"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 29 December 2012

የሳልሃዲን እርምጃዎች …[ቃለ ምልልስ]


* ሳላ አሁን የት ነው ያለኸው?
በቤልጅየም ዋና ከተማ ብራሰልስ፡፡

* ብራሰልስ ምን ትሠራለህ?
የግብፅ ሊግ መቋረጡን ተከትሎ ክለቤ ዋዲ ደግላ ከእንቅስቃሴ እንዳይርቅ ለዝግጅት ግጥሚያዎች ወደ አውሮፓ አቅንቷል፡፡ የእኔም ጉዞ ከዚያ ጋር በተያያዘ ነው፡፡

* የዋዲ ደግላ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ወይም አስተዳዳሪ ማነው?
የክለቡ ባለቤት ቤልጅየም ሀገር የሚኖር ማጌድ ሳሚ የተባለ ግብፃዊ ባለፀጋ ነው፡፡ ሳሚ በግብፅ ከተሳካላቸው የንግድ ሰዎች አንዱ ሲሆን ዋዲ ደግላ የተባለ ግዙፍ ኩባንያ ካይሮ ውስጥ አለው፡፡ ይህ ኩባንያ በሪል ስቴት፣ በመንገድ ግንባታ፣ በውጪ ንግድ እና ገዘፍ ባሉ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማራ ነው፡፡ እኔ የምጫወትበት ዋዲ ደግላም የሚተዳደረው በዚሁ ኩባንያ ሥር ነው፡፡ ዋዲ ደግላ ልክ እንደ ኢትዮጵያው ሚድሮክ ቁጠረው፤ በሥሩ በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን አቅፎ ይዟል፡፡

* የዋዲ ደግላ እና የቤልጅየሙ ሊርስ አንድነት ምንድነው?
ማጌድ ሳሚ ከአንድ ዓመት በፊት ኪሳራ ውስጥ የተዘፈቀው ሊርስን ዕዳውን ከፍሎ ገዝቶታል፡፡ ስለዚህ እኔ የምጫወትበት ክለብ እና ሊርስ ንብረትነታቸው የአንድ ሰው ነው፡፡ በቅርቡ በቤልጅየም ሶስተኛ ዲቪዚዮን የሚወዳደረው ቱርንሃውት የተባለው ክለብም የግብፃዊው ንብረት ሆኗል፡፡

* ወደ ብራሰልስ ከመጣህ ስንት ጊዜ ሆነህ?
ቡድኑን የተቀላቀልኩት አስር ቀን ዘግይቼ ነው፡፡ የቀለበት ፕሮግራም ሀገር ቤት ስለነበረኝ ቡድኑ ወደ ብራሰልስ ከመንቀሳቀሱ ከቀናት በፊት ወደ አዲስ አበባ ሄድኩኝ፡፡ ከዚያም በታህሣሥ የመጀመሪያ ሳምንት ወደ ቤልጅየም መጣሁ፡፡

* በብራሰልስ ልምምድ ብቻ ነው የምታደርጉት ወይስ ግጥሚያ አግኝታችኋል?
ሁለቱንም፡፡ እኔ ከመጣሁ እንኳን በሁለት ጨዋታዎች ተሰልፌያለሁ፡፡ አንዱን አርባ አምስት ደቂቃ ስጫወት በሌላኛው ለአስራ አምስት ደቂቃ ተሰልፌያለሁ፡፡ የምንገጥመው በቤልጅየም ፕሮ ሊግ (አንደኛ ዲቪዚዮን) የሚገኙ ቡድኖች ሁለተኛ ስብስባቸውን ነው፡፡ በተጨማሪም ከሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲቪዚዮን ቡድኖች ጋር ተጫውተናል፡፡

* ሁኔታው ለምን ያህል ጊዜ ይቀጥላል?
የግብፅ ሊግ እስኪጀመር ነው፡፡ ስንመጣ የአንድ ወር ተኩል ፕሮግራም ነበር የተያዘው፡፡ አሁን ግን ዕቅዱ ተለውጦ ቤልጅየም የምንቀርበት ዕድል እየተመቻቸ ነው፡፡

* የግብፅ ሊግ ዘንድሮ አይጀምርም ማለት ነው?
የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ይጀመራል የሚል ግምት አለ፡፡

* ቤልጅየም መቅረት ሲባል እንዴት ነው?
ሊርስ እና የሶስተኛ ዲቪዚዮኑ ቱርናውት የሚተዳደሩት በዋዲ ደግላው ባለቤት ነው፡፡ በዋዲ ደግላ አሰልጣኝ ጥቆማ ስድስት ልጆች ወደ ሊርስ እንዲዛወሩ ተደርጓል፡፡ የቀሩት ደግሞ ለቱርንሃውት እንዲጫወቱ የሥራ ፈቃድ እየተመቻቸላቸው ነው፡፡ (በነገራችን ላይ የሊርስ አሰልጣኝ የቀድሞ የግብፅ ዕውቅ ተጫዋች ሃኒ ራምዚ ነው)

* አንተ ከስድስቱ ውስጥ የለህም?
የለሁበትም፡፡ ሲጀመር እዚህ የመጣነው ለአንድ ወር ተኩል ነበር፡፡ እኔ ደግሞ በብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት እና በአፍሪካ ዋንጫ የተነሳ ቢያንስ ለአንድ ወር ከቡድኑ እርቃለሁ፡፡ በዚህም የተነሳ ከስድስቱ ውስጥ እንዳላካተተኝ አሰልጣኙ ነግሮኛል፡፡ እኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ስለምሄድ አንድ አጥቂ እንደሚፈልግም አስታውቆኛል፡፡

* ምክንያቱ ይህ ብቻ ነው?
ዋናው ምክንያት ይህ ቢሆንም በምሰለፍበት ቦታ ከአሰልጣኙ ጋር አልተግባባንም፡፡ እርሱ ተደራቢ አጥቂ ሆኜ እንድጫወት ይፈልጋል፡፡ እኔ ደግሞ በዚያ ቦታ ጥሩ አይደለሁም፡፡ ወደ መሐል ተስቤ ስጫወት ጎል የማግባት ብቃቴ ይቀንሳል፡፡ ለስልጠናው ዓለም አዲስ እንደመሆኑ ልምዱም አናሳ ነው፡፡ በዚያ ላይ ሲያሰራ ንግግሩ ይበዛል፡፡ በአጠቃላይ የአሰልጣኝ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ዋዲ ደግላ አልተመቸኝም፡፡ ከቀድሞው አሰልጣኝ ጋር ጥሩ ተግባብተን ነበር፡፡ ቤልጅየማዊው ተሰናብቶ ግብፃዊው ከመጣ በኋላ ግን ነገሮች እንደበፊቱ አልሆኑም፡፡

* መጪው ጊዜ ምን ሊሆን ይችላል?
ክለቡ ለሶስተኛ ዲቪዚዮኑ ቱርንሃውት እንድጫወት ጠይቆኛል፡፡ የእኔ ፍላጎት ደግሞ ሊርስ ነው፡፡ በዚህ መሐል የአፍሪካ ዋንጫ አለ፡፡ መጪውን ጊዜ ከአፍሪካ ዋንጫ በኋላ አብረን ብናይ አይሻልም?

