"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 25 September 2012

“ወደ ፍቅር” የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በጥቅምት ይካሔዳል


“ወደ ፍቅር” የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በጥቅምት ይካሔዳል
September 23, 2012   ·

በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕረፍት ምክንያት ድንገተኛ ሞት ተሰርዞ የነበረው የድምፃዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ጥቅምት 3 ቀን 2005 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ሊካሔድ ነው፡፡

ኮንሰርቱን ለማከናወን ታስቦ የነበረው በአዲስ ዓመት ዋዜማ ቢሆንም፣ ወዲያውም ተሰርዞ ላልተወሰነ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በመጨረሻም ቀን ሊቆረጥ ችሏል፡፡

ቴዲ መጨረሻ ላይ ካወጣው ጥቁር ሰው አልበሙ በኋላ የሚደረገው ይኼ ኮንሰርት ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመርያው ይሆናል፡፡ አርቲስቱ ከዚህ አልበም መውጣት በኋላ በእንግሊዝ ኮንሰርት አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ታዳሚዎችም እንደተገኙበትም ለመረዳት ተችሏል፡፡

“ወደ ፍቅር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ኮንሰርቱ 15‚000 ያህል ታዳሚዎችም ዝግጅቱን እንደሚከታተሉ አዘጋጆቹ ይጠብቃሉ፡፡ ቴዲ አፍሮ በአቡጊዳ ባንድ አጃቢነትም ምሽቱን እንደሚያደምቀው ይጠበቃል፡፡ የኮንሰርቱ የቲኬት ሽያጭ መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ይጀምራል፡፡ የቲኬቱም ዋጋ 400 ብር ሲሆን ቪአይፒም 800 ብር ነው፡፡ የቲኬቱ ሽያጭም ከዝግጅቱ በፊት እንደሚያልቅ አዘጋጆቹ ይናገራሉ፡፡

አቶ አሸናፊ ዘለቀ የአዲካ ኢቨንትስና ኮሚዩኒኬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሚዋብበት ዲዛይን የአልበሙን (ጥቁር ሰው) ጭብጥ የያዘ ነው፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ ቴዲ ጥቁር ሰው ከሚለው አልበሙ የሚዘፍን ሲሆን ከዚህ ቀደም ከወጡት አልበሞች የተወሰኑ ዘፈኖችንም እንደሚዘፍን ይጠበቃል፡፡ አዘጋጆቹ እንደገለጹት ይኼ ዝግጅት ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል፡፡

ተደናቂነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴዲ አፍሮ አራት አልበሞች ያሉት ሲሆን፣ ጥቁር ሰው በተባለው የመጨረሻው አልበሙ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ አዲስ የሽያጭ ሬኮርድ ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ቴዲ አፍሮ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የራሱ ኮንሰርት ያልነበረው ሲሆን፣ አንዳንድ ኮንሰርቶች ላይ ግን እንግዳ በመሆን ዘፍኗል፡፡ ይሔ ኮንሰርት በጉጉት መድረክ ላይ ሊያዩት የሚጠብቁትን አድናቂዎቹን አንድ ላይ እንደሚያገናኝ ይጠበቃል፡







No comments:

Post a Comment