"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 28 September 2012

ልጆቻቸውና “ቀዳማዊ እመቤቶቻችን” – ከሮቤል ሔኖክ


ልጆቻቸውና “ቀዳማዊ እመቤቶቻችን” – ከሮቤል ሔኖክ

(በዲዛይኑ ላይ የተጻፈው የማይነበብ ከሆነ በሚል ስጋት ከታች በጽሁፍ አቅርበነዋልና ያንብቡት።)
ከሮቤል ሔኖክ (ምንጭ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 43)
ስልጣን expired date ይኑረው ብሎ ነበር በ እውቀቱ ስዩም በአንድ ትረካው ላይ። የመለስ የስልጣን expired date በፍቃድ ላይ የተመሰረት አልነበረም። በእግዚአብሔር ጥሪ እንጂ። ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ ጃዋር መሀመድ እንዳለው “ኢትዮጵያ ቢያንስ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት ተሳዳቢ ጠ/ሚ/ር አይኖራትም”። ከአቶ መለስ ሞት በኋላ የመጣውን ለውጥ እንዲህ በቀላሉ አንመለከተውም። ለውጡ በብዙ መልኩ ነው። ከነዚም መካከል የመሪዎቻችን ቤተሰቦች ይጠቀሳሉ። እኛ እናሳይዎ – እርሶ ደግሞ ለውጡን በመቁጠር ያግዙን።
ሰምሃል
መለስ ዜናዊ
ውጭ ሃገር የምትማረው የቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ መለስዝ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰምሃል መለስ እንደምታይዋት ሽጉጥ ይዛ ነው። በ እረፍት ጊዜዋ ወደ ጦር ካምፖች በመሄድ መሳሪያ መተኮስ ስትለማመድ የተለያዩ ፎቶ ግራፎች በተለያዩ ጊዜያት ወጥተው እንደነበር እናስታውሳለን።

ዮሀና
ኃይለማርያም ደሳለኝ

ኢትዮጵያ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ውስጥ የምትማረው የጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ልጅ ዮሃና 22 ዓመቷ ነው። ይህች ወጣት በትርፍ ጊዜዋ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ የባለስልጣን ልጅ ነኝ የሚል ስሜት ሳይሰማት ሰዎች የበሉበትን ሰሃን እና ኩባያዎችን ሁሉ በማጠብ ለእግዚአብሄር ያላትን ታዛዥነት ታሳያለች።
“ቀዳማዊት እመቤቶቻችን”
ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ
 (የኃይለማርያም ባለቤት)
በፎቶ ግራፉ ላይ የምታዩዋት አዲሷን ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬን ነው። ወ/ሮ ሮማን በኢኮኖሚክስ እና በሊደርሺፕ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ አላት። በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ፣ በሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በከፍተኛ ኃላፊነት የሰራችው ሮማን በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ኅብረት ውስጥ ትሰራለች ተብሏል። በወላይታ የተወለደችው ወ/ሮ ሮማን ከአቶ ኃይለማርያም አብራክ ሦስት ሴት ልጆችን ወልዳለች።S
 ወ/ሮ አዜብ መስፍን
(የመለስ ባለቤት)
ክልላቸውን ለጋብቻቸው ሲሉ የቀየሩት (የተወለዱበት ወልቃይት ወደ ትግራይ ክልል መካለሉን ልብ ይሏል) አዜብ መስፍን (ጎላ) ከአቶ መለስ ሌላ ከቀድሞው የደህንነት ሚ/ር ክንፈ ገ/መድህን አንድ ልጅ አላቸው። ከወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር የሚያመሳስላቸው 3 ልጆችን ወልደዋል። ወ/ሮ አዜብ ከበርሃ ድረስ ከባለቤታቸው አቶ መለስ ጋር ተዋግተው የመጡ ሲሆን ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በመግባት ተምረዋል። የሕወሓት ትልልቅ የንግድ ድርጅቶችን ከላይ ሆነው ይመራሉ። በአፍሪካ የሴቶች እና የኤች አይቪ ጉዳዮች ላይ ተሳትፈዋል። ወልቃይት የተወለዱት ወ/ሮ አዜብ የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ  በአዋሳ ቤተመንግስት ግንባታ ላይ በተሰራው ሙስና ክስ ሲቀርብባቸው ወንጀሉን የሰሩት በወ/ሮ አዜብ  ትዕዛዝ መሆኑን ማጋለጣቸው ይታወሳል።S 

No comments:

Post a Comment