃብተወልድ ነው !



በነ እስክንድር ላይ አስገራሚ ውሳኔ ተላለፈ።
1-እስክንድር ነጋ ፦በስሙ ተመዘገበ ባለ አንድ ፎቅ ቤት እና <<በውርስ ከቤተሰቡ ያገኘው ‘ግራውንድ ፕላስ ቱ’ ቤት
2-አንዷለም አራጌ በስሙ የተመዘገበ አንድ መኪና እና
3-አበበ በለው በሚስቱ ስም የተመዘገበ <<ግራውንድ ፕላስ ዋን>> ቤት እንዲታገድ ተብሎ ነው ውሳኔ የተላለፈው።
ስለማውቀው ልናገር፦

በጣም የሚገርመው ነገር፤ እስክንድር ነጋ እናቱ ከማረፋቸው በፊት ቤታቸውን ሲያወርሱት፦” አልፈልግም !”በማለት ውርሱን ያልተቀበለ ሲሆን፤ አሁን እንዲታገድ የተባለው በውርስ የተገኘ ቤት የእርሱ ንብረት አለመሆኑ ነው።
በአጭሩ ላብራራ፦ውርሱ የሚገባው ለእሱ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ እናቱ በጣም የሚወዱትና የሚሣሱለት ብቸኛ ልጃቸው ስለሆነ ጭምር ሽማግሌዎችን ሰብስበው የቤቱን ኑዛዜ እንዲቀበል ይጠይቁታል። እስክንድር ግን ገንዘብና ንብረትን አስቀድሞ የናቀ ልጅ በመሆኑ ፤ ከአቋሙ ሊነቃነቅ አልቻለም። በመጨረሻም ቤቱ የአባቱ ልጅ ለሆነች እህቱ ተሰጠ። ውርሱ ለእሷ ጸና።
ዛሬ ይህ የእህቱ ቤት ነው እንዲታገድ የተወሰነው። የእስክንድር እህት፤እህት በመሆኗ ብቻ ንብረቷ ታገደባት። ከእስክንድር ቤተሰብ መወለዷ፤ እንደ ወንጀል ተቆጠረባት።ቤቷን አጣች።

ቢሆንም፤የፍትህ መዛባት ጉዳይ ያሳዝነው ካልሆነ በስተቀር ይህ የቤት ማገድ ውሳኔ ከንብረት ማጣት ጋር በተያያዘ እስክንድርን ቅንጣት ታህል እንደማይጎረብጠው እርግጠኛ ነኝ። እንደውም በውሳኔው ላይ አስተያዬት እንዲሰጥ ቢጠየቅ ኖሮ በደስታ ፦” ሌላ የምትፈልጉትና የቀረ ነገር ካለ ጨምራችሁ ውሰዱ”ሊላቸው እንደሚችልም እገምታለሁ።ለእስክንድር፦ መቀበል ዕዳ፤መስጠት ብጽዕና መሆኑን አውቃለሁና።አዎ <ከሚቀበል የሚሰጥ ሰው ብጽዕ ነው>እንዲል መጽሐፉ፤ እስክንድር መስጠት እንጂ መቀበል አይወድም።ደሞ ለቤት ንብረት!
እንዴ! ከሁለት ዓመት እስር ቆይታ በሁዋላ፣ ከሁለት ዓመት ሥራ መፍታት በሁዋላ፣ የቢሮ ንብረቶቻቸው ተወርሰውባቸው ፣በሥራ እንዳይሰማሩ ተከልክለው ..እና በሌሎች ብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነው በነበረበት በዚያ ወቅት እንኳ ሰርካለም የተሸለመችውን 5 ሺህ ዶላር፤ በችግር ላሉ ጋዜጠኞች መርጃ ይውል ዘንድ ለዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ኮሚቴ(ሲፒጄ) ያበረከቱኮ ናቸው-ጀግኖቹ ጥንዶች።
አንድ ነገር ግን ሁላችንንም አሳዝኖናል-ከኢዲሱ አመራር ጋር በብልጭታ መጠንም ቢሆን ብቅ ትል ይሆናል ብለን በተስፋ የጠበቅናት የፍትሕ ፀሀይ ይብስ እያዘቀዘቀች መሄዷ።
አቶ ሀይለማርያም፤ ይህን እያዩና እየሰሙ ነው? ?

No comments:

Post a Comment