"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 28 September 2012

ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ታፍኖ ቆየው ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የሙከራ ስርጭት ጀምሯል።



564188_201743973292815_1901961_n
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሙከራ ስርጭት ጀመረ መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በገዢው ፓርቲ አፈና ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ታፍኖ ቆየው ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የሙከራ ስርጭት ጀምሯል። ከኒው ሆርን ቴሌቪዥን የአየር ስርጭት በመግዛት በሚቀጥሉት ቀናት ሙሉ ስርጭቱን የሚጀምረው ኢሳት፣ በቅርቡ ተጨማሪ የራሱ ሙሉ የስርጭት ጊዜ
ይኖረዋል። አዲሱ ስርጭት በኤ ቢ 7 በ7 ዲግሪ ዌስት ላይ በ 10815 ሜጋ ሀርዝ፣ በ27 ሺ 500 ሜትር ባንድ ሲምቦል ሬት፣ በ5 ስድስተኛ
ኤፍ ሲ ይተላለፋል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ናይል ሳትን በመክፈት ስርጭቱን በቀላሉ ለማግኘት ይችላል። ተጨማሪ መግለጫዎችን ሙሉ ስርጭቱ
እንደተጀመረ እንሰጣለን።ባሳለፍነው አመት በአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ የኢሳት ቴሌቪዥን ለሃገሪቱ ይሰጥ የነበረው የአገልግሎት ስርጭት በአሸባሪነት በመወንጀል  ስርጭቱን እንዲታፈን ማድረጋቸውን በተለያዩ የመረጃ  ተቋማት  መዘገቡን ይታወሳል ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ የሚያደርገውን የመረጃ አፈና ከጊዜ ወደጊዜ እየቀጠለ በመምጣቱ  ብዙ የነጻ ጋዜጦችም ባሳለፍነው አመት መዘጋታቸው እርግጥ ነው ።በዚህ ሳምንት በተጀመረው  ዘመቻ ነጻነት በሚለው የመረጃ መለዋወጥ ሃሳብ ነጻነትን የሚያራምድ አቋም በሃገሪቱ እንዲያንሰራፋ በማለት በነጻነት ጋዜጣ አሳታሚዎች መጀመሩን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሰው ወቅታዊ መረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያኖችን የመረጃ ማእከሎችን ብቻ ሳይሆን ከግብጽ እና ከኢንዶኔዢያ እየታተመ በዌብሳይት መገናኛ ስርጭት ላይ የዋለውንም ቢኪማሳር የተሰኘውን ዌብሳይት መዝጋታቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን ዌብሳይት የሙስሊሞችን ወቅታዊ ጥያቄ በተከታታይ ሲዘግብ በመገኘቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታይ ማድረጋቸው ይታወቃል ሆኖም ግን ይህንን አስመልክቶ እና በስውድናውያን ጋዜጠኞች ጥያቄ እና መልስ ላይ ከፍተኛ ትኩረትን ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ያደረገው ይሄው ሚዲያ አሁንም ድብቁን ሚስጥር ከመናገር ወደኋላ አንልም ሲሉ ሃተታቸውን በትላንትናው እለት አስፍረዋል  በዚህም ዘገባ ተከፈተ ወይንም አየር ኦን የሚል ፎቶ በመለጠፍ ሪፖርታቸው በመገናኛው ሽፋን ላይ ያተኮረ ዘገባ አትተዋል። ሆኖም የአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የዚህ መረጃ ማእከል ለዘብተኛ ሆነው ሁሉንም የመረጃ ድርጅቶች ክፍት ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የህትመት ዋጋዎችን እና የደህንነት ሚንስቴር የግል ሚዲያዎችን ክትትላቸውን እንዲያቆሙ ያሳውቃሉ ተብሎ የሚጠበቁ ሰው መሆናቸውን እና የነጻነት አርአያ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታሉ ። ለዚህ ደግሞ ትልቅ እና ፈታኝ ስራ ይጠብቃቸዋል ።መረጃዎች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ይፈሳሉ አፈና ሁሉ ይቅር ይላል የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ።

ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው


ጣቱ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን የማይወድ እና የማያደንቅ ወጣት አዛውንት የለም ሆኖም ይህንን የሰርጉን ቀን አስመልክቶ ወዳጅ ዘመዶቹ ታላቅ የደስታ ቀናቸው ነበር ።በዛሬው እለት የተፈጸመው ይህ ሰርጉ ደማቅ ከመሆኑም በላይ ታሪክ የተሰራበት እለት መሆኑን ታዳሚዎቹ ገልጸዋል ።ብዙ አርቲስቶች የተሳተፉበት ይህ የሰርግ በአል የእርሱን ኩራትም ሆነው በሰርጉ እለት አሳይተውታል። ቴዲ አፍሮ ለውዱ ባለቤቱ እሱ ከመድረክ ላይ ሆኖ ሙሽሪት ከሚዜዎቿ ጋር ከመድረክ ስር እየጨፈረች ጸባየ ሰናይ የሚለውን ዘፈኑን አቀንቅኖላታል ።ከዚያም በላይ አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ የሚለውን ዘፈን ሲዘፍን ተሰምቷል በዚህም ዘፈን ላይ መድረክ ላይ በመውጣት የጋራ ዳንሳቸውን አሳይተዋል ።በመጨረሻም የሰርግ ዘፈን ሲዘፈን በታዳሚው ፊትለፊት እየተሳሳሙ የፍቅር ጉያቸውን በሞቀ ትንፋሻቸው አሙቀውታል ሌሎችም የሙዚቃ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከሰአት ማጠር የተነሳ ሃይልዬ ታደሰ እና ታምራት ደስታ ብቻ ሳይዘፍኑ ፕሮግራሙ ተጠናቆአል ።ይህ የቴዲ አለም ዛሬ ታላቅ ቀን ነበር ያሉት ታዳሚዎቹ ቴዲ ለዚህች አገር እና ለሙዚቃ ወዳጆቹ ብዙ መሰዋእትነትን ከፍሎአል አሁንም በዚህ ክብረ በአሉ ላይ ወዳጆቹ መንገዶችን ሞልተው ሞተር ሳይክል አሸከርካሪዎች በተለያዩ ሾዎች እያሳዩ ፍቅራቸውን ለግሰውታል አድናቆታቸውንም ቸረውታል ።ከዚያ በተለየ መልኩ ሻንበል እና ሰአሊ ለማ ጉያ አስደናቂ የሆነ ስጦታ ለቴዲ አፍሮ ቴዲ ስጦታ ያወረሱት ሲሆን ከስእሎቻቸው መሃል ለዚህ ለሰርጉ ቀን ተብሎ የተሳለ የአጼ ቴዎድሮስን ስእል ከአንበሳ ጋር ያለበትን ታላቅ ስጦታ ሲያበረክቱለት የህዝቡ ስሜት ታላቅ ነበር ብለዋል ።በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሱት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በዚህ ስጦታ ላይ ተዲ ሳቅ እና ለቅሶ  ሲታይበት ሰአሊውን አቅፎ ለረጂም ሰአት ስሟቸዋል። ኢዮብ መኮንን (ብረባም ባልረባም ትወጂኛለሽን) ሲያቀነቅን ጎሳዬ ተስፋዬ ከራሱ ዘፈኖች እና ከቴዲ ዘፈን ዘፍኖአል ሸዋንዳኝ የቀረብኝ የለም ሲል አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ ብሏል ታደለ ገመቹ ኦሮምኛ ሲያዘም ግርማ ካሳ ፣ተሾመ ወልዴ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፣ዳግማዊ አሊ ፣ሳምሶን ጃፋር ፣ፋሲል ውሂብ፣አሸናፊ አሊ ፣አቡጊዳ ባንድ ፣ኤክስፕረስ ባንድ፣ ክብረት ዘኪዎስ ፣ታምራት ሃይሉ (ቁም ነገር መጽሄት) :ታምራት ደስታ
እና ሃይልዬ ታደሰ የመድረኩ አጋፋሪዎች ነበሩ ።ከላይ እንደጠቀስነው በፕሮግራሙ መጣበብ ምክንያት ሃይልዬ እና ታምራት ብቻ ሳይዘፍኑ የሰርጉ ሁኔታ ተጠናቆአል።ሁሉም አርቲስቶች በጣም ተደናቂ የሆኑትን እና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ዘፈኖቻቸውን አቅርበዋል።
በዚህ የክቡር ቀን ለአካል ጉዳተኞች የአንድ መቶ ሺህ ብር በብሄራዊ ቴአትር ጋር ማስረከቡን ይበልጥ ኩራት ለህዝቡ ሆኖታል ፣የአካል ጉዳተኞችም ደስታቸውን እና የሰርጉን ድምቀት ሆነውት አልፈዋል ።
ማለዳ ታይምስ

ልጆቻቸውና “ቀዳማዊ እመቤቶቻችን” – ከሮቤል ሔኖክ


ልጆቻቸውና “ቀዳማዊ እመቤቶቻችን” – ከሮቤል ሔኖክ

(በዲዛይኑ ላይ የተጻፈው የማይነበብ ከሆነ በሚል ስጋት ከታች በጽሁፍ አቅርበነዋልና ያንብቡት።)
ከሮቤል ሔኖክ (ምንጭ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 43)
ስልጣን expired date ይኑረው ብሎ ነበር በ እውቀቱ ስዩም በአንድ ትረካው ላይ። የመለስ የስልጣን expired date በፍቃድ ላይ የተመሰረት አልነበረም። በእግዚአብሔር ጥሪ እንጂ። ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ ጃዋር መሀመድ እንዳለው “ኢትዮጵያ ቢያንስ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት ተሳዳቢ ጠ/ሚ/ር አይኖራትም”። ከአቶ መለስ ሞት በኋላ የመጣውን ለውጥ እንዲህ በቀላሉ አንመለከተውም። ለውጡ በብዙ መልኩ ነው። ከነዚም መካከል የመሪዎቻችን ቤተሰቦች ይጠቀሳሉ። እኛ እናሳይዎ – እርሶ ደግሞ ለውጡን በመቁጠር ያግዙን።
ሰምሃል
መለስ ዜናዊ
ውጭ ሃገር የምትማረው የቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ መለስዝ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰምሃል መለስ እንደምታይዋት ሽጉጥ ይዛ ነው። በ እረፍት ጊዜዋ ወደ ጦር ካምፖች በመሄድ መሳሪያ መተኮስ ስትለማመድ የተለያዩ ፎቶ ግራፎች በተለያዩ ጊዜያት ወጥተው እንደነበር እናስታውሳለን።

Tuesday, 25 September 2012

“ወደ ፍቅር” የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በጥቅምት ይካሔዳል


“ወደ ፍቅር” የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በጥቅምት ይካሔዳል
September 23, 2012   ·

በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕረፍት ምክንያት ድንገተኛ ሞት ተሰርዞ የነበረው የድምፃዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ጥቅምት 3 ቀን 2005 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ሊካሔድ ነው፡፡

ኮንሰርቱን ለማከናወን ታስቦ የነበረው በአዲስ ዓመት ዋዜማ ቢሆንም፣ ወዲያውም ተሰርዞ ላልተወሰነ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በመጨረሻም ቀን ሊቆረጥ ችሏል፡፡

ቴዲ መጨረሻ ላይ ካወጣው ጥቁር ሰው አልበሙ በኋላ የሚደረገው ይኼ ኮንሰርት ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመርያው ይሆናል፡፡ አርቲስቱ ከዚህ አልበም መውጣት በኋላ በእንግሊዝ ኮንሰርት አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ታዳሚዎችም እንደተገኙበትም ለመረዳት ተችሏል፡፡

“ወደ ፍቅር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ኮንሰርቱ 15‚000 ያህል ታዳሚዎችም ዝግጅቱን እንደሚከታተሉ አዘጋጆቹ ይጠብቃሉ፡፡ ቴዲ አፍሮ በአቡጊዳ ባንድ አጃቢነትም ምሽቱን እንደሚያደምቀው ይጠበቃል፡፡ የኮንሰርቱ የቲኬት ሽያጭ መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ይጀምራል፡፡ የቲኬቱም ዋጋ 400 ብር ሲሆን ቪአይፒም 800 ብር ነው፡፡ የቲኬቱ ሽያጭም ከዝግጅቱ በፊት እንደሚያልቅ አዘጋጆቹ ይናገራሉ፡፡

