"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 6 August 2012

የወያኔ ጨዋታ ቀጠለ – አዲስ አድማስ ጋዜጣ “መለስ ቤተመንግስት ውስጥ እያገገሙ ነው ተባለ” አለ


(ዘ-ሐበሻ) የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደሞቱ እየዘገቡላቸው የሚገኘው አቶ መለስ ዜናዊ “ቤተመንግስት ውስጥ እያገገሙ ነው” ሲል የወያኔው ባለስልጣን ስብሃት ነጋ የአክሲዎን ድርሻ ያላቸው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ። ወያኔ አንዴ በሪፖርተር ጋዜጣ “መለስ አሜሪካ እያገገሙ ነው” ሌላ ጊዜ በፎርቹን ጋዜጣ”ተሽሏቸው አዲስ አበባ ገቡ”፤ አሁን ደግሞ በአዲስ አደማስ ጋዜጣ “ቤተመንግስት እያገገሙ ነው ተባለ” የሚሉ ዜናዎችን በማሰራጨት በመለስ ሞት ላይ ሕዝቡ አንድ አይነት አቋም እንዳይዝ በማሳሳት ላይ ይገኛል። “ተባለ እንዴ” አለ ጸሐዬ በአንድ ዘፈኑ ላይ… ቂቂቂቂቂቂቂ! አቶ መለስ በሕይወት ካሉ 45 ቀናት ሙሉ ተደብቀው ምን ያደርጋሉ የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች በአዲስ አድማስ ዘገባ ስቀዋል። የአዲስ አድማስ መረጃ የሚከተለው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሚገኙበት ቦታ እና የሕመማቸው ደረጃ በይፋ ባለመነገሩ ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን አነጋጋሪነቱ የቀጠለ ሲሆን፤ ጠ/ሚኒስትሩ ከመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከአራት ባለስልጣናት ጋር ብቻ በመነጋገር እየሰሩ ናቸው በማለት አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቆሙ፡፡ እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፤ ጠ/ሚ መለስ በውጭ ሀገር ሕክምናቸውን ተከታትለው ከሳምንት በፊት አዲስ አበባ እንደገቡ ጠቅሰው፤ በሁለት ኢትዮጵያዊያን ዶክተሮች ክትትል እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ቤተመንግስት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከአራት ባለሥልጣናት ጋር ብቻ በመነጋገር፣ የሚቀርብላቸውን ሪፖርት እያዳመጡ ትዕዛዝ በመስጠት ላይ ናቸው ብለው እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፡፡
አቶ መለስ ፊት ለፊት በሚታየው የአካላቸው ክፍል ላይ ምንም ዓይነት የቀዶ ሕክምና ምልክት እንደሌለ የተናገሩት እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ህክምናውን ያደረጉላቸው ሐኪሞች ብዙ ከመነጋገር እና ከመሥራት እንዲቆጠቡ እንዲሁም በቂ እረፍት እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ እንደሰጧቸው አረጋግጠዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ባለፈው ሣምንት በጽ/ቤታቸው አጠር ያለ መግለጫ እንዲሰጡ ታቅዶ እንደነበር እኚሁ ባለስልጣን የተናገሩ ሲሆን፤ ከጤናቸው ጋር በተያያዘ መግለጫው ሊሰረዝ እንደቻለ ምንጮች ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሕመም በማስመልከት ከአሥራ አምስት ቀናት በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን፤ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥራ የሚመለሱት መቼ ነው? በቀናት፣ በሣምንት ወይስ በወር ጊዜ ውስጥ?›› በሚል ተጠይቀው ‹‹በቀናት›› የሚል ምላሽ ሰጥተው የነበረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ከአቶ በረከት መግለጫ በኋላ ለዓይን ሣይታዩ ሁለት ሣምንት ተቆጥሯል፡፡
በአጠቃላይ ከአደባባይ ከራቁ ደግሞ 45 ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment