"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday, 2 February 2013

Artist Abebe Melese አበበ መለሰ ህይወቴን ታደጔት ድረሱልኝ ይላል

 


ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ ብዙ የኢትዬጵያ ሙዚቃዎች ጀርባ ሁልጊዜ ስሙ ይጠራል። በ1970 ዎቹ እና 80 ዎቹ ከተሰሩ ሙዚቃዎች የአብዛኞቹ የዜማ ደራሲ ነዉ ቢባል ማጋነን አይሆንም።
abebe melese
Account number: 1000033097453
Owners: Tsegaye Eshetu and Hailye Tadesse and Dawit Yifru
Commercial Bank of Ethiopia, Finfine Branch, Addis Ababa
Swift code: CBETETAA
Tele: +251115518844
ከ ሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ የዜማ፣ ግጥምና ቅንብር ስራዎች ባለቤት አበበ መለሰ።
ለተወዳጆቹ ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ አስቴር አወቀ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ አረጋሃኝ ወራሽ፣ ኬኔዲ መንገሻ እና ለአያሌ ሌሎች ድምፃውያን በሳል የዜማና የግጥም ስራዎችን አበርክቷል።
በሁለት አስርት አመታት ውስጥ ሁለት ሺህ የሚደርሱ የዜማ፣ የግጥም እና ሙዚቃ ቅንብር ስራዎችን ሰርቶ በኢትዬጵያ ሙዚቃ ውስጥ የማይረሳ አሻራውን አሳርፏል።
እነዚህን ዘመን የማይሽራቸው ሙዚቃዎችን አምጦ ሲወልድ ለከፋ የደም ግፊት በሽታ በመጋለጡ የጥላሁንን ‘ኢትዬጵያ’ ስራ ከሰራ በኋላ የዜማ ስራ እንዳይሰራ በሀኪም ትዕዛዝ ከሙዚቃ ስራ ለረዥም ጊዜ ተገሏል።
በአሁኑ ሰዓት አበበ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ላይ ይገኛል ሁለቱም ኩላሊቶቹ አገልግሎት በማቆማቸው በህይወት ለመቆየት በሳምንት 3 ቀናት አርቲፊሻል የደም ማጣራት (Dialysis) ማድረግ ግድ ሆኖበታል።
አበበ በአሁኑ ጊዜ የኩላሊት ተከላ መቀበል ይችላል። ነገር ግን ህክምናዉን ለማድረግ አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ የአሜሪካን ዶላር (150,000.00 USD) ያስፈልገዋል። አበበ ህይወቴን ታደጔት! ድረሱልኝ! ይላል።
አበበን ህይወት ለመታደግ ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት እንድናደርግ!!!
source : bawza ድረገፅ

መሪዎቻችን እነማን ናቸው አርቲስቶቹ ወይስ ታጋዮቹ?

   … ከመሞታቸው በፊት የተጻፈ
አቤ ቶክቻው
ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው ለዛሬው የፍትህ ጋዜጣ ጨዋታችን በዋነኛነት ይዤ የመጣሁት ጉዳይ መሪዎቻችን እነማን እንደሆኑ የሚጠይቅ ነው። ያው እንደተለመደው ሌሎች ጨዋታዎችም ይኖሩናል። አውራ ርዕሱ ግን “መሪዎቻችን እነማን ናቸው… አርቲስቶቹ ወይስ ታጋዮቹ?” የሚለው ይሆናል። “ለፓርቲ አውራ እንዳለው ሁሉ ለጨዋታም አውራ አለው።” እንልና ገዢው ፓርቲን ገልመጥ እናደርጋለን…
ለበርካታ አመታት በኤርትራ እስር ቤት እየማቀቀ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ አውሮፕላን አብራሪ በዛብህ ጴጥሮስ እንዲፈታ ሲል ታዋቂው አርቲስት ታማኝ በየነ በቅርቡ ለኤርትራ መንግስት ልመና አቅርቧል። እርሱን በሰማን በስንተኛው ቀን ድግሞ ሌላው ታዋቂ እና ተወዳጅ አርቲስት ቴዲ አፍሮ በሶማሌ ፑንት ላንድ ታስሮ ሞት ሊፈረድበት ጥቂት የቀረውን ወጣት አስመሮምን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ከፍሎ አስፈትቶታል። በእውነቱ እነዚህ አርቲስቶቻችን እያከናወኑ ያሉት እንደ አርቲስት ሳይሆን እንደ መንግስት ነው። የመንግስት ዋና ሰዎቻችን ደግሞ በየ ፓርላማው እና በየ መድረኩ የሚሰበስቡትን ሰው በሳቅ ሲያፈርሱ ስናይ “ታጋዮቹ አርቲስት፤ አርቲስቶቹ ደግሞ መንግስት ሆኑ እንዴ?” ያሰኛል። ቆይ ቆይ ይችን ታህል ለመግቢያ ካልን በመጀመሪያ አንዳንድ መልዕክቶች አሉኝ በአዲስ መስመር ላይ እንገናኝ… ታድያ ቀጠሮ ይከበር…