* እስከዚያ ክለቡ ይታገስሃል?
ገና የአንድ ዓመት ተኩል ውል ይቀረኛል፡፡ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሳልሄድ ምላሼን እንዳሳውቃቸው ነግረውኛል፡፡ እኔም ሶስተኛ ዲቪዚዮን ወርጄ እንደማልጫወት አሳውቄያቸዋለሁ፡፡

* ሌሎች ክለቦች የዝውውር ጥያቄ አላቀረቡልህም?
የሱዳን ክለቦች ገፍተው መጥተዋል፡፡ በተለይ ሜሪክ እና አል አህሊ ሻንዲ አሁንም ድረስ እየጠየቁኝ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ከአፍሪካ ዋንጫ መልስ የምወስነው ይሆናል፡፡

* የእግርህ ጤንነት አንዴት ነው?
በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡

* ጉልበትህን በደንብ ተሸሎሃል?
አዎን፡፡

* አዲስ አበባ ላይ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ስትጫወት የተጎዳኸውሳ?
እርሱ በግራ እግሬ እና በመቀመጫዬ መጋጠሚያ ላይ የደረሰብኝ የጡንቻ መሳሳብ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት እዚያ አካባቢ የሚሰማኝ ነገር የለም፡፡

* በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከጊኒ ጋር ኮናክሪ ላይ የተጎዳኸው ጉልበትህን ነበር?
የቀኝ ጉልበቴ ላይ ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነት ጉዳት በእግር ኳስ ዘመኔ አይቼ አላውቅም፡፡ ሜዳው ጭቃ ነበር፡፡ ከኋላ ሲጠልፉኝ በጉልበቴ ጭቃው ላይ ተሰካሁኝ፡፡ የተጎዳው ከኋላ የጉልበቴን ሎሚ አቅፎ የሚይዘው አንደኛው ጅማት (ሊጋሜንት) ነው፡፡ ከጉልበት ጀርባ ሁለት ጅማቶች አሉ፡፡ ጭቃው ላይ በሙሉ ኃይል ስወድቅ አንዱ ጅማት ተበጠሰ፡፡ እርሱን ለማስታመም ስድስት ወር ፈጅቶብኛል፡፡

* ጉዳቱ የዋዲ ደግላ ቆይታህ ላይ ተፅዕኖ አላሰረፍብህም?
ለዋዲ ደግላ ፈርሜ አዲስ አበባን እንደለቀኩኝ ካይሮ በሚገኘው የክለቡ ማዕከል ቀለል ያሉ ልምምዶችን እያደረኩ ነበር፡፡ ከዚያም ወደ ጨዋታ ሳልገባ ጊኒን ለመግጠም ወደ አዲስ አበባ መጣሁ፤ ጉልበቴንም ተጎዳሁ፡፡ ጉዳቴን አስታምሜ ስመለስ የግብፅ ሊግ ተቋረጠ፡፡ ይህን ተከትሎ ብቃቴን በግብፅ ሜዳዎች ለማሳየት የነበረኝ ህልም ተጨናግፏል፡፡ ሆኖም በጉዳት ወደ ካይሮ ስመለስ ክለቡ ልዩ እንክብካቤ አድርጎልኛል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡

* ለምን ያህል ጊዜ ነበር ከሜዳ የራቅከው?
ስድስት ወር፡፡ ከሶስት ወር በኋላ አገግሜ ወደ ሜዳ ስመለስ እንደገና ተጎዳሁ፡፡ ጉዳቱ የደረሰብኝ ሳይሻለኝ ቶሎ ወደ ጨዋታ በመግባቴ ነበር፡፡ ድጋሚ ከተጎዳሁ በኋላ ለሶስት ወራት ከሜዳ ርቄያለሁ፡፡

* ጉልበትህ ላይ ቀዶ ጥገና አድርገሃል፡፡ ወጪውን ማነው የሸፈነው?
ለሕክምና ከኪሴ ሰባት ሺህ ዶላር አውጥቻለሁ፡፡ ቀሪውን የቻለው ክለቡ ነበር፡፡ የክለቡ ድርሻ በዛ ይላል፡፡

* በአፍሪካ ዋንጫ አዲስ የዝውውር ጥያቄ ቢመጣስ?
ዋዲ ደግላ እና ፈላጊው ክለብ ይነጋገሩና የእኔ ፍላጎት ተጠብቆ ዝውውሩ ይፈፀማል፡፡ የእዚህ ሀገር ዝውውር የተደበቀ ነገር የለውም፡፡ ሁሉም ነገር ፊት ለፊት በሚደረግ ድርድር የሚፈፀም ነው፡፡ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ለዋዲ ደግላ ስፈርም በውላችን ላይ የተጠቀሰ ነገር አለ፤ የተሻለ ክፍያ የሚሰጠኝ ክለብ ከመጣ ሊለቁኝ፡፡ እንደውም ለካይሮው ክለብ በዋናነት የፈረምኩት ወደ አውሮፓ መሸጋገሪያ ይሆነኛል በሚል ነው፡፡ ይህም ጉዳይ በውላችን ላይ በግልፅ ተቀምጧል፡፡

* ከቡድኑ አባላት ጋር በምን ትግባባለህ?
ዓረቢኛ እሞክራለሁ፡፡

Friday 28 December 2012

The unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dying…

Gen Samora Yenus is dying…
The unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dyingThe Horn Times Newsletter, 28 December 2012
by Getahune Bekele

A poor peasant and a primary school dropout, who was described by senior political commentator as cold blooded murderer with thinking and reasoning capacity of a dinosaur, Gen Samora is dying…
According to a sensitive document leaked to the Horn Times from Bella military referral hospital in Addis Ababa, the frail TPLF army chief-of-staff and top November criminal, the dastardly Gen Samora Yenus Mohamedfereja, has less than a year to live.
And if he dies before being arrested and tried, Samora Yenus will be the fourth high profile TPLF war criminal to escape justice after the late fuehrer Meles Zenawi, former intelligence chief Kinfe G.medhin and after former army commander the late Gen Hayelom Araya, who was killed during gun fight over a prostitute in one of Addis Ababa’s brothels.
Diagnosed with HIV AIDS in 2006 and declared a habitual defaulter for not taking his medication regularly, the illiterate and lowbrow Samora has been receiving treatment consisted of strengthening the body’s natural defense, killing bacteria and battling infection at Essen university hospital in Germany.
However, despite the impoverished Ethiopia footing his massive medical bill including the purchase of an expensive drug called zidovudine, the bawling warlord has developed new strain known as extensively drug-resistant (XDR) tuberculosis, which resisted all 8 second line drugs.
The intercepted document further revealed that the murderous warlord is suffering from other scourges as well; diabetes mellitus and hypertension, which complicated the costly multi-system treatments. And currently, he is not responding well to available medications both at home and abroad.

