"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday, 11 August 2012

የቤተመንግስት ዜናዎችየመለስ ዜናዊ ቤተሰቦች ሃዘን ላይ መቀመጣቸው ታወቀ በፍርሃትና በጭንቀትም ተውጠዋል!


የቤተመንግስት ዜናዎች
በሙሉነህ ዮሃንስና የዲፕሎማቲክ ምንጮች የተቀናበረ (August 9, 2012)
 የመለስ ዜናዊ ቤተሰቦች ሃዘን ላይ መቀመጣቸው ታወቀ በፍርሃትና በጭንቀትም ተውጠዋል!
 የአዜብ እና የበረከት ጸብ እየተካረረ ሄዷል!
 ውጭ አገር የተመደቡ አምባሳደሮች በሙሉ ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደአዲስ አበባ እንዲመለሱ ታዘዙ!
አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስካሁን አልተመለሰም!
የመለስ ዜናዊ ቤተሰቦች ሃዘን ላይ መቀመጣቸው ታወቀ በፍርሃትና በጭንቀትም ተውጠዋል!
ከህዝብና ከሚዲያ ከተሰወረ 45  ቀናት ያሳለፈው የመለስ ዜናዊ መኖርና አለመኖር አሁንም በሰፊው አወዛጋቢ እንደሆነ
ቢቀጥልም ከወደ ቤተመንግስት ጓዳ ያገኘናቸው የማያወላዱ መረጃዎች ግን የሰውየውን ህልፈት የሚያረጋግጡ ናቸው።
ለዋቢነትም የመለስ ዜናዊ ሚስት እናት የሆኑት ቆንጂት ጎላ ጎሹ እና የመለስ እህት የሆነቸው ዘውዲ ዜናዊ እጅግ በከባድ
ሃዘን ተውጠው መሰንበታቸውና ውስጥ ውስጡንም ቅርብ የሆኗቸው ሰዎች እያስተዛዘኗቸው መሆኑ ተረጋግጧል። እነዚሁ
ግለሰቦች ስለመለስ ሁኔታ እንዲገለጽላቸው የመንግስት አካላትን ቢጠይቁም አርፋችሁ ተቀመጡ ተብለዋል። መለስንም
በስልክም ሆነ በአካል አግኝተው አያውቁም። እኒህ ቤተሰቦች የመለስን በህይወት አለመኖር ተገንዝበው ሌት ተቀን በለቅሶ
እያሳለፉ መሆኑ ታውቋል። የቅርብ ሰዎቻቸውም እያሾለኩ እለቅሶውን እየደረሷቸው ይገኛሉ። የመለስን መሰወር በመደበቁ
ባለቤቱ አዜብ መስፍንም እንዳለችበት የተረዱት ቤተሰቦቿ ሃዘናቸውን አክብዶታል ተብሏል። በአጠቃላይ ግን
በቤተመንግስት አካባቢ ጭንቀት፤ ፍርሃት፤ አለመረጋጋትና መረበሽ እንደሰፈነበት መረጃውን ያካፈሉን የዛው ሰፈር ሰዎች
ጨምረው ገልጸውልናል።
የአዜብ መስፍን እና የበረከት ስምዖን ጸብ እየተካረረ ሄዷል!
መነሻው ለጊዜው ያልታወቀው የአዜብ መስፍንና የበረከት ስምዖን ጸብ እየተካረረ መምጣቱን የተለያዮ ምንጮች እየገለጹ
ነው። ጸባቸው አደባባይ የወጣው ግን ከመለስ ዜናዊ ህመም/ሞት በተያያዘ መሆኑ ታውቋል። አዜብ ምን እንደሆነ በግልጽ
ያልታወቀ ትእዛዝ ለበረከት ስታዘው አንቺን እኮ የማውቅሽ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚስትነት ብቻ ነበር የሚል ምላሽ
በመስጠቱ የተበሳጨችው አዜብ ይህው ትእዛዝ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲደርሰው ታደርጋለች። በዚህ ናላው
የዞረው በረከት አኩርፎ ባህር ዳር መሽጎ ነበር። ለዛውም ነው የመለስን መታመም የምንግስት አፈቀላጤ የሆነው በረከት
ይፋ ማድረግ ሲገባው ከባህር ዳር አልመለስም ብሎ ስለነበር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ሰሞን ለህዝብ
በይፋ ለመጀመሪያ እንዲገልጽ ግድ የሆነበት። በተያያዘም አማራን እወክላለሁ በሚለው የብአዴን ታጣቂዎች ዘንድ ተወዳጅ
ነው የሚባልለት ተፈራ ዋልዋ ከመለስ ጋር በነበረበት የረዥም ጊዜ ውዝግብ ምክንያትው ከተገለለበት አመራር ቦታ እንዲመለስ
ጥሪ ቀርቦለት እንዳልተቀበለው መገለጹ የባለስልጣናቱ የሃይል አሰላለፍ ጥድፊያ በይፋ እየታየ ነው። በረከትና ተፈራም
በክፉ የሚተያዮ ሰዎች እንደሆኑ የብአዴን ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ።                                                                    ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደአዲስ አበባ እንዲመለሱ ታዘዙ!
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባስተላለፈው አስቸኳይ ትእዛዝ መሰረት ውጭ ሃገር ተመድበው የሚሲዮኖች ዋና
ሃላፊዎች የሁኑት አምባሳደሮች በሙሉ ወደ አዲስ አበባ ባልታወቀ ጉዳይ እንዲመለሱ መታዘዛቸውን የተለያዮ የዲፕሎማቲክ
ምንጮች አረጋግጠዋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወደ ውጭ ጉዳይ
ሚኒስቴር እስካሁን እንዳልተመለሰ ታውቋል። ብዛት ያላቸው ዲፕሎማቶች ደግሞ ከኢምባሲ እየጠፉ በውጭ ሃገራት
ጥገኝነት እያመለከቱ መሆኑ ተረጋግጧል። የመንግስት አለመረጋጋት በግልጽ በሚታይበት በዚህ ወቅት አምባሳደሮቹ
መጠራታቸው የሚጠበቅ ነው የሚሉት እኒህ የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠሩት ለብርቱ ጉዳይ በአካል መነጋገር ግድ
ስለሚል መሆኑን ጨምረው አብራርተዋል። ይህ ጥሪ በስዮም መስፍን አመራር እየተካሄደ መሆኑ ግን በዲፕሎማቶች
አካባቢ ግርታን ፈጥሯል። ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሳ እንደዘገበችው ስዮም መስፍን ከቻይና ተመልሶ
መንግስት የመምራት ስራ ላይ እንደተጠመደ ተመልክቷል። ከላይ የጠቀስነው የሃይል አሰላለፍ ጥልፍልፎሽ ሽኩቻው አድጎ
ወደ ሃይል መጠቀም ማደጉ አይቀሬ መሆኑን ብዙ ተንታኞች ይስማሙበታል።

Friday, 10 August 2012

በደሴ “አረብገንዳ” መስጊድ ፖሊስ ጥቃት ሰነዘረ




(አቤ ቶኪቻው) 
ላለፉት ስምንት ወራት የቀጠለው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚያሰሙት ተቃውሞ በዛሬው ዕለትም በተለይም በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ እና በደሴ አረብገንዳ መስጊድ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ፖሊስ በደሴ የተገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ወሬዎች ደርሰውኛል።
የረመዳን ፆም እንደገባ “ድምፃችን ይሰማ” በሚል ተቃውሞውን ሲያስተባብሩ የነበሩት የኮሚቴ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቢውሉም ህብረተሰቡ በራሱ አስተባባሪነት “ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ” የሚል ተጨማሪ ጥያቄ አንግቦ ተቃውሞውን ቀጥሏል።

ባለፈው ሳምንት ተቃውሞቸውን በይፋ የጀመሩት የደሴ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ወገኖችም ተቃውሟቸውን በተጠናከረ መልኩ ዛሬም የቀጠሉበት ቢሆንም ልዩ የፖሊስ ሀይል “ከመስጊድ እንዳይወጡ ከልክሎ” የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱን ሰምቻለሁ። በተተኮሱ አስለቃሽ ጭሶች ሴቶች እና በዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች ራሳቸውን ስተው በመስጊድ ውስጥ እርዳታ ሲደረግላቸው እንደነበር ከስፍራው የሰማሁት ወሬ ያስረዳል። (ያረዳል ብንለው ይሻላል)
ባለፈው ጊዜ፤ “ህብረተሰቡ ተረባርቦ ይሄንን ተቃውሞ የማያስቆም ከሆነ የከፋ ነገር ይመጣል!” ሲሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በሞቅታ ይሁን በብስጭት ሲናገሩ ሰምቻቸዋለሁ።
እኔ የምለው ግን የራሳችን ሀገር ፖሊስ “ወዮላችሁ!” እያለ የሚያስፈራራን ከሆነ ጠባቂያችን ማነው!? ብሎ መጠየቅ ይቻላል!?



Ethiopian police crack down on Muslim press


Nairobi, August 9, 2012-Ethiopian authorities must release a journalist who has been detained for almost three weeks, and allow three Muslim news outlets to resume publishing immediately, the Committee to Protect Journalists said today. Local journalists believe the Muslim press in Ethiopia is being targeted for its coverage of protests by the Muslim community.



In recent months, Ethiopian Muslims have begun staging protests on Fridays to oppose government policies they say are interfering with their religious affairs, according to news reports . These protests are a highly sensitive issue for the government, which fears a hardline Islamist influence within the predominantly Christian country, news reports said. Local journalists believe the recent harassment of Muslim journalists and newspapers are part of an attempt by Ethiopian authorities to quell coverage of the ongoing protestsin the capital.

Wednesday, 8 August 2012

“እስላም ክርስቲያኑ ባንድ ሆነ ፆማቸው… ከአምላክ ለመድረስ ቀጠሮ እንዳላቸው” ማን ያውቃል




የአሁኑ አመጣጤ ክርስቲያን ወዳጆቼን አንኳን ለፆመ ፍልሰታ አደረሳችሁ ለማለት እና ሙስሊም ወዳጆቼን ደግሞ የተጀመረው “ዱዓ” ይቀጥልልን ብሎ ለማበከር ቢሆንም “በልጅ አመካኝቶ ይበላል እንኩቶ” እንዲል እንኮቶ ያማረው አባት… እግረ መንገዴን  ከመጣሁ አይቀር ኮስተር ብዬ የማነሳው አንድ ጉዳይ አለኝ።

ትላንት አንድ መረጃ ለጥፌ ነበር። መረጃው “በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በህቡዕ የሚንቀሳቀስ” አንድ ንቅናቄ ያወጣው መግለጫ ነበር። ይህ መግለጫ “የሰራዊቱ አባላት ከዚህ በኋላ ህዝብ ላይ አንተኩስም እስከ መቼ ለአምባገነን መሪዎች አግዘን፤ እኛ መሳሪያ ታጥቀን ቀበቶ እና መቀነት ብቻ የታጠቀውን ህዝብ እንደበድባለን!? ይሄ ነገር ነውር መሆኑን አየን ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነት ነገር ላለመፈፀም ዝግጅታችንን አጠናቀናል”  የሚል ነበር።

ታድያ በዚህ ወሬ የተነሳ በርካታ አስተያየቶችን ተቀብያለሁ። “እሰይ የኔ ወሬ አቀባይ በርታልኝ” ብለው ያበረታቱኝ እንዳሉ ሆነው አንዳንድ ወዳጆች ደግሞ “አንተ ከሀገር ወጥተህ እኛን ልታስጨርስ ነው!” የሚል ወቀሳ ሰንዝረዋል። ይህ ወቀሳ ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ፉርሽ መሆኑን እንደሚከተለው አስረዳለሁ!

ሀ    የንቅናቄው መግለጫ የሚለው የመንግስት ግልበጣ ላድርግ አይደለም፣ ጫካ ገብቼ ጦርነት ልክፈትም አላለም። ከዚህ በኋላ መንግስት ተኩስ ባለኝ ቁጥር ግን ህዝቤ ላይ አልተኩስም ነው ያለው።  በኛ የጨዋታ ስልት ሲቀርብ ደግሞ “ክላሽ እኮ ካውያ አይደለም… ሰውን ያበላሻል እንጂ ልብስን አያሳምርም!”  ስለዚህ ከእንግዲህ ፖሊስም ሆነ ሌላው የጦር ሃይል ከህዝቡ ወገን ነው እንጂ የህዝቡ ወጊ አይደለም ነው ያለው። ታድያ ይሄ እንዴት ሆኖ ነው ህዝብ ማስጨረስ የሚሆነው??? (ጥያቄ ምልክት ጨምሩልኝ!)