Wednesday, 30 January 2013

የእግር ኳሳችንና የኤፍ ኤም ሬዲዮናችንን፡እኔ ነደታዘብኩት........ እናንተስ....እንዳለ ጌታነህ ከኖርዌ



በመጀመሪያ እንኳን ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት አሸጋገረን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለቴ ነው፤በፌስ ቡክ ላይ አንድ ነገር አነበብኩና  ፈገግ አልኩኝ ምን ይላል መሰላችሁ፤ሰበር ዜናን በረኞቻችን አርገውት የገቡት የካራቴ ጫማ ተመሳሳዩ  ጆሀንስበርግ ላይ እየተቸበቸበ ነው።;
;                ሶስት ጨዋታ አድርገን ሶስቱንም   ጨዋታዎች በሙሉ ተጨዋች  አልጨረስንም ሶስት ተጨዋቾች ለቀይ ካርድ ሰለባ ሁነዋል ሁለቱ የኛ  ግብ ጠባቂዎቻችን ሲሆኑ  አንዱ ግን የቡርኪና ፋሶ ተጨዋች ነው ። እኛ ከዛምቢያ ጋር  በጎዶሎ  ልጅ ጎል ስናስቆጥር ቡርኪና  እኛ ላይ በጎዶሎ ልጅ አራት አገባብን፤ እንግዲህ ለዚነው የካራቴ  ጫማ በስማቸው የተሰየመላቸው።ግን የበረኝነቱ  ልምምዱ ካራቴንም ያካተተ ነበር ? ወይስ የበረኞቹ አሰልጣኝ ካራቲስት ነበር  ? ዋናው ግን መረሳት የሌለበት ገጠመኝ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋችን ሶስት ጨዋታ ተጫውትን በአንዱ አቻ ስንወጣ በሁለቱ ስንሸነፍ ሰባት ጎል ሲቆጠርብን አንድ ብቻ ማስቆጠራችን ፤ለእኛ ጎሉን ያሰቆጠረው ሰባት ቁጥር መሆኑ፤ ሁለት ቀይ ካርድ ስናገኝ ሁለቱንም ቀይ ካርድ ያገኙት በረኞቻችን መሆናቸውና ደጋፊዎች አጠፉ ተብሎ  አምስት ሺ ዶላር መቀጣታችን ነው።    ለጽሁፌ  አርስት የለውም ስለዚ የፈለኩትን   ደስ ያለኝን ሃሳብ አነሳለው አይዟችሁ አላሰለቻችሁም፤