ጠቃሚ እና አስፈላጊ ሁሉም ሊተገብረው የሚገባ ምክር

Ashenafimekonen
ቊርባን እንዳይነጥብ ቀሳውስት እንደሚጠነቀቁ ምክርም እንዳያልፍህ ጆሮህ ነቅቶ ሊሰማ፣ ብዕርህ ሰልቶ ሊመዘግብ ይገባዋል፡፡ ምክር ባለበት የጠራ ውሳኔ ይኖራል፣ ድልም ይገኛል፡፡ ምክር ገንዘብ ሊገዛው የማይችል ትልቅ ሀብት ነው፡፡ ገንዘብ የሰጠህ ባለጠጋ ከኪሱ መዝዞ ነው፡፡ ምክር የሚሰጥህ አዋቂ ግን ከነፍሱ አውጥቶ ነው፡፡ ምክር የነፍስ ስጦታ መሆኑን አስተውል፣ ተጠንቅቀህም ያዘው፡፡ በትክክል የሚታዘዝ በትክክል የሰማ ነው፡፡ በደንብ ለመታዘዝ በደንብ መስማት እንደሚያስፈልግ እወቅ፡፡

ወዳጄ ሆይ!
የተቋረጠውን ጥቅምህን ለማስቀጠል ብለህ ይቅርታ መጠየቅ አይገባህም፡፡ የምትፈልገውን ከወዳጅህ ከመጠየቅህ በፊት የወሰድክበትን ሰላም በይቅርታ መልስለት፡፡ ይቅርታ ሳይጠይቁ ንብረትን መጠየቅ አንተን አልፈልግህም ንብረትህን ግን እፈልጋለሁ እንደ ማለት ነው፡፡ ይቅርታ የበረከት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ ያ ሰው ይቅር ካለህ ካሰብከው በላይ ይሆንልሃል፡፡ ቢሆንም ይቅርታን የጥቅም ማግኛ መንገድ አታድርገው፡፡ ካጣኸው ንብረት ያጣኸው ወንድምነት የበለጠ ኪሣራ መሆኑን እባክህ አስተውል፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ይቅር ያልከውን ስህተት መልሰህ አትናገረው፡፡ ይህ ግርሻት ያመጣል፡፡ ከዋናው በሽታ በድንገት የሚጥል ግርሻት ነው፡፡ ይቅር ያሉትን ስህተት ማሰላሰልም ትልቅ ጉዳት ነው፡፡ ዛሬ የተሳሳተውን ወገንህን ካለፈው ስህተቱ ተነሥተህ አትውቀሰው፡፡ እርሱ ከስህተቱ እንዳልተመለሰ ሁሉ አንተም ከቂምህ አልተመለስክም ማለት ነው፡፡ የሰጡትን ስጦታ መልሶ መቀበል ውርደት ነው፡፡ ይቅርታም ስጦታ ነውና ከሰጠኸው በኋላ መንሣት ትልቅ ሐፍረት ነው፡፡ ውሻ የተነቀፈው የተፋውን በመላሱ ነው፡፡ የተፉትን ቂም መላስም ያስነቅፋል፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ረጅም ሰዓት ዝም ብለህ ስትናገር ንግግርህ ኃይል የተሞላ ይሆናልና ከዝምታ በኋላ ስትናገር አንደበትህን በስመ ሥላሴ አሟሸው፡፡ ዝምተኛ ሰው ሁሉ አስተዋይ ነው አትበል፡፡ የሚናገረው የሌለውም ዝም እንደሚል እወቅ፡፡ “የእንጦጦ መምህር ቢናገር ባመት፣ ያውም እሬት” እንዲሉ ዝም ብሎ የኖረ ሰውም ሲናገር ንግግሩ ከባድ ነው፡፡ ንግግር ልምምድ መሆኑን አስተውል፡፡ አንድ ጊዜ ለመናገር ሁለት ጊዜ ማሰብ ከፀፀት እንደሚጠብቅ ተረዳ፡፡

ወዳጄ ሆይ!
አፍ ቢደፍኑት ይሸታል፣ ችግርም ይዘው ቢያሰላስሉት ይጐዳል፡፡ ለሁነኛ ሰው ማማከር ግን ይቀላል፡፡ ችግርህ ከሴት ጋር የተያያዘ ከሆነ ለሴት አማክረው፡፡ ችግርህ ከጭንቀት ጋር የተያያዘ ከሆነ ከእናቶች ጋር ተማከረው፡፡ ችግርህ ከኃጢአት ጋር የተያያዘ ከሆነ ከሃይማኖት አገልጋይ ጋር ተማከረው፡፡ ችግርህ የማይነገር መስሎ ከተሰማህ ከእግዚአብሔር ጋር ተማከረው፡፡ ከመጣው ችግር በላይ ዝምታ እንደሚጎዳ እወቅ፡፡ ደግሞም፡- “ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው” የተባለውን አትርሳ፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ሰው ቆሞ የሚጠብቅህ ሐውልት አይደለም፡፡ ሐውልት እንኳ ዘመን ሲረዝም ወድቆ ይሰበራል፡፡ ሰው ጠዋት ለማታ የማታገኘው ሕልም እልም ነው፡፡ ለመኖር ሲደላደል የሞት ጥሪ የሚደርስበት፣ በምድር አለ ስትለው በሰማይ የሚውል፣ ካመለጠህ የማታገኘው ነውና ፍቅርህን ለመግለጥ ሰዓቱ አሁን መሆኑን አስተውል፡፡ ሰው ለቀጠሮ የማይመች ፍጡር መሆኑን እወቅ፡፡ ትልቁ የፍቅር መግለጫም ክርስቶስን መስጠት መሆኑን አስተውል፡፡ ሰውን ለማፍቀር ጊዜው አሁን፣ ለመርዳትም ቀኑ ዛሬ፣ ይቅር ለማለትም ሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ ዕድሉ ይህች ጀምበር፣ አብሮ ለመኖርም ከአሁን የተሻለ ምቹ ዘመን የለም፡፡ የተሰጠን ዕድሜም እንኳን ለጠብ ለፍቅርም እንደማይበቃ አስተውል፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ሰውን ከማሳቅ ሰውን ማስደሰት ይበልጣል፡፡ ሰውን የምታስቀው እውነትና ሐሰትን ቦታ በማለዋወጥ ነው፣ ወይም ውሸትን በማቆንጀት ነው፡፡ ሰውን የምታስደስተው ግን በቁምነገርህ ነው፡፡ ፌዝ የአንደበት፣ ቊምነገር የተግባር ጉዳይ መሆኑን እወቅ፡፡ ፌዘኛ የሚያረሳሳ፣ ቁምነገረኛ ግን የሚፈውስ መሆኑን ተረዳ፡፡

