"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 8 August 2012

አቶ ስብሀት በምን “ካፓሲቲ” ነው እየተናገሩ ያሉት?



የአቶ መለስን መታመም አስመልክቶ አቦይ ስብሀት በቅርቡ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፦”ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት ስለገነባን በቀለ ሄደ አልሄደ፤ፋጢማ ሄደች አልሄደች የሚመጣ ለውጥ የለም” ብለው ነበር። ትናንትም በደቸ ቨለ ራዲዮ ቀርበው ያንኑ አባባላቸውን የሚያጠናክር ነገር ሲናገሩ ተደምጠዋል።
አቶ ስብሀት የመጀመሪያውን ቃለ-ምልልስ ለቪ.ኦ.ኤ በሰጡ በተከታዮቹ ቀናት በኢሳት የትኩረት ፕሮግራም ተጋባዥ የነበሩት አቶ የሱፍ ያሲን ይህን የአቶ ስብሀትን ንግግር እንዴት እ
ንደሚያዩት ጋዜጠኛ ሢሳይ ላቀረበላቸው ጥያቄ፦ አቶ ስብሀት እያደረጉት ያለው ነገር፤ከሚናገሩት ነገር ጋር የሚጣረስና ህጋዊ ሥርዓት አለመኖሩን የሚያሳይ እንደሆነ ነው በግልጽ ያስረዱት።
“ ህጋዊ ስርዓት ቢኖር፤ አቶ ስብሀት ያን ቃለ-ምልልስ ሊሰጡ አይችሉም ነበር” በማለት።

በእርግጥም አቶ የሱፍ እንዳስቀመጡት አቦይ ስብሀት በመንግስት የሥልጣን መዋቅር ውስጥ የሥልጣን ቦታ የላቸውም። በህወሀት ውስጥ ከነበራቸው የኢፈርት የቦርድ ሊቀ-መንበርነት ቦታም ተገፍተው ወርደዋል። ” የኢትዮጵያ ዓለማቀፍ የሰላምና የልማት ኢንስቲትዩት” ተብሎ የሚጠራ እዚህ ግባ የማይባል ቢሮ ተወርውረው አኩርፈው ከተቀመጡ ዓመታት አልፈዋል።
ታዲያ ዛሬ አቶ መለስ መታመማቸውን ተከትሎ የዚያ ዓይነት ቃለ-ምልልስ የሰጡት በምን “ካፓሲቲ” ነው? ምንድነኝ እያሉ ነው ? የመንግስት ሀላፊነት ሳይኖራቸው፣የድርጅት ባርኔጣቸውንም ተነጥቀው ሳለ፤ መለስ ቢኖሩ እና ባይኖሩ ሊፈጠር ስለሚችለው ሁኔታ በዘፈቀደ በአደባባይ የሚናገሩት ፤ በቃለ-ምልልሳቸው እንዳሉት ፦“ህጋዊ ሥርዓት” ስላለ ነውን? በፍጹም!
አዎ! አቶ የሱፍ እንዳሉት ፦ መስመራቸውን ሳይጠብቁ አቶ ስብሀት ህጋዊ ስርዓት እንደተገነባ የተናገሩበት ቃለ-ምልልስ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር፤ በኢትዮጵያ ገና ህጋዊ ሥርዓት አለመኖሩን ነው።



No comments:

Post a Comment