ፌደራል ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ “የጁነዲን ሳዶን ባለቤት ያሰርኩት በሽብርተኝነት ጥርጥሬ ነው” አለ



የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሁለት ሣምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሽብር ተግባር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገ ሲል ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ።
የፌዴራል ፖሊስ የውጪና ሕዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወ/ሮ ሃቢባ የተያዙት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር በተያያዘ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ ከፍ/ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ መሠረት ነው። ፖሊስ ያለማስረጃና ያለበቂ ጥርጣሬ ከመሬት ተነስቶ አንድን ግለሰብ ሊይዝ የሚችልበት ሕጋዊ መሠረትም እንደሌለ አስረድተዋል።
ተጠርጣሪዋ ከተያዙ በኋላ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ ተፈቅዶ በምርመራ ላይ መሆናቸውን ኮማንደር አበበ አስታውሰዋል።
ሚኒስትር ጁነዲን የምርመራ ሂደቱ ሳያልቅ ባለቤታቸው ንፁህ መሆናቸውን መናገራቸው ተገቢ አለመሆኑን ኮማንደሩ ገልፀዋል። ‘‘የአንድ ሰው ነፃ መሆን የሚረጋገጠው በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ ነው። ፖሊስና የዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ባልተሰማበት ሁኔታ ባለቤቴ ንፁህ ናት ብሎ መናገር ተገቢ አይደለም’’ ብለዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ይኸው ጋዜጣ በዛሬው እትሙ በሕዝበ-ሙስሊሙ እና በመጅሊሱ መካከል ላለፉት ሰባት ወራት የተፈጠረውን አለመግባባት በሽምግልና ለመፍታት እየተሞከረ ነው፤ ሽምግልና ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ያሉት በራስ ተነሳሽነት የተሰባሰቡ ስምንት አባላት ያሉት ገለልተኛ ግለሰቦች ናቸው ሲል ዘገበ።
አለመግባባቱን በሽምግልና ለመፍታት ጥረቱን የጀመሩት የእምነቱ ተከታይ የሆኑ የሀገር ሽማግሌዎችና የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው። ይህንኑ ሙከራቸውን በተመለከተ በመንግስት በኩል ያለው ምላሽ እስካሁን አለመታወቁን ሽምግልናውን ጀምረናል ካሉት መካከል አንዱ ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለጹለት ዘግቧል።
የሽምግልናው መጀመር በተመለከተ በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ የተደበላለቀ ስሜት መፍጠሩን ምንጮቻችን አመልክተዋል ያለው ሰንደቅ ሽምግልናውን የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ ቀላል የማይባሉ የእምነቱ ተከታዮች ጅምሩን በጥርጣሬ አይን እያዩት ነው። ሽምግልናውን ከጀመሩት የኮሚቴ አባላት አንዱ የሽምግልናው መጀመር መደገፍም ሆነ መቃወም መብት መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ‘‘እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን’’ ማለት ግን አክራሪነት ነው ብለዋል።
‘‘አንደኛውም ሆነ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሰላም ስምምነት ነው የተፈታው’’ ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሽምግልናው ኮሚቴ አባል ችግሩ በእርቅና በሽምግልና ይፈታ ማለት የሃይማኖታችንና የሀገራችን ባህል ነው ብለዋል።
የሽምግልና እንቅስቃሴው ከተጀመረ በኋላ አንዳንድ ታዋቂ ሰዎችም በጉዳዩ ውስጥ ለመግባት ፍላጐት እያሳዩ መሆኑም ታውቋል። ሽምግልናው የታሰሩትን አባላት ከማስፈታት ባለፈ ችግሩን ከስሩ መርምሮ የመፍታት ዓላማ እንዳለው ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም በዘለለ እንደ ሀገር መኖር ስላለብን መንግስት የሽምግልናውን ሂደት በሆደ ሰፊነት ይመለከተዋል የሚል ተስፋ አለን ብለዋል።
ሕዝቡ ሙስሊሙ በተመለከተ የቁርአንን ሕግና የነብዩን ትምህርት ላይ የቀረቡ ደንብና ስርዓቶችን እያገናዘበ እንዲጓዝ እንፈልጋለን ያሉት የሽምግልናው አስተባባሪዎች፤ ሕዝበ-ሙስሊሙ የቁርአንን ሕግ፣ የእስልምና ታሪክ በወጉ በማወቅና በሰከነ መንፈስ እንዲጓዝ ጠይቀዋል። ‘‘ጉዳዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም’’ የሚሉት አስተባባሪዎቹ የሃይማኖት ጉዳይ በወጉ መያዝ እንዳለበት አሳስበዋል። የሽምግልናው ሂደት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ሲል ማንነታቸውን በግልፅ እንደሚያሳውቁም አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በመንግስት በኩል ስለ ሽምግልናው ያለው ምላሽ ለጊዜው አልታወቀም። አንደ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የመንግስት ባለስልጣን መንግስት ከወንጀለኞች ጋር አይደራደርም ማለታቸው የሽምግልናውን ሂደት አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋትን ከወዲሁ ፈጥሯል።
ባለፉት ሰባት ወራት በእስልምና ም/ቤት መጅሊስ አመራር ምርጫ፣ ምርጫው የትና በማን ይከናወን፣ በአወሊያ ት/ቤት አስተዳደር፣ በአሕባሽ አስተምህሮ ጉዳይ በሕዝበ-ሙስሊሙ እና በመጅሊሱ እንዲሁም በመንግስት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ይታወሳል። አለመግባባቱንም ተከትሎ በታላቁ በአንዋር መስጊድና በአወሊያ ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች መጎዳታቸውና መታሰራቸው ይታወቃል።