ወዳጄ ሆይ!
የምስክር ወረቀት ያላቸው አዋቂዎች ዕውቀታቸውን ብዙ ጊዜ የሚወስዱት ያልተማሩ ከሚባሉት መሆኑን እወቅ፡፡ ኑሮ የተግባር ትምህርት ቤት ነውና በዕድሜ ከበረቱት ጠይቅ፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ከወጣት ሞት ይልቅ የሽማግሌ መታጣት አሳሳቢ ነው፡፡ ሽምግልና የዕድሜ ብቻ ሳይሆን የጸጋ ነው፡፡ በዕድሜ የሸመገሉ ሁሉ ጠቢባን አይደሉም እንደ ተባለ ጸጋ የለበሱ ሽማግሌዎችን እንዲሰጠን መጸለይ ያስፈልጋል፡፡ የአንድ ማኅበረሰብ ቀጣይነቱ የሚረጋገጠው የሚሰማቸው አባቶች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ንግግርህ ዕውቀት ብቻ ሆኖ እንዳያሰለች፣ የምትናገረው ፍቅር የሌለው እውነት ሆኖ እንዳይሰብር፣ “ጌታ ሆይ በንግግሬ አንተ ተናገርበት፣ በዕውቀቴ ጥበብ ጨምርበት” ብለህ ጸልይ፡፡ እግዚአብሔር የቀደሰው አንደበት ቡሩክ ምንጭ ነውና፡፡





ምክር ለሰሚው


ወዳጄ ሆይ!
እግዚአብሔር ለልብ ይናገራል፡፡ ከግርግር፣ ከትርምስ ወጣ ብለህ በጽሞና ስትቀመጥ የእግዚአብሔርን ድምፅ ትሰማለህ፡፡ እግዚአብሔርን የምትሰማ ነፍስ ከመከራ ስጋት ታርፋለችና እርሱን ስማ፡፡ እግዚአብሔርን በጆሮህ ብቻ ሳይሆን በዕዝነ ልቡናህም አድምጠው፡፡

ወዳጄ ሆይ!
ከራስህ ጋር ሰላም ሆነህ ሰዎች ቢጠሉህ አያስደነግጥም፣ ከራስህ ጋር ተጣልተህ ሰዎች ቢወዱህ ግን አስደንጋጭ መሆኑን እወቅ፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚከዱኝ እውነተኛ ስለሆንኩ፣ ሐቁን ስለምናገር ነው ብለህም ተማምነህ አትቀመጥ፡፡ ራስህን መርምር፣ ምክርንም ተቀበል፡፡

ወዳጄ ሆይ!
በሳቅ ብቻ ይህችን ዓለም ለመርሳት አትሞክር፣ በመደነቅ ብቻ ያለ ሥራ አትቀመጥ፡፡ ዕረፍት ያለበትን የእግዚአብሔር ጸጋ ፈልግ፡፡

ወዳጄ ሆይ!
የምትወደውን ሰው ድምፅ በስልክ እየሰማህ ሞቷል እንደማትል፣ ድምፅ የህልውና መገለጫ እንደሆነ ሁሉ የማይታየው እግዚአብሔርም ህልውናው በመናገሩ እንደሚገልጥ ዕወቅ፡፡

Thursday 27 December 2012

ጂጂና ቴዲ እንደ ቦብ ማርሊ እንደ ፌላ ኩቲ




(ክንፉ አሰፋ)

ጃማይካዊውን የጥበብ ሰው ጋሪሰን ሃውክን በመንተራስ አርቲስት ጂጂ እና ቴዲ አፍሮ ሰሞኑን የለቀቁት '

ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'´ ነጠላ ዜማ በብዙዎች አድናቆትን እየተቻረይገኛል።ብዙዎችንም አነቀቅቷል። ሙዚቃው የተለየ ነው፣ የሚያበረታታ እና የሚያነቃቃም ነው።



'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'! “
ብዙውን ግዜ በጦር ጀብዱ የፈጸመን ወይንም ድል ያደረገን ሰው ጅግና ብለን እንጠራዋለን።ጀግንነትን በዚህ መስፈርት ብቻ ከለካነው -ይህ ቀላሉ ጀግንነት ሊሆን ይችላል። ከባዱ እናእውነተኛው ጀግንነት ግን ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን ማሸነፍ መቻል ነው።
ምንም አይነት ጅብዱ ቢፈጽም ራእይ ግን የሌለው ሰው ጀግና ሊሆን አይችልም። ህይወት ካለ ተስፋ አለ። ተስፋ ካለ ህልም አለ። ህልም ካለ ራዕይ አለ። ራእይ ያለው ሰው ነው ጀግና። 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!የኢትዮጵያ አርቲስቶች በተለያዩ ወቅቶች ከፍቅር ወጣ ያሉ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ሲጫወቱ አስተውለናል። በአብዮት ዘመን፣ በጦርነት ዘመን፣ በድል ዘመን፣ ወዘተ ... አብዛኞቹ ዘፈኖችም ሆ ኑቀረርቶዎች ታዲያ ፈረንጆቹ

