ቅድስት ዕሌኒ
የቅድስት ዕሌኒ ባለቤቷ ተርቢኖስ ይባላል፤ በቅድስና ተፋቅረው ነበር የሚኖሩት፤ ተርቢኖስ የሚል ጽሁፍ ያለበት የአንገት ሀብል አሰርቶላት ነበር። ተርቢኖስ ነጋዴ ስለነበር ከጓደኞቹ ጋር በመርከብ ተሳፍረው እሩቅ አገር ሄደው ከ 3 ዓመት በኃላ ይመለሳሉ ፤ ታዲያ መርከብ ላይ እንዲህ እያሉ ይጫወታሉ ፤ እኛስ በሰላም ወደ አገራችን ተመለስን ሚስቶቻችን ግን በሰላም ይጠብቁን ይሆን ሌላ ወንድ ወደውና ለምደው እንዳይጠብቁን አሉ፤ ተርቢኖስ ደግሞ የኔ ሚስት ዕሌኒ ከኔ ሌላ ማንንም አትወድም አትለምድም ይላቸዋል፤ ያንተ ሚስት ከሄዋን ሴቶች ትለያለችን እኔ ሄጄ ወድጃት ወዳኝ ለምጃት ለምዳኝ ብመጣ ምን ትሰጠኛለህ ይለዋል ንብረቴ ሁሉ ላንተ ይሁን ይለዋል በወረታቸው ተወራርደው ይሄዳል::