i

አምባሳደር ስዩም መስፍን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ተክተው እየሰሩ መሆኑ ተጠቆመ



የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ከ45 ቀናት በላይ በመደበኛ ስራቸው ላይ ባለመሆናቸው በኢህአዴግ አመራሮች መካከል በስልጣን ሽኩቻ እንደተፈጠረና አቶ ስዩም መስፍን የአቶ መለስን ቦታ ተክተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮች እንደገለፁት የቻይና ዲፕሎማቶች ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድርድር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ስዩም መስፍን ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ጋር በመምጣት ቤተመንግስት ሆነው የመሪነቱን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን ይህንን ለማጣራት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ጋር ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ስልካቸው ባለመነሳቱ ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጠይቀናቸው “አምባሳደር ስዩም መስፍን በአሁን ወቅት በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ናቸው፡፡ መደበኛ ሥራቸውም ይሄ ነው፤ ከዛ ውጭ እንደማንኛውም አምባሳደር ለስራ ጉዳይ ሀገር ቤት ይመጣሉ” በማለት ተጨማሪ ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጤና አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እየተገለፀ ቢሆንም በቅርቡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጠ/ሚኒስትሩን መታመምና በህክምና ላይ መሆናቸውን እንዲሁም እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው በሐኪሞቻቸው እንደተነገራቸው ከማሳወቅ ውጭ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በግልፅ ማን እየመራ እንዳለ ከመግለፅ በመቆጠቡ ይታወሳል፡፡


አቶ ስብሀት በምን “ካፓሲቲ” ነው እየተናገሩ ያሉት?



የአቶ መለስን መታመም አስመልክቶ አቦይ ስብሀት በቅርቡ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፦”ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት ስለገነባን በቀለ ሄደ አልሄደ፤ፋጢማ ሄደች አልሄደች የሚመጣ ለውጥ የለም” ብለው ነበር። ትናንትም በደቸ ቨለ ራዲዮ ቀርበው ያንኑ አባባላቸውን የሚያጠናክር ነገር ሲናገሩ ተደምጠዋል።
አቶ ስብሀት የመጀመሪያውን ቃለ-ምልልስ ለቪ.ኦ.ኤ በሰጡ በተከታዮቹ ቀናት በኢሳት የትኩረት ፕሮግራም ተጋባዥ የነበሩት አቶ የሱፍ ያሲን ይህን የአቶ ስብሀትን ንግግር እንዴት እ
ንደሚያዩት ጋዜጠኛ ሢሳይ ላቀረበላቸው ጥያቄ፦ አቶ ስብሀት እያደረጉት ያለው ነገር፤ከሚናገሩት ነገር ጋር የሚጣረስና ህጋዊ ሥርዓት አለመኖሩን የሚያሳይ እንደሆነ ነው በግልጽ ያስረዱት።
“ ህጋዊ ስርዓት ቢኖር፤ አቶ ስብሀት ያን ቃለ-ምልልስ ሊሰጡ አይችሉም ነበር” በማለት።

Tuesday, 7 August 2012

Ethiopian Dictator Goes MIA



Is Meles a Vegetable?
Ethiopian Dictator Goes MIA
by THOMAS C. MOUNTAIN
Eritrea.

