"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 30 January 2013

የእግር ኳሳችንና የኤፍ ኤም ሬዲዮናችንን፡እኔ ነደታዘብኩት........ እናንተስ....እንዳለ ጌታነህ ከኖርዌበመጀመሪያ እንኳን ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት አሸጋገረን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለቴ ነው፤በፌስ ቡክ ላይ አንድ ነገር አነበብኩና  ፈገግ አልኩኝ ምን ይላል መሰላችሁ፤ሰበር ዜናን በረኞቻችን አርገውት የገቡት የካራቴ ጫማ ተመሳሳዩ  ጆሀንስበርግ ላይ እየተቸበቸበ ነው።;
;                ሶስት ጨዋታ አድርገን ሶስቱንም   ጨዋታዎች በሙሉ ተጨዋች  አልጨረስንም ሶስት ተጨዋቾች ለቀይ ካርድ ሰለባ ሁነዋል ሁለቱ የኛ  ግብ ጠባቂዎቻችን ሲሆኑ  አንዱ ግን የቡርኪና ፋሶ ተጨዋች ነው ። እኛ ከዛምቢያ ጋር  በጎዶሎ  ልጅ ጎል ስናስቆጥር ቡርኪና  እኛ ላይ በጎዶሎ ልጅ አራት አገባብን፤ እንግዲህ ለዚነው የካራቴ  ጫማ በስማቸው የተሰየመላቸው።ግን የበረኝነቱ  ልምምዱ ካራቴንም ያካተተ ነበር ? ወይስ የበረኞቹ አሰልጣኝ ካራቲስት ነበር  ? ዋናው ግን መረሳት የሌለበት ገጠመኝ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋችን ሶስት ጨዋታ ተጫውትን በአንዱ አቻ ስንወጣ በሁለቱ ስንሸነፍ ሰባት ጎል ሲቆጠርብን አንድ ብቻ ማስቆጠራችን ፤ለእኛ ጎሉን ያሰቆጠረው ሰባት ቁጥር መሆኑ፤ ሁለት ቀይ ካርድ ስናገኝ ሁለቱንም ቀይ ካርድ ያገኙት በረኞቻችን መሆናቸውና ደጋፊዎች አጠፉ ተብሎ  አምስት ሺ ዶላር መቀጣታችን ነው።    ለጽሁፌ  አርስት የለውም ስለዚ የፈለኩትን   ደስ ያለኝን ሃሳብ አነሳለው አይዟችሁ አላሰለቻችሁም፤