እስኪ ደግም ሸገር ኤፍ ኤምን እንቦጭቅ አዎ ማን ነበር ባለፈው ለጊዜው ስሙን የረሳሁት ጸሀፊ ይቅርታ አስታውሻለው ዳንኤል ክብረት ነበር    ምን አለ  መሰላች ኤፍ ኤሞቻችንን መልሱልን በሚለው ጽሁፉ፤   በአንድ የኤፍ ኤም ራድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም ታክሲ ውስጥ ሆኜ እየሰማሁ ነበር፡፡ «ጋዜጠኛው» ቀብሩ በትናንትናው ዕለት ስለተፈጸመ አርቲስት ተናገረና «rest in peace ብለናል» አለ፡፡ የአፍ ወለምታ ወይንም ልማድ ነው ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አሁንም ስለ ሌላ ስለ ዐረፈ ሰው ተናገረና ያንኑ ደገመው፡፡ ይኼኔ ደነገጥኩ፡፡ ይኼ የኤፍ ኤም ሬዲዮ በአማርኛ ቋንቋ ለሕዝበ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነው፡፡ አሁን «ነፍስ ይማር» የሚለው የአማርኛ ቃል የሚጠፋው ጋዜጠኛ እንዴት ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጉዳዮች ሊያነሣ የሚችለው?ቀጠለ አሁንም ዳነኤል የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው
እንደሚለው የሠርግ ዘፈን እንግሊዝኛ ማወቅ የዕውቀት መለኪያ ነው? ለነገሩ እርሱ ምን ያድርግ «ቢሾፍቱ አውቶቡስ? ብሎ መጻፍ ሲቻል «ቢሾፍቱ ባስ» ብሎ ጽፎ በከተማዋ ውስጥ በኩራት በሚዞርባት ሀገር፣ «ልዩ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ስፔሻል ክትፎ» «ተራ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ኖርማል ክትፎ» ተብሎ የጉራጌ ክትፎ እንግሊዛዊ በሚሆንባት ሀገር «ነፍስ ይማር»ን አለማወቅ ነውር ላይሆን ይችላል፡፡ መቼ በዚ አበቃ ዳንኤል «good bye have a nice weekend´ ብለው ተሰናበቱንና ሌሎች ደግሞ መጡ፡፡ ስለ ውጭ ሀገር ዘፋኞች፣ የፊልም ተዋንያን፣ ፊልሞች እና ዘፈኖች እንደሚያወሩን፣ ስለ አንዳንዶቹም ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጡን ነገሩንና ለመሸጋገርያ ብለው የእንግሊዝኛ ዘፈን ጋበዙን፡፡
ይኼኔ ነው ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች የማን ናቸው? እያልኩ መጠየቅ የጀመርኩት፡፡ አንድ ዓይን ያላት በዐፈር አትጫወትም ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ጥርስ የላት በዘነዘና ትነቀስ አማራት ብሎም ይጨምርበታል፡፡ ለራሳችን ኤፍ ኤም ሬዲዮ እና ስኳር እያጠረን ተቸግረናል፡፡ ከነዚሁም ቆርሰን ለፈረንጆቹ ከሰጠናቸው ምን ሊተርፈን ነው? ወይስ እነርሱ ለኛ ብድር እኛ ለእነርሱ ሬዲዮ ልንሰጣቸው ተስማምተናል፡፡   ብሎ መርር አድርጎ  ጽፎ  ነበር ዛሬ እኔ ደግሞ ጊዚዬን መልስሉኝ እላለው ፤ማን አዳምጥ አለህ ? ማን አስገደደህ ? ካላችሁም ዜግነቴ  ብቻ በቂ ነው ኢትዮጵያዊ ሆኜ መፈጠሬም በቂ ነው እላለው።                                              ወደ ተነሳሁበት ሀሳብ ልገስግስ በተለይ ሰይፉ የተባለ ፎጋሪ ከነ ልጆቹ የሚሞላፈጡበት  ታዲያስ አዲስ የተባለው ፕሮግራም በቀን  ካለው የሁለት ሰዓት የአየር ላይ ዝግጅት  ምን አለፋችሁ በፐርሰንት ብናስቀምጠው 80 ፐርሰንት ማስታወቂያ፤ 10 ፐርሰንት ሰዓት ዕወጃ፤7 ፐርሰንት ሙዚቃና፦3 ፐርሰንት ዋናው ፕሮግራም ነው ።ዋናው ስል እነሱ ማይክ ይዘው እየገለፈጡ በሰው ሃዘን  የሚቀልዱበትን ማለቴ ነው። ሙዚቃውም ቢሆን የሚቀርቡት  ለአዘጋጆቹ ዳጎስ ያለ ጉቦ  የሰጡ ናቸው።ግለሰቦች ለሚያዘጋጁት ኮንሰርት  በተለይ አዲካ   ከሆነ  ጭቅጭቅ በሉት  የሆነ ነገር ጆሮሯችሁ እስኪቃጠል ትነዘነዛላችሁ።እንግዲህ እዩት የመዝናኛ ፕሮግራም ተበሎ የተያዘለትን ሰዓት ባልባሌ ማስታወቂያ  ያልቃል።  [ላዳማጩ ማለቴ ነው]እነሱማ ገንዘባቸውን ከማስታወቂያ ያገኛሉ  ፡ዝም ብለው  ታዲያስ አዲስ ከማለት ማስታወቂያ አዲስ ቢባልስ ወይም የመዝናኛ ፕሮግራም ከማለት ይልቅ የእከክልኝ ልከክልህ ፕሮግራም ቢባል፤ ጥሩ አይመስላችሁም?  ሌላው እነሱ ባላቸው ወያኔያዊ ተሳትፎ  እቤታቸው ሊያወሩት የሚገባን ዝባዝንኬ እንደ ትልቅ ፕሮግራም በሚዲያ እንዲቀልዱበት  መደረጉ እድሜ ለሰው በላው መንገስታቸው [ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰበራል]ይባል የለ ?አዎ  መንግስትም የሚፈልገው ይኽንን ነው። ህዝቡ ችግሩን፤  ብሶቱን ፤ ረሀብ እርዛቱን እንዳይገልጽ  ላይፍ ስታይል  ይባልና እገሊት የተባለችው የአሜሪካ ዘፋኝ የምትበላው ባናና ነው፣ የምትጠጣውአፕል፣ ልብሷ ሚኒ ነው፣ ጫማዋ ቲዌንቲ ናይን ቁጥር፣ ቤቷ ማንሐተን ነው፣አቧቷ ጄምስ እናቷ አና ትባላለች፡፡ ባለፈው ሰኞ ስፒች አደረገችና  ሎትኦፍ ፒኦፕል ምናምን እያሉ፡አምሮውን በውጭ ሸቀጦች እየበረዙት፤ማንችስተር፡አርሴናል በማለት አጠገቡ የሚሰራውን ግፍ እንዳያይ እንዳያገናዝብ የሀገር ፍቅር  ማለት ምን እንደሆነ እንዳያውቅ ፤በአደንዛዠ ዕጽ አይምሮውን አደንዝዞ ይዞለታል። በመገናኛ ብዙኃን የሚነገር ነገር ከልጅ እስከ ዐዋቂው የሚሰማው በመሆኑ የሀገርን ወግ፣ ባሕል እና ደረጃ መጠበቅ አለበት፡፡ አንዳንዴኮ ጠዋት የሚተላለፍ ፕሮግራም ላይ እንደምን ዋላችሁ» የሚል ሰላምታ ትሰማላችሁ፡፡ እንዴት ነው አንድ ሰው በእንደምን ዋላችሁ? በእንደምን አረፈዳችሁ?፣ በእንደምን አመሻችሁ? እና በእንደምን አደራችሁ መካከል ያለውን ልዩነት ሳያውቅ ጋዜጠኛ ለመሆን የቻለው? መቼም ይህቺ ሀገር መቀባት እንጂ መማር የማይጠቅምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡ ቆይ ቆይ ግን እኔ ብቻ ነኝ የታዘብኩት ? ወይስ እንደኔ  አውቃችሁ ግን የት እንተንፍስ ብላችሁ በሆዳችሁ ይዛችሁት ነው ?ወይንስ ምን አገባን ብላችሁ ትታችሁት ነው ?                                       እስከ ሚቀጥለው ጽሁፌ  ሰላም ሁኑልኝ