አቶ አሸናፊ ዘለቀ የአዲካ ኢቨንትስና ኮሚዩኒኬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሚዋብበት ዲዛይን የአልበሙን (ጥቁር ሰው) ጭብጥ የያዘ ነው፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ ቴዲ ጥቁር ሰው ከሚለው አልበሙ የሚዘፍን ሲሆን ከዚህ ቀደም ከወጡት አልበሞች የተወሰኑ ዘፈኖችንም እንደሚዘፍን ይጠበቃል፡፡ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ይኼ ዝግጅት ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል፡፡

ተደናቂነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴዲ አፍሮ አራት አልበሞች ያሉት ሲሆን፣ ጥቁር ሰው በተባለው የመጨረሻው አልበሙ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ አዲስ የሽያጭ ሬኮርድ ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ቴዲ አፍሮ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የራሱ ኮንሰርት ያልነበረው ሲሆን፣ አንዳንድ ኮንሰርቶች ላይ ግን እንግዳ በመሆን ዘፍኗል፡፡ ይሔ ኮንሰርት በጉጉት መድረክ ላይ ሊያዩት የሚጠብቁትን አድናቂዎቹን አንድ ላይ እንደሚያገናኝ ይጠበቃል፡







የቀድሞዋ እመቤትወ/ሮ አዜብ ቤተ መንግስቱን የሙጥኝ እንዳሉት ነው።


በፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አልተገኙም ነበር
September 25, 2012   ·


(ኢ.ኤም.ኤፍ) በየትኛውም አገር አንድ መንግስት ሲቀየር አዲስ የሚመረጠው አካል፤ ወደ አስተዳደር ቢሮው መግባት ይኖርበታል። በራሺያ የክሬምሊን ቤተ መንግስት ወይም በአሜሪካ ኋይት ሃውስ የመንግስት መቀመጫ ስፍራዎች ናቸው።  ለኢትዮጵያ ደግሞ የመንግስት ስራ ማከናወኛ የአራት ኪሎው ምኒልክ ቤተ መንግስት መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ በሌሎች አገራት የመንግስት ለውጥ ሲደረግ፤ ፕሬዘዳንቱም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጨዋ ደንብ ጨርቅ እና ማቃቸውን ይዘው ይወጣሉ። በኢትዮጵያ ግን ይህ አልሆነም። የቀድሞዋ እመቤት ቤተ መንግስቱን የሙጥኝ እንዳሉት ነው።

አቶ ኃይለማርያም ምኒልክን ቤተ መንግስት ከሩቅ ከማየት ውጪ ከነቤተሰባቸው ወደ ቅጥር ግቢው አልተዛወሩም። ሌላው ቀርቶ በትላንትናው እለት የሁለቱን ሱዳኖች ልዑካን ተቀብለው ያነጋገሩት፤ ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሚገኙበት ኢዮቤልዩ ቤተ መንግስት ውስጥ ነበር። ከዚህ በፊት በመለስ ዜናዊ ይደረጉ የነበሩ የእንግዳ አቀባበል ስርአቶች ይፈጸሙ የነበረው በአራት ኪሎው ምኒልክ ቤተ መንግስት ሲሆን፤ አሁን ግን ሴትዮዋ አልወጣም በማለቷ ምክንያት… አቶ ኃይለማርያም ፕሬዘዳንቱ የሚገኙበትን ቤተመንግስት በጋራ ለመጠቀም ተገደዋል።

‹‹መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብዬ አልፈርምም፣ እናንተ ብትስማሙም እኔ አላስፈጽምም›› አቶ አያሌው ጎበዜ



September 25, 2012   ·  


‹‹መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብዬ አልፈርምም፣ እናንተ ብትስማሙም እኔ አላስፈጽምም›› አቶ አያሌው ጎበዜ
 በ1999 ዓ.ም በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ተነስቶ የነበረውን የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ተከትሎ የተወሰኑ መሬቶችን ከጎንደር ላይ በመውሰድ ለሱዳን ለመስጠት በተደረገው ስምምነት ላይ ፊረማቸውን እንዲያኖሩ የተጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ በእምቢተኝነት ሲፀኑ በወቅቱ ምክትላቸው የነበሩት የአሁኑ አዲሱ ተሿሚ ም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል፡፡
አቶ አያሌው ጎበዜ በወቅቱ ‹‹መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብዬ አልፈርምም፣ እናንተ ብትስማሙም እኔ አላስፈጽምም›› በማለታቸው አቶ በረከትን ጨምሮ የብአዴን አመራሮች ተበሳጭተውባቸው ነበር።
አቶ አያሌው ጎበዜ በችሎታና በልምድ ከአቶ ደመቀ መኮንን የተሻሉ ቢሆኑም፣ አቶ በረከት አቶ አያሌው ” በሱዳን ድንበር ላይ ባሳዩት አቋም” ቂም በመያዝ በእርሳቸው ስር ሆነው ሲሰሩ የነበሩትን አቶ ደመቀን ወደ ፊት በማምጣት አቶ አያሌውን እንደተበቀሉዋቸው ታውቋል። አቶ አያሌው አቶ በረከት እንደፈለጉ የሚያሽከረክሩዋቸው ሰው አለመሆናቸው ለከፍተኛው ስልጣን እንዳይታጩ እንዳደረጋቸው የውስጥ ምንጮች ገልጠዋል።
አቶ መለስ ” ምንም ይሁን ምን አቋም ያለው ሰው ይሻላል” በማለት አቶ አያሌው ጎበዜ በስልጣን እንዲቆዩ የተከራከሩላቸው፣ በእነ አቶ በረከት በኩል የሚታየውን የመሰባሰብ እንቅስቃሴ ለመከፋፈል እንዲመቻቸው እንደነበር ታውቋል።
አቶ መለስ የአማራ ክልልን ለሁለተኛ ጊዜ በፕሬዝዳንትነት በመምራት ላይ የሚገኙትን አቶ አያሌው ጎበዜን ከስልጣን እንዳይወርዱ ታድገዋቸው እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለጸዋል፡፡
 አቶ መለስ ‹‹እዚህ ተቋም ላይ ከሰበሰብካቸው ሰዎች ይልቅ ያ የግል ጋዜጣ የሚያዘጋጀው ልጅ የበለጠ ኮሚትመንት አለው፣ እሱ የሚሰራውን ያውቃል፣ ያንተ ሰራተኞች የሚሰሩትን አያውቁም›› በማለት አቶ በረከትን ወርፈዋቸው ነበር ።
 የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት ኢህአዴግ በፕሮፖጋንዳው መስክ ለደረሰበት ኪሳራ አቶ መለስ አቶ በረከትን ተጠያቂ አድርገው ነበር።
በአንድ የግንባሩ ስብሰባ ላይ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሠራተኞች ብቃት ማነስ የተበሳጩት አቶ መለስ ‹‹እዚህ ተቋም ላይ ከሰበሰብካቸው ሰዎች ይልቅ ያ የግል ጋዜጣ የሚያዘጋጀው ልጅ የበለጠ

ኮሚትመንት አለው፣ እሱ የሚሰራውን ያውቃል፣ ያንተ ሰራተኞች የሚሰሩትን አያውቁም›› በማለት አቶ በረከትን ወርፈዋቸው ነበር ።
አቶ መለስ ስም ሳይገልጹ በደፈናው ‹‹አንድ ጋዜጠኛ›› ሲሉ ማነፃጸሪያ ያደረጉት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነው በማለት ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
በኢህአዴግ ባለሥልጣኖች ዘንድ አቶ መለስ ዜናዊ በግምገማ እና ስብሰባ ወቅት የኮሙኒኬሽን መሥሪያ ቤትን አይተቹም እየተባሉ ይታሙ የነበረ ሲሆን ከላይ የተገለጸውን ትችት ያቀረቡትም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደነበር ምንጮቻችን አስረግጠው ገልጸዋል፡፡
አቶ መለስ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚንስትር ማዕረግ የሚመሩትን አቶ በረከት ስምዖንን ከሌሎች ሚንስትሮቻቸው እና የፓርቲያቸው አመራሮች የበለጠ እንደሚያቀርቧቸው ይታወቃል፡፡  (ምንሊክ ሳልሳዊ)









