"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 27 December 2012

አሳዛኝ ሰበር ዜና ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ መስጂድ በር ላይ በሳንጃ ታርደው ተገኙ።

    

አሳዛኝ ሰበር ዜና
ሳኡድ አረቢያ ሪያድ ከተማ ዉስጥ በተለምዶ መንፋሃ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ሻራ እሽሪን መስጂድ በር ላይ ሁለት ኢትዮጵያውያንበሳንጃ ታርደው ተገኙ። ሲሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮት ገለጡ::
ኢትዮጵያውያን በሪያድ ከተማ በብዛት ከሚኖሩባቸው አከባቢዎች አንዱ መንፍሃ ተብሎ የሚጠራው አከባቢ ይጠቀሳል::
ይህ ቦታ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ አስከፊውን የባህር ጉዞ አልፈው ሳኡድ አረብያን ለመርገጥ የታደሉ ወጣቶች የሚስተናገዱበት እንደመሆኑ መጠን በወገኖቻችን መካከል አልፎ አልፎ በሚፈጠረው የብሄር ግጭት በሰው ሃገር የሚሰማው ዘግናኝ ዜና የሃገራችንን በጎ ጘጽታ ለውጦታል::
በተለይ ቀደም ብሎ ያንድ ኢትዮጵያዊት ሬሳ በሳንጃ ተዘልዝሎ በሻንጣ ተጠቅልሎ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ዉስጥ ተጥሎ መገኘቱ በአከባቢው ነዋሪ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮዋል ሲል የሚኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ከሪያድ ተናግረዋል::
በሪያድ እና አከባቢው እትዮጵያውያን ወጣቶች ማህበርን ምኒሊክ ሳልሳዊ ያመስግናቹሃል::
ኢትዮጵያውያንን
በዛሬው እለት በዚህ ዙሪያ የወያኔ ዲፕሎማቶች ስብሰባ ጠርተዋል::

No comments:

Post a Comment