Tuesday, 29 January 2013

ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ



ከኢየሩሳሌም አርአያ

ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩ በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤

«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።

ዛሬ እነዚህን ደካማ ጐኖች ተጠቅመው ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚፈልጉ ያውም ደግሞ የእኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ። ይህንን ግልፅ ለማቅድረግ አሁን በቅርብ ጊዜ በመቀሌ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ ስብሰባ አካሄደን ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ነው እንግዲህ ተከታዩ ነገር የተነሳው። ይኽውም፥ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ ከሚስቱ ጋርና ሌሎችም ያሉበት ይህን አሉ፤

«ድርጅታችን ጨርሶ ተዳክሞዋል። እኛ የኢትዮጲያ ሕዝብ ትግል መስራች ሆነን ሳለ ወደኋላ ተገፍትረን በአንፃሩ ሌሎች ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው። ባዛው መጠን ሕዝባችን እየተጎዳ ነው። ስለዚህ አሁን ካጋጠመን አደጋ መውጣት ካለብን ከድርጅቱ -የተወገዱትን ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩትን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የሕዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው።» በማለት ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው።

“ሕዝባችን አስተውል። በዚህ አይነት ዳግመኛ በድርጅታችን ተኃድሶ እንደሚያስፈልገን ነው የተገነዘብነው። በሚቀጥለው የካቲት ወር በሚካሄደው ጉባኤያችን ይህንን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶና አጥርቶ (ውሳኔ አሳልፎ) እንደሚወጣና እነዚህንና መሰሎቻቸው ከሚያራምዱት አቋም ጋር ጠራርጐ እንደሚያስወግድልን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህም እያንዳንዱ እንደከዚህ ቀደሙ የተለመደ አስተዋፅኦ (ሚና) እንደሚያበረክት አንጠራጠርም።

በተጨማሪ ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል።”

ከመቀሌ…