"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 18 September 2012

ከመለስ የተላከ ደብዳቤ



     
ከመለስ  የተላከ  ደብዳቤ
ለውድ ተጋዳላይ ጎደኞቼና ዘመዶቼ እንደምን አላችሁ፤ አኔ እግዚአብሄር ይመስገን ደህና ነኝ;; ያእግዚአብሄርን ስም ጠራህ ትሉኝ
ይሆናል ግምገማ ስላለ ነው;; መቼም ድንገት በመሄዴ እንደ ደነገጣችሁና እንደ ተረበሻችሁ አባ ጻውሎስ ነገሩኝ፤ በመንፈስ ከኔጋር
ልትተባበሩ በስጋ አጥምቄአችሗለሁና ሁሌም መንፈሴ ከናንተ ጋር ነው;;የኔን ቦታ የሚተካ ሰው ውስጣችሁ እንደሌለ አውቃለሁ;;
በዚህም ምክንያት ሀያ አንድ አመት ለናንተ መኖሬን ታውቃላችሁ አሁንም ማድረግ ያለባችሁ መከላከያውን አጠናክሩ ጠቅላላ
መከላከያውን ከተቐጣጠራችሁ ማንም ምንም ሊያመጣባችሁ አይችልም;; የብሄር ተዋጽዎ የለውም ብለው ቢያወሩባችሁ
አትስሞቸው እስከመቸም መንግስቱን እደፈለጋችሁ የምታዙበት ቁልፉ ነገር እሱ ነው;; ቃሌን አድምጡ ፖሊሲየን ጠብቁ ራዕየንም
አትዘንጉ;;ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን ሌላም እምቢ ያሏችሁን ልታስሩና ልትፈርዱባቸው አትፍሩ አንዳንድ ትችቶች ሊሰነዘርባችሁ
ይችላል ቦታ አትስጡት;; ምእራብያኖችን ስሟቸው እድሜአችሁ ይረዝማል አድርጉ ያሉአችሁን አታቅማሙ ይጠብቛችሗል
ስትከፉም መሸሸጊአችሁ ናቸው;; ከቻይና ጋር ስራችሁን አብዙ ለመስረቅና ለመከፋፈል ይመቻሉ;; በተረፈ ላለቀሱልኝ ደጉሟቸው
ለአናተም ይጠቅሟችሗል፤ ውሻ የሚበላው አይጎዳም ስራው ግን ትልቅ ነው;; ሌላ ካአባ ጳውሎስ ጋር አንድ ለይ ነን ያለንበት ቦታ
ብዙም አይመችም እነ ጋዳፊም እዚሁ ናቸው እኔም አባጻውሎስም ፍርድ ቤት ቀርበን ነበር፤ የአባታችን ጉዳይ በልዩ ፍርድ ቤት
እንዲታይ ትዛዝ ተሰጥቶበታል፤ የኔ ግን በጣም ይገርማችሗል የክስ መዝገቡ ተነቦ እስከሚያልቅ ብቻ ሀያ አንድ ዓመት ያስፈልጋል
ስለተባለ፤ የዋስ መብት አንዲከበርልኝ ጠይቄ ነበር? አቃቢ ህጉ የተከሰሱበት ክስ ፈፅሞ ዋስትና ሊያሰጣቸው አይችልም በሁለተኛ
ደረጃ ደግሞ ሰውየው ጫካ የነበሩ ስለሆነ አሁንም ጠፍተው ጫካ ይገባሉ ብሎ ስላቀረበ በዚሁ ሆኛ እድከታተል ፍርድ ቤቱ
ወስኗል;; ዳኛው ገርሞአቸው ሀያኛው ከፍለዘመን ከገባ እንደዚህ ክሱ እንዳተ የበዛ አላየሁም ብለው ባግራሞት ነው ያዩኘ
ለማንኛውም ሁላችሁም መምጣታችሁ አይቀርም፤በምድር የሰራንውን ወንጀል አንድ ላይ ስለሆነ እዚህም አንድ ለይ ነን;;
ይቀጥላል………//

No comments:

Post a Comment