እስኪ ደግም ሸገር ኤፍ ኤምን እንቦጭቅ አዎ ማን ነበር ባለፈው ለጊዜው ስሙን የረሳሁት ጸሀፊ ይቅርታ አስታውሻለው ዳንኤል ክብረት ነበር    ምን አለ  መሰላች ኤፍ ኤሞቻችንን መልሱልን በሚለው ጽሁፉ፤   በአንድ የኤፍ ኤም ራድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም ታክሲ ውስጥ ሆኜ እየሰማሁ ነበር፡፡ «ጋዜጠኛው» ቀብሩ በትናንትናው ዕለት ስለተፈጸመ አርቲስት ተናገረና «rest in peace ብለናል» አለ፡፡ የአፍ ወለምታ ወይንም ልማድ ነው ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አሁንም ስለ ሌላ ስለ ዐረፈ ሰው ተናገረና ያንኑ ደገመው፡፡ ይኼኔ ደነገጥኩ፡፡ ይኼ የኤፍ ኤም ሬዲዮ በአማርኛ ቋንቋ ለሕዝበ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነው፡፡ አሁን «ነፍስ ይማር» የሚለው የአማርኛ ቃል የሚጠፋው ጋዜጠኛ እንዴት ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጉዳዮች ሊያነሣ የሚችለው?ቀጠለ አሁንም ዳነኤል የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው
እንደሚለው የሠርግ ዘፈን እንግሊዝኛ ማወቅ የዕውቀት መለኪያ ነው? ለነገሩ እርሱ ምን ያድርግ «ቢሾፍቱ አውቶቡስ? ብሎ መጻፍ ሲቻል «ቢሾፍቱ ባስ» ብሎ ጽፎ በከተማዋ ውስጥ በኩራት በሚዞርባት ሀገር፣ «ልዩ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ስፔሻል ክትፎ» «ተራ ክትፎ» ማለት ሲቻል «ኖርማል ክትፎ» ተብሎ የጉራጌ ክትፎ እንግሊዛዊ በሚሆንባት ሀገር «ነፍስ ይማር»ን አለማወቅ ነውር ላይሆን ይችላል፡፡ መቼ በዚ አበቃ ዳንኤል «good bye have a nice weekend´ ብለው ተሰናበቱንና ሌሎች ደግሞ መጡ፡፡ ስለ ውጭ ሀገር ዘፋኞች፣ የፊልም ተዋንያን፣ ፊልሞች እና ዘፈኖች እንደሚያወሩን፣ ስለ አንዳንዶቹም ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጡን ነገሩንና ለመሸጋገርያ ብለው የእንግሊዝኛ ዘፈን ጋበዙን፡፡
ይኼኔ ነው ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች የማን ናቸው? እያልኩ መጠየቅ የጀመርኩት፡፡ አንድ ዓይን ያላት በዐፈር አትጫወትም ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ጥርስ የላት በዘነዘና ትነቀስ አማራት ብሎም ይጨምርበታል፡፡ ለራሳችን ኤፍ ኤም ሬዲዮ እና ስኳር እያጠረን ተቸግረናል፡፡ ከነዚሁም ቆርሰን ለፈረንጆቹ ከሰጠናቸው ምን ሊተርፈን ነው? ወይስ እነርሱ ለኛ ብድር እኛ ለእነርሱ ሬዲዮ ልንሰጣቸው ተስማምተናል፡፡   ብሎ መርር አድርጎ  ጽፎ  ነበር ዛሬ እኔ ደግሞ ጊዚዬን መልስሉኝ እላለው ፤ማን አዳምጥ አለህ ? ማን አስገደደህ ? ካላችሁም ዜግነቴ  ብቻ በቂ ነው ኢትዮጵያዊ ሆኜ መፈጠሬም በቂ ነው እላለው።                                              ወደ ተነሳሁበት ሀሳብ ልገስግስ በተለይ ሰይፉ የተባለ ፎጋሪ ከነ ልጆቹ የሚሞላፈጡበት  ታዲያስ አዲስ የተባለው ፕሮግራም በቀን  ካለው የሁለት ሰዓት የአየር ላይ ዝግጅት  ምን አለፋችሁ በፐርሰንት ብናስቀምጠው 80 ፐርሰንት ማስታወቂያ፤ 10 ፐርሰንት ሰዓት ዕወጃ፤7 ፐርሰንት ሙዚቃና፦3 ፐርሰንት ዋናው ፕሮግራም ነው ።ዋናው ስል እነሱ ማይክ ይዘው እየገለፈጡ በሰው ሃዘን  የሚቀልዱበትን ማለቴ ነው። ሙዚቃውም ቢሆን የሚቀርቡት  ለአዘጋጆቹ ዳጎስ ያለ ጉቦ  የሰጡ ናቸው።ግለሰቦች ለሚያዘጋጁት ኮንሰርት  በተለይ አዲካ   ከሆነ  ጭቅጭቅ በሉት  የሆነ ነገር ጆሮሯችሁ እስኪቃጠል ትነዘነዛላችሁ።እንግዲህ እዩት የመዝናኛ ፕሮግራም ተበሎ የተያዘለትን ሰዓት ባልባሌ ማስታወቂያ  ያልቃል።  [ላዳማጩ ማለቴ ነው]እነሱማ ገንዘባቸውን ከማስታወቂያ ያገኛሉ  ፡ዝም ብለው  ታዲያስ አዲስ ከማለት ማስታወቂያ አዲስ ቢባልስ ወይም የመዝናኛ ፕሮግራም ከማለት ይልቅ የእከክልኝ ልከክልህ ፕሮግራም ቢባል፤ ጥሩ አይመስላችሁም?  ሌላው እነሱ ባላቸው ወያኔያዊ ተሳትፎ  እቤታቸው ሊያወሩት የሚገባን ዝባዝንኬ እንደ ትልቅ ፕሮግራም በሚዲያ እንዲቀልዱበት  መደረጉ እድሜ ለሰው በላው መንገስታቸው [ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰበራል]ይባል የለ ?አዎ  መንግስትም የሚፈልገው ይኽንን ነው። ህዝቡ ችግሩን፤  ብሶቱን ፤ ረሀብ እርዛቱን እንዳይገልጽ  ላይፍ ስታይል  ይባልና እገሊት የተባለችው የአሜሪካ ዘፋኝ የምትበላው ባናና ነው፣ የምትጠጣውአፕል፣ ልብሷ ሚኒ ነው፣ ጫማዋ ቲዌንቲ ናይን ቁጥር፣ ቤቷ ማንሐተን ነው፣አቧቷ ጄምስ እናቷ አና ትባላለች፡፡ ባለፈው ሰኞ ስፒች አደረገችና  ሎትኦፍ ፒኦፕል ምናምን እያሉ፡አምሮውን በውጭ ሸቀጦች እየበረዙት፤ማንችስተር፡አርሴናል በማለት አጠገቡ የሚሰራውን ግፍ እንዳያይ እንዳያገናዝብ የሀገር ፍቅር  ማለት ምን እንደሆነ እንዳያውቅ ፤በአደንዛዠ ዕጽ አይምሮውን አደንዝዞ ይዞለታል። በመገናኛ ብዙኃን የሚነገር ነገር ከልጅ እስከ ዐዋቂው የሚሰማው በመሆኑ የሀገርን ወግ፣ ባሕል እና ደረጃ መጠበቅ አለበት፡፡ አንዳንዴኮ ጠዋት የሚተላለፍ ፕሮግራም ላይ እንደምን ዋላችሁ» የሚል ሰላምታ ትሰማላችሁ፡፡ እንዴት ነው አንድ ሰው በእንደምን ዋላችሁ? በእንደምን አረፈዳችሁ?፣ በእንደምን አመሻችሁ? እና በእንደምን አደራችሁ መካከል ያለውን ልዩነት ሳያውቅ ጋዜጠኛ ለመሆን የቻለው? መቼም ይህቺ ሀገር መቀባት እንጂ መማር የማይጠቅምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡ ቆይ ቆይ ግን እኔ ብቻ ነኝ የታዘብኩት ? ወይስ እንደኔ  አውቃችሁ ግን የት እንተንፍስ ብላችሁ በሆዳችሁ ይዛችሁት ነው ?ወይንስ ምን አገባን ብላችሁ ትታችሁት ነው ?                                       እስከ ሚቀጥለው ጽሁፌ  ሰላም ሁኑልኝ

1 comment:

  1. ጥሩ ቁም ነገር አዘል ሁሉም እየተዝናና ሊያስተውል የሚገባው ነጥብ ነው የነገርከን፥፥

    ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ፥፥

    ReplyDelete