ኢንስፓሬሽናል እንደሚሉት መንፈስን የሚያነቃቁና የጀግነነት ሞራልን ከፍ የሚያደርጉ አልነበሩም።



አንቱ የሚባሉ የሃገራችን አርቲስቶች ካቀነቀኗቸው የፍቅር ዜማዎች አንዳንዶቹ የሚደንቁናቸው።
“ቆዳዬ ተገፎ፣ ይሁንልሽ ጫማ፣
ስጋየም ይደገም፣ ላንቺ ከተስማማ..”
“ፍየል ቅጠል እንጂ፣ አትበላም እንጉዳይ፣
በጥርሷ ሰላሳ፣ ባይኗ መቶ ገዳይ...”
“አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ እስቲ ቁጥር ጥሩ፣
እኔ ልጣራ ነው፣ እናንተ ሞክሩ የሚሉ ስንኞችን እናያለን::”
አርቲስቶቹ ከፍቅር ወጣ ሲሉ ደግሞ፣
“ይለያል ዘንደሮ...ይለያል!”
“አባረህ በለው... ፍለጠው ቁረጠው..”
“አያ ሆሆ ማታነው ድሌ ..”
“ደም በደም ይሁን መረማመጃው!”.ወዘተ የመሳሰሉትን ስራዎቻቸውን መጥቀስ ይቻላል።

አሳዛኝ ሰበር ዜና ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ መስጂድ በር ላይ በሳንጃ ታርደው ተገኙ።

    

አሳዛኝ ሰበር ዜና
ሳኡድ አረቢያ ሪያድ ከተማ ዉስጥ በተለምዶ መንፋሃ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ሻራ እሽሪን መስጂድ በር ላይ ሁለት ኢትዮጵያውያንበሳንጃ ታርደው ተገኙ። ሲሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮት ገለጡ::
ኢትዮጵያውያን በሪያድ ከተማ በብዛት ከሚኖሩባቸው አከባቢዎች አንዱ መንፍሃ ተብሎ የሚጠራው አከባቢ ይጠቀሳል::
ይህ ቦታ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ አስከፊውን የባህር ጉዞ አልፈው ሳኡድ አረብያን ለመርገጥ የታደሉ ወጣቶች የሚስተናገዱበት እንደመሆኑ መጠን በወገኖቻችን መካከል አልፎ አልፎ በሚፈጠረው የብሄር ግጭት በሰው ሃገር የሚሰማው ዘግናኝ ዜና የሃገራችንን በጎ ጘጽታ ለውጦታል::
በተለይ ቀደም ብሎ ያንድ ኢትዮጵያዊት ሬሳ በሳንጃ ተዘልዝሎ በሻንጣ ተጠቅልሎ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ዉስጥ ተጥሎ መገኘቱ በአከባቢው ነዋሪ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮዋል ሲል የሚኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ከሪያድ ተናግረዋል::
በሪያድ እና አከባቢው እትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበርን ምኒሊክ ሳልሳዊ ያመስግናቹሃል::
ኢትዮጵያውያንን
በዛሬው እለት በዚህ ዙሪያ የወያኔ ዲፕሎማቶች ስብሰባ ጠርተዋል::

Wednesday 26 December 2012

ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል


“[ሙስና] የስርዓቱ አደጋ ነው” ርምጃ ግን የለም!!
corruption fight
ሙስና በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኢህአዴግ አይክድም። ኢህአዴግ ባለስልጣኖቹ በሙስና ስለመዘፈቃቸው ማመኑን የገለጸው “የመንግስት ሌቦች አስቸገሩኝ” በሚል ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሙስና የተለከፉ ዋጋቸውን ያገኛሉ” ሲሉ ስልጣን በያዙ ማግስት መዛታቸውን የሚያስታውሱ በስተመጨረሻ “ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ ነው።
“ትልቅ ጫካ ሰርታችሁ የኛንም የናንተንም ሌቦች መደበቅ በመቻላችሁ ሁሉንም መመንጠር ስላልቻልን እየተተራመስን ነው” በማለት ጣታቸውን ወደ ነጋዴው ህብረተሰብ በመቀሰር ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአገሪቱ ያለውን ሙስና አስከፊነት በገለጹበት መድረክ “ስልጣን የመክበሪያ ብቸኛው መንገድ በሆነበት አገር ዘላቂ ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው። በኪራይ ሰብሳቢነት እንደ መንግስትም፣ እንደ ባለሃብትም መቀጠል አንችልም። እንደ ሶማሌ ነው የምንሆነው። እንተራመሳለን። በድጎማ እየኖርን ሙስናው ከከፋ አገር የሌለው ባይተዋር እንሆናለን” ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነትና በኢህአዴግ ስሌት ሙስናው የሚያስከትለውን የመጨረሻ ጣጣ አመላክተው ነበር።

የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን (ማሕሌት ፋንታሁን)



two faces  Leave a Comment
የዘወትር የድረገጻችን ተሳታፊ የሆኑ ይህንን ጽሁፍ እንድናነበውና እንድናትመው በላኩልን መሠረት እነሆ ለአንባቢዎቻችን አቅርበነዋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ለጸሐፊዋ ማሕሌት ፋንታሁን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን

አነጋገራችንን፣ አካሄዳችንን፣ አበላላችንን፣ አስተያየታችንን ባጠቃላይ የምናደርገውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ቀጥጠኛ አስተዋፅኦ ካላቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው በኪሳችን ያለው ገንዘብ ነው፡፡ ገንዘብ ከምናገኝባቸው አንዱ መንገድ ደግሞ ተቀጥሮ መሥራትና ወር ሲያልቅ የሠራንበትን ክፍያ/ደሞዝ ማግኘት ይገኝበታል፡፡ አብዛኛው በከተማ አካባቢ የምንኖር በዚህ መስመር ውስጥ እንገኛለን፡፡
ደሞዝ ተቀብሎ ቀጣዩን የደሞዝ ቀን እንደ ምፅአት ቀን በጉጉት የማይጠብቅ ካለ ይህ ሰው ከደሞዙ ውጪ ሌላ ተጨማሪ ገቢ አለው ወይም አንድ ቀልድ ላይ እንደሰማሁት በአስማት ነው የሚኖረው ማለት ነው፡፡ ደሞዛችን እዛው እንዳለ ወይም በተወሰነ ጭማሪ… ብቻ ኑሮ ግን በብዙ እጥፍ ጨምሮ መኖር መቻላችን እውነትም አስማተኛ ያስብላል፡፡ እንደየደረጃው ይለያይ ይሆናል እንጂ አብዛኛው ደሞዝተኛ ደሞዝ ከተቀበለ በኋላ ካሉት የተወሰኑ ቀናት ውጪ ለመጪው የደሞዝ ቀን ስንት ቀን እንደቀረው በመቁጠር፤ ቀሪውን ጊዜ በብድር እንዴት እንደሚያሳልፍ በማውጠንጠን፤ የሰቀቀን ኑሮ መኖሩን የተለማመድነው ይመስላል፡፡
የደሞዝ ሰሞንና የጠብሽ ሰሞን እንደየሰው ይለያያል፡፡ በአብዛኛው ደሞዝ ከተቀበሉ ከ10-15ኛው ቀን በኋላ ሰሞነ ጠብሽ ይገባል፡፡ ደሞዝ የተቀበሉ እለትም ደሞዟ ብድር ብቻ ከፍላ የዕለቱለት ጠብሽ የሚጀምርበት አጋጣሚም አለ፡፡ የበዓል ወቅቶች እና ጳጉሜ ወር “የጠብሽ” ወቅትን ከሚፋጥኑ/ከሚያረዝሙ ምክንያቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጳጉሜ ወር ግን ለምን ደሞዝ እንደሌላት ሁሌም ይገርመኛል፡፡ በዛ ላይ የአዲስ ዓመት ወጪ ተጨምሮበት አስቡት፡፡
የደሞዝ ሰሞን 1
የደሞዝ ሰሞንን አስታከው የሚመጡ ወጪዎች ብዛታቸው አይጣል ነው፡፡ በመሥሪያ ቤት ለተለያዩ ጉዳዮች የሚሰበሰቡ መዋጮዎች፣ በየመሥሪያ ቤቱ እና ካፌው እየዞሩ እርዳታ የሚጠይቁ እና  የመንገድ ላይ ለማኞች የሚበዙት በዚህ በደሞዝ ወቅት ነው፡፡ መንገድ ላይ የተለያዩ ዕቃዎችን ለሽያጭ ይዘው የሚወጡ ነጋዴዎችም ከሌላው ቀን በተለየ መንገዱን ሞልተው የምናያቸውን ደሞዝተኛን የሚያባብል እና የሚያግባባ ቃላት በመጠቀም ሸቀጦቻቸውን እንድንገዛ ሲታትሩ የሚታዩት በዚሁ በደሞዝ ወቅት  ነው፡፡ እኛም አዎንታዊ ምላሻችንን አንነፍጋቸውም፡፡
የደሞዝ ሰሞን 2
ከቤተሰብ፣ ጓደኛ እና በአካባቢያችን ከምናገኛቸው ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ይጠብቃል፡፡ ሰላምተኞች፣ ደውሎ ጠያቂ፣ አስታዋሽ እና እንገናኝ ባዮች እና  አሰባሳቢዎች እኛ ነን፡፡ ከፋይ ወይም ከፋይ ለመሆን ልባዊ የሆነ ተነሳሽነት እናሳያለን፡፡ ሲያወሩን በጥሞና እናዳምጣለን (የተሰበሰበ ቀልብ ይኖረናል)፡፡ ድንገት የሚያውቁት ሰው ካለ በማለት አካባቢን እያስተዋሉ መሄድ፡፡ (ምክንያቱም ገንዘብ በኪስ አለ፤ ሻይ ቡና እንበል ቢባሉ ቢያንስ ወጪን ተጋርቶ ለመክፈል ቢበዛ ደግሞ ለመጋበዝ ይችላሉ፡፡)
የደሞዝ ሰሞን 3
የሌለን ነገር ግን ሊኖረን ይገባል የምንለው ነገር ይበዛል፡፡ በተለይ ልብስ፣ ጫማ፣ መጽሐፍ፣ የቤት ቁሳቁስ…እና የመሳሰሉት ከዝርዝራችን ውስጥ የመካተት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በመንገዳችን ያገኘነው መገበያያ ቦታ ወይም ሥራዬ ብለን እገበያው ቦታ በመሄድ የምንፈልገው ነገር እንዳለ እናያለን፡፡ እናማርጣለን፡፡ ልንገዛም ላንገዛም እንችላለን ነገር ግን ለማየትም እንኳን ቢሆን የምንሄደው የደሞዝ ሰሞን ነው፡፡ ይህ አምሮታችን የበዛ ከሆነና ያማረንን ሁሉ የምንገዛ ከሆነ የጠብሽ ሰሞንን ያለጊዜው እንዲመጣ ያፋጥናል፡፡
የደሞዝ ሰሞን 4
ለቀን ወጪያችን መጠንቀቅ አይታይብንም፡፡ የእግር መንገድ እንጠላለን፡፡ አውቶብስ፣ ሃይገር ባስና ሌሎች ታሪፋቸው ዝቅተኛ የሆኑ ትራንስፖርቶችን አንጠቀምም፡፡ የምንመገብበት ምግብ ቤት ከሌላው ቀን ደረጃው ከፍ ያለ ይሆናል፤ ምሳ ከቤት ቋጥሮ መምጣት ይረሳና የምግብ ቤቶች ተጠቃሚ እንሆናለን፡፡
የደሞዝ ሰሞን –ሌሎች
በየሳምንቱ የሚወጡ ትኩረታችን የሚስቡ ጋዜጦችን እና መፅሄቶችን ገዝቶ ማንበብ፡፡ የሚያዝናንን ነገር ለምሳሌ እንደ ፊልም እና ቲያትር ማዘውተር፡፡ መጠጥ፣ ሲጋራ፣ ጫት እና የመሳሰሉ ሱሶችን በምርጫችን ማስተናገድ፡፡ እራስን ማዝናናት፡፡ ‹‹ቺክ›› ለመጥበስ ወይም ፍቅረኛን ለማግኘት ማቀድ እና ተግባራዊ ማድረግ፡፡ በዚሁ ወደጠብሽ ሰሞን እንሸጋገር…
የጠብሽ ሰሞን 1
ደሞዝተኛ ደሞዙን ጨርሶ ቀጣዩ ደሞዙ እስከሚደርስ ያለውን ጊዜ ለማሳለፍ የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም ይጠበቅበታል፡፡ ከዛ ውስጥ አንዱና ዋነኛው ተበድሮ ያን የጠብሽ ጊዜ በቁጠባና በማብቃቃት ጥበብ ማሳለፍ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ደሞዝተኛ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አበዳሪዎች እንዲኖሩት ከሚሠራው ሥራ ባልተናነሰ ተግቶ መሥራት አለበት፡፡ አበዳሪዎች ቋሚ ወይም የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የገንዘብ ሰብሳቢ ካለውና ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነው ሰው ወይም ጓደኛ ከሆኑ  ብዙም ሳይጨናነቁ ብድር በቀላል የማግኘት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡  ‹አበዳሪ ሲያበድር የሰጠ ይመስለዋል› የምትለዋ አባባልም በተበዳሪ የተፈጠረችና በጠብሽ ወቅት በአበዳሪና ተበዳሪ ግንኙነት ተደጋግማ የምትጠቀስ ናት፡፡
የጠብሽ ሰሞን 2
ከጓደኛ ጋር ያለንን ግንኙነት እንቀንሳለን፣ ለወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስልክ አለመደወልን እንመርጣለን ወይም ሚስድ ኮል እናደርጋለን፣ ጓደኞችን ለማግኘት ብዙም ደስተኞች አንሆንም፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ባንገናኝ እንመርጣለን፣ ብዙ ጊዜ ስልካችንን ልናጠፋ እንችላለን፣ ሰዎች ሲያወሩን ቀልባችንን ሰብስበን አናዳምጥም፣ በራስ የመተማመን መንፈሳችን ይቀንሳል፡፡
የጠብሽ ሰሞን 3
በጣም አስቸኳይ እና በእለቱ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር የምንገዛው አዲስ ነገር አይኖርም፡፡ አዲስ የሚገዙ ነገሮችን አይናችን እንዳያይ መከልከል ባንችልም ለአእምሮአችን ግን ያየነው አዲስ ነገር እንዴት እንደማያስፈልገን፤ ባለን ነገር መቆየት እንደምንችል፣ ከለው ሰው ተውሰን መጠቀም እንደምንችል እና የመሳሰሉ ምክንያቶችን እንነግረዋለን፡፡
የጠብሽ ሰሞን 4
ወጪያችንን ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ዋጋው ረከስ ያለ ቤት ተመርጦ መመገብ ይጀመራል፡፡ አውቶብስ፣ ሃይገር ባስና የመሳሰሉትን ዝቅተኛ ታሪፍ ያላቸውን የትራንስፖርት መንገዶችን እንጠቀማለን፡፡ የተወሰነ መንገድ በእግር ልንጓዝ እንችላለን፡፡ ምሳ ቋጥረን መምጣታችንን እንጀምራለን፡፡ እነዚህን ስናደርግ ግን ጠብሽ ሰሞን ላይ በመሆናችን እንዳልሆነ ለማሳወቅ የተለያዩ ምክንያቶችን ስንሰጥ ይሰማል፡፡ ለምሳሌ የምግብ ቤቱን፡- ‹ምግቡ እኮ ያው ነው ዋጋው ብቻ ነው፡፡ የዚ የዚ….›፡፡ የትራንስፖርቱን፡- ‹ከታክሲ እኮ ቀድሞ የሚደርሰው ባስ ነው፡፡ በዛ ላይ ቀጥታ ሰፈሬ ያደርሰኛል…›፡፡ በእግር መጓዛችንን ደግሞ ለጤንነት ወይም ክብደት ለመቀነስ ጥሩ ነው ብለን እንደሆነ እንናገራለን፡፡ ምሳ ቋጥረን ስንመጣ ‹የሆቴል ቤት ምግብ እኮ ጥሩ አይደለም፡፡ በምን እንደሚሠሩት አይታወቅም፡፡ ምንም ቢሆን እቤት የተሠራ ይሻላል፡፡….› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እንሰጣለን እንጂ የተበደርናትን ብር አብቃቅተን እስከ ደሞዝ ለመድረስ የምናደርገው እንደሆነ አንናገርም፡፡
የጠብሽ ሰሞን–ሌሎች
ጋዜጣ እና መጽሔት ገዝተን እናነብ የነበርን ወደ ኪራይ እንገባለን፡፡  የገዛ ወይም የተከራየ ሰው ተውሰን ልናነብም እንችላለን፡፡ ፊልም እና ቲያትር ማየት አያምረንም፡፡ መዝናናት አይታሰብም፡፡ የሱስ ነገር ስለማይሆንልን ተጋባዥ የምንሆንበትን አጋጣሚ እናመቻቻለን፡፡ በተወሰነም ፍላጎታችንን እንገድባለን፡፡ ፍቅረኛን ለማግኘትና ‹‹ቺክ›› ለመጥበስ ይህን ወቅት አንመርጠውም፡፡
እነዚህን ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሮችን እየሆንን እና እያደረግን፤ ሁለቱ ወቅቶች እየተፈራረቁ ሲገዙን ወሩ ያልቃል፡፡ በዚህ ተመሳሳይ ዑደትም ቀናት ወራትን፤ ወራት ዓመታትን እየሆኑ ጌዜዎች ያልፋሉ፡፡
በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ በሁለቱ ወቅቶች የሚኖረን አስተሳሰብ የተለያየ ነው፡፡ በተለይ የገንዘብ አወጣጥ መርሓችን በሁለቱ ወቅቶች ፍፁም አይገናኝም፡፡ የጠብሽ ሰሞን በምንከተለው የገንዘብ አወጣጥ ቀመር እየተመራን ሙሉ ወሩን ማሳለፍ ብንችል የት በደረስን ብዬ አስብና እሱን ለማሰብ ግን የጠብሽ ሰሞን ጭንቅላት እንደሚጠይቅ ትዝ ሲለኝ እተወዋለሁ፡፡ ልክ ይህን ጽሑፍ ለጻፈፍ የጠብሽ ሰሞን ጭንቅላት እንደጠየቀኝ ሁሉ ማለት ነው፡፡
ረጅም እድሜ ለአበዳሪዎቻችን!
—–
* ጠብሽ – በኢ-መደበኛ (‹‹የአራዳ››) አነጋገር ዘይቤ ባዶ ኪስ ወይም የችግር ሁኔታን ይገልጻል፡፡