ከዚህ በኋላ በሕይወት ብኖር ባልኖር ከልጆቼ በቀር የምቆጭበት ነገር አይኖርም


 – ታማኝ በየነ (አዲስ ቃለምልል

(ዘ-ሐበሻ) “ሰው ወደ ሀገሩ ሲገባ እፎይ ይላል እንጂ ከሃገሩ ሲወጣ እንዴት እፎይ ይላል?” ነበር ያለው ዝነኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ ከመለስ ሞት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገው ሰፊ ቃለ ምልልስ። አንድ ሰዓት ከአስራ ሦስት ደቂቃ የፈጀ ቃለ ምልልስ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በኢሳት ቴሌቭዥን አድርጓል። በቃለ ምልልሱ ወደ አውስትራሊያ ሲሄድ በወቅቱ አቶ መለስ መሞታቸው በመንግስት ሚዲያ የተገለጸበት ዕለት ነበርና ወደዚያ ሲሄድ “ከጥሩ ዜና ጋር እመለሳለሁ” ያለው ከርሳቸው ሞት ጋር እንደማይገናኝ ተናግሯል። “ከዚህ በኋላ በሕይወት ብኖር ባልኖር ከልጆቼ በቀር የምቆጭበት ነገር አይኖርም” ሲል ታማኝ የተናገረበትን ቃለ ምልልስ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አንባቢዎችም ይድረሳቸው በሚል አምጥተነዋል። ይቋደሱት።




Sunday, 23 September 2012

የቴዲ አፍሮ ሰርግ ለምን ባልተመለደ መልኩ ሐሙስ ቀን እንዲሆን መወሰኑን ያውቁ ኖሩዋል




የቴዲ አፍሮ ሰርግ ለምን ሐሙስ ቀን እንዲሆን ተወሰ? (ያውቁ ኖሩዋል?)
የቴዲ አፍሮ ሰርግ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚደረግ ዘ-ሐበሻ መዘገቡዋ ይታወሳል:: የቴዲ ሰርግ የፊታችን ሐሙስ በሒልተን ሆቴል ሲደረግ 1000 ሺህ ሰዎች የሰርግ ካርድ ተልኮላቸዋል:: ለሰርጌ በሚል የዛሬ 5 ዐመት የሰራውና ለሰርጌ ቀን ብሎ ያስቀመጠው የሰርግ ዘፈን በዚሁ ቀን ይደመጣል:: ይህ ዘፈን ዛሬ በአዲስ አበባ ለአድማጭ መልቀቁ ለዘ-ሐበሻ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
ከዚህ ውጭ የቴዲ አፍሮ ሰርግ ባልተለመደ መልኩ ለምን ሐሙስ ቀን እንዲሆን መወሰኑን የቅርብ ምንጮች ለዘሐበሻ መረጃውን አድርሰዋል::
መስከረም 17 እና ቴዲ ብዙ ታሪክ አላቸው:-
1ኛ. የመስቀል በዐል ስለሆነ
2ኛ. አባቱ የተቀበረበት ዕለት ስለሆነ
3ኛ. የቴዲ እናት ልደት ነው
4ኛ. የእውቁ ድምጻዊ የዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ልደት ስለሆነ ነው::
ከቴዲ ሚዜዎች መካከል ሸዋንዳኝ ሀይሉ; የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ቴዲ ባሪያው; ሀይልዬ ታደሰና የእውቋ ሞዴል ሊያ ከበደ ወንድም ኤርሚያስ ከበደ ይገኙበታል:: በአጠቃላይ ከቴዲ በኩል ሰባት; በሚስቱም በኩል 7 ሚዜዎች ይኖሩዋቸዋል:: ከአምለሰት ሚዜዎች መካከል የኤፍሬም ታምሩ ልጅ ቤዛ ኤፍሬም ታምሩ እንደምትገኝበት የዘ-ሐበሻ ምንጮች መረጃውን አድርሰውናል::
የቴዲ የሰርግ ዘፈን ደርሶናል፤ ቀጥሎ ይቀርባል።