Long time Ethiopian dictator Meles Zenawi, missing in action for almost 2 months now, is reported to be in a coma leaving the Obama White House’s Crisis Team for Africa scrambling to find a replacement. Officially, Ethiopian “Prime Minister” Meles Zenawi has taken “sick leave” and “getting better”, end of story.

In reality the situation in Ethiopia’s capital Addis Ababa finds the CIA media handlers floating the idea that with Meles Zenawi “sick” a “Transitional Government” will hold power until national “elections” scheduled for 2015 are held.

Numerically as well as in equipment inventory the Ethiopian army is the largest best equipped in Africa. The CIA has been paying the Ethiopian army’s salaries directly for some time now, as they have done in South Sudan since 2009.

Most of the Ethiopian army is little more than militias, often times paid in wheat “donated” by the UN’s World Food Program amongst others. These militias are made up largely of street boys recruited out of Addis Ababa’s teaming slums or village boys whose service is traded by their families for grain and a few dollars a month. These “soldiers” are mainly of the Oromo nationality, half or more of Ethiopia, and are lead by the remnants of the Tigrayan officer core from within which Meles Zenawi once found a power base.

Etnisk vold herjer sør i Etiopia Publisert 29.07.12 - 09:35, endret 29.07.12 - 09:42 (© NTB)


Over 18 mennesker er drept og flere tusen har flyktet fra etniske kamper i Etiopia, melder Røde Kors.

VG Nett følger

Flere enn 20.000 mennesker har krysset grensen til Kenya fra Sør-Etiopia, opplyser Kenya Røde Kors til BBC. Selv om etiopiske regjeringsstyrker har grepet inn for å stanse sammenstøtene, fortsetter folk å strømme over grensa.

Kampene i Moyale-distriktet mellom folkegruppene Borana og Garri skal hastartet som en uenighet over hvem som hadde rettighetene til et landområde.

Det har lenge vært konflikter om vanntilgang og beitemark i området                                                    transelation               .Ethnic violence raging in southern Ethiopia
Published 07/29/12 - 09:35, edited 29/07/12 - 09:42 (© AP)

   Tell a friend Print article
Over 18 people are killed and thousands have fled ethnic fighting in Ethiopia, said the Red Cross.

AP follows
Ethiopia
More than 20,000 people have crossed into Kenya from southern Ethiopia, according to Kenya Red Cross said. Although the Ethiopian government forces have intervened to stop the clashes, people continue to pour across the border.

Fighting in Moyale district between ethnic groups Boran and Garri to have started as a disagreement over who had rights to a territory.

It has long been conflicts over access to water and pasture in the area.

Monday, 6 August 2012

የወያኔ ጨዋታ ቀጠለ – አዲስ አድማስ ጋዜጣ “መለስ ቤተመንግስት ውስጥ እያገገሙ ነው ተባለ” አለ


(ዘ-ሐበሻ) የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደሞቱ እየዘገቡላቸው የሚገኘው አቶ መለስ ዜናዊ “ቤተመንግስት ውስጥ እያገገሙ ነው” ሲል የወያኔው ባለስልጣን ስብሃት ነጋ የአክሲዎን ድርሻ ያላቸው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ። ወያኔ አንዴ በሪፖርተር ጋዜጣ “መለስ አሜሪካ እያገገሙ ነው” ሌላ ጊዜ በፎርቹን ጋዜጣ”ተሽሏቸው አዲስ አበባ ገቡ”፤ አሁን ደግሞ በአዲስ አደማስ ጋዜጣ “ቤተመንግስት እያገገሙ ነው ተባለ” የሚሉ ዜናዎችን በማሰራጨት በመለስ ሞት ላይ ሕዝቡ አንድ አይነት አቋም እንዳይዝ በማሳሳት ላይ ይገኛል። “ተባለ እንዴ” አለ ጸሐዬ በአንድ ዘፈኑ ላይ… ቂቂቂቂቂቂቂ! አቶ መለስ በሕይወት ካሉ 45 ቀናት ሙሉ ተደብቀው ምን ያደርጋሉ የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች በአዲስ አድማስ ዘገባ ስቀዋል። የአዲስ አድማስ መረጃ የሚከተለው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሚገኙበት ቦታ እና የሕመማቸው ደረጃ በይፋ ባለመነገሩ ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን አነጋጋሪነቱ የቀጠለ ሲሆን፤ ጠ/ሚኒስትሩ ከመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከአራት ባለስልጣናት ጋር ብቻ በመነጋገር እየሰሩ ናቸው በማለት አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቆሙ፡፡ እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፤ ጠ/ሚ መለስ በውጭ ሀገር ሕክምናቸውን ተከታትለው ከሳምንት በፊት አዲስ አበባ እንደገቡ ጠቅሰው፤ በሁለት ኢትዮጵያዊያን ዶክተሮች ክትትል እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ቤተመንግስት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከአራት ባለሥልጣናት ጋር ብቻ በመነጋገር፣ የሚቀርብላቸውን ሪፖርት እያዳመጡ ትዕዛዝ በመስጠት ላይ ናቸው ብለው እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፡፡

አንድ አስተያየት፤ አቶ ጁነዲን ቻል ያድርጉት… ሁሉም የሚታሰረው ያለ ማስረጃ ነው!


አቶ ጁነዲን ሳዶ ዛሬ ለታተመው ኢትዮ ቻናል  ጋዜጣ  የነገሩትን አውራምባ ታይምስ ዌብ ሳት አቀብላን ተመልክተነዋል።
ሚኒስቴር ጁነዲን ሳዶ ባለቤታቸው ከታሰሩባቸው ዛሬ አስራ ስድስተኛ ቀናቸው ነው። በዚህም የተነሳ ቤታቸው መቀዝቀዙን ልጆቻቸው መጎሳቆላቸውን እና የመሳሰሉትን ጠቅሰው እስሩ አግባብ አይደለም ብለው ተናግረዋል።
የሚኒስቴሩ ባለቤት የታሰሩት ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ መሆኑን ነገር ግን ምንም ማስረጃ እንዳልተገኘባቸው እና የዚህ አይነቱ እስር ነውር መሆኑን አስረድተውናል።
ጥሩ ነው ለሚስትዎ እርስዎ ካልተከራከሩላቸው ሌላ ማን አላቸው…!? ነገር ግን ኦቦ ጁነዲን፤ ካለ ማስረጃ መታሰር እኛ ሀገር ብርቅ ነው እንዴ!?
አንድ ወዳጄ በዚህ ጉዳይ ላይ ስናወራ ምን አለኝ መሰልዎ፤ በቅርቡ የዋልድባ ገዳም መነኩሴዎችን እና የአንዋር መስጊድ “ኡስታዞችን” እስር አነሳልኝ እና “ተዋርዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ!” ሲል አንጎራጉሮልኛል።
እናልዎ አቶ ጁነዲን ቃሊቲ አንዳፍታ ሄድ ብለው ማን በምን ታሰረ…? የሚለውን መርመር ቢያደርጉ እውነት እውነት እልዎታለሁ “እስር ቤቱ ባዶ ከሚሆን” ተብለው የታሰሩ በርካታ ሰዎችን ያገኛሉ።
በቅርቡ እንኳ ፍፁም ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ሙስሊም ወዳጆቻችን “አፈሳ” በሚመስል መልኩ ወደ እስር ቤት ተግዘዋል። እነዚህ ወገኖች ለምን እንደታሰሩ ለማወቅ ከፈለጉ ዝም ብለው አንድ አርብ ወደ አንዋር መስጊድ ይሂዱ፤ በዛውም ለባለቤትዎ “ዱዓ” አድርገው ይመለሳሉ። እናልዎ በአንዋር የሚደንቅ አይነት ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንት ሲደረግ ይመለከታሉ።  እንግዲህ ይህንን ሰላማዊ ተቃውሞ ያስተባበሩ ወገኖች በሙሉ ተለቅመው ከታሰሩ ዛሬ ረመዳን አስራ ስድስተኛ ቀናቸው ነው።
እና አቶ ጁነዲን ከተናገሩ አይቀር ባለ ስልጣን ኖትና በርስዎ ያምራል፤ ሁሉም ያለ ምንም ማስረጃ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ይጠይቁ… አለበለዛ ግን የእርስዎ ባለቤት ያለ ማስረጃ መታሰር ብርቅ አይደለምና ቻል ያድርጉት!
አረ ሳልነግርዎ አንድ ወዳጄ ባለቤትዎ መታሰራቸውን ገና ሲሰማ ምን እንዳለ ሰምተዋል…? ከሰሙም ይድገሙት ካልሰሙም እንሆ፤ “ባለቤቱን ካልናቁ ሚስቱን አይነቀንቁ!”