Tuesday 25 December 2012

ምነው ኖርዌ ምነው ኦስሎ[ወለላዬ ከስዊድን]



ሀገራችን በግፍ ችንካር ተከንችራ፤.............. በሞት ሽረት ተውጥራ፤

የመከራ የጭንቅ ማቅ፤............. ተከናንባ ስትማቅቅ፤

ከግፈኞች መዲፍ ወጥተን፤............ ባንቺ ጉያ ተወሽቀን፤

ግዜ ባማጥን ቀን በገፋን፤............... ምነው! ምነው! ምነው! ኖርዌይ ምነው! ኦስሎ?

ችግራችን ታየሽ ቀሎ። ...........ምን አጥፍተን ጨከንሽብን .......ምነው ፊትሽ ጠቆረብን፤

ምነው ጣልሽን ከእቅፍሽ፤ ..........ምን አረግን ምን በደልንሽ?

ደራሽ ሆነሽ ለተጎዳ፤ ..........አግኝተሽን ባንችው ጓዳ፤

ምነው ውጪ ወረወርሽን፤ ..............በምን ጥፋት ተቀየምሽን?

ምነው! ምነው! ምነው ኖርዌ ምነው! ኦስሎ? ........ችግራችን ታየሽ ቀሎ?

ምነው ኦስሎ ምነው ኖርዌ፤ .............ሀገራችን የዘር ደዌ፤

ይዟት ታማ ስትማቅቅ፤ ............በችግሯ ስትጨነቅ፤

የሰው ክብር ሰብዓዊነት፤ .........ዱሞክራሲ እኩልነት፤ ......ጭራሽ አጥታ ቆማ እራቁት፤

ሕግ ጠፍቶ ፍርድ ሲጎድል፤ .........ባንቺ ጉያ ብንጠለል፤

ጉዳጉዱን በጠረግን፤ ...........ስርቻውን ባጣጠብን፤

ምን አጥፍተን ምን በደልን፤ ..........ፀዲል ፊትሽ ጠቆረብን።

ጉያሽ ኖረን ሇብዙ ዓመት፤ .........ሳንጨብጥ ትንሽ ቅሪት፤

ካንቺው ወስደን፤ ......ላንቺው ሰጥተን፤ .......አጎብሰን አንገት ደፍተን፤ ......ግብር ከፍለን ሕግ አክብረን፤

አጎንብሰን አንገት ደፍተን፤ ...........በኖርንብሽ በመዋተት፤

ምነው! ኖርዌ ምነው? ኦስሎ፤ .........ችግራችን ታየሽ ቀሎ?

ደጅሽ ተርፎ ተትረፍርፎ፤ ...........እጅግ በዝቶ ሀብትሽ ገዝፎ፤

ሆነሽ ሳለ ሀብታም ምድር፤ ............ምነው? ጣልሽን እኛን ላአሳር?

ሲቸግረው ሰው ሲከፋ፤ ................በሀገሩ ሲያጣ ተስፋ፤

ሁለም ቢሆን ይሰደዳል፤ .............ዛሬም አለ ፊትም ደርሷል።

ሆኖም ወጥቶ ለሚጠለል፤ ........የታላቁ መጽሐፍ ቃል፤ ........ድጋፍህን ስጠው እንዱል


እያወቅሽው እያስተማርሽ፤ ..........በዓለም ዙሪያ እየሰበክሽ፤ ..........ሰብዓዊ ሀገር ጥሩ እያለሽ፤

ምነው በእኛ እንዲህ ጨከንሽ? .............ምነው! ምነው! ምነው! ኖርዌ ምነው! ኦስሎ፤

ችግራችን ታየሽ ቀሎ?

Monday 24 December 2012

ሰበር ዜና ከጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም መኝታ ቤት እና የቤተሰብ ሳሎን ውስጥ ምስጥራዊ የድምጽ መቅጃ ተገኙ !!!

 


ሰበር ዜና
ከጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም መኝታ ቤት እና የቤተሰብ ሳሎን ውስጥ ምስጥራዊ የድምጽ መቅጃ ተገኙ !!!

ከቤተ መንግስት ታማኝ ምንጮች ዛሬ ባገኘሁት መረጃ መሰረት የአቶ ሃይለማርያም ትንሽዋ ልጅ እጹብ ባባትዋ መኝታ ቤት በረቀቀ መንገድ ከአልጋው ተያይዞ የተቀመጠ ምስጢራዊ የድምጽ መቅጃ በማግኘትዋ...ይህንን ተከትሎ በተደረገው ከፍተኛ ፍተሻ በቤተሰቡ ሳሎን ውስጥም ሌላ ተመሳሳይ መገኘቱን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች አሳብቀዋል::

ቤተሰቡ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ መገኘቱ ከሌላ የስነልቦና ቀውስ እንዳይዳረጉ በመስጋት የሃዋርያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከነተከታዮቻቸው ለጽሎት በጠ/ሚ መኖርያ ከትመዋል::

ምንጮቼ እንዳሉኝ በከፍተኛ አይነቁራኛ የሚጠበቁት ሃ/ማርያም እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው በየሰአቱ ለ ሕወሓት አመራሮች ወኪል ዸብረጺሆን ሪፖርት ይደረጋል::ከጥቂት ቀናት በፊት ሶስና ለተባለች ልጃቸው ካልታወቀ ሰው..በሞባይል ቁጥርዋ በኢንተርኔት መስመር ተደውሎ `` አባትሽ የስልጣን መልቀቂያ እንዲያቀርብ ግፊት አድርጉበት ....`` የተባለች ሲሆን ` ይህንን ንግግር ሪኮርድ አድርጋ ለአባትዋ እንድታሰማ በታዘዘችው መሰረት አድርጋዋለች:: ይህንን ደሞ ሊያደርግ የሚችለው ሕወሓት ብቻ ነው ሲሉ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

የቤተሰቡ ምንጮች እንደሚሉት አቶ ሃ/ማርያም ...እነዚህ ሰዎች ሊያሰሩን አልቻሉም ከጌታ ሊያጣሉኝ ነው ሲሉ ተሰምተዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከቀድሞው ወድጆቻቸው ጋር ተገናኝተው በነበረ ጊዜ ሕወሃት ሊያሰራቸው እንዳልቻለ / http://www.ethiopianreview.com/content/43279 / ገልጠዋል::
የወታደሩን ክፍል እና ቢሮክራሲውን በተለየ የተቆጣተሩት ህወሃቶች አቶ ህ/ማርያም ምንም አይነት ዉሳኔ እንዳያደርጉ ተጽእኖ ፈጥረውባቸዋል ሲሉ አንድ ወዳጃቸው ተናግረዋል:: በደህንነት የተከበቡት እኚህ ምስኪን ሰው እንደ በላይ ተቆጣጣሪ ሃገራዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን በወቅቱ እንደማያገኙ ተናግረዋል::

አቶ ሃይለማርያም ለፖለቲካ እስረኞች ምህረት ማድረግ እየፈለጉ በሕዋሓት ተጽእኖ ምንም ሊወስኑ አልቻሉም::
ከኤርትራ መንግስት ጋር ለአከባቢው ሰላም ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ለመስራት ቢፈልጉም ህወሃት በዚህ ጉዳይ እንዳይገቡበት አስጠንቅቁዋቸዋል::
የአባይን ግድብ በተመለከት ሃይለማርያም የፖለቲካ መጭበርበር እንደተደረገባቸው እየተናገሩ ሲሆን መለስ ዜናዊ ካረፉ በሁዋላ ሕወሓት ፕሮጀክቱ እንዳይንቀሳቀስ እንቅፋት በመሆን የፕሮጀክቱ ገንዘብ እና ንብረት እንዲመዘበር አድርጉዋል...ሰራተኞች ክፍያቸዉን እንዳያገኙ ችግር ፈጥሩዋል...እስከዛሬ የተሰበሰበው ገንዘብ እንዳይታወቅ እንቅፋት ሆነዋል ሕወሓቶች!!!! እንዳሉት የቤተ መንግስት ምንጮች::