"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 25 September 2012

‹‹መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብዬ አልፈርምም፣ እናንተ ብትስማሙም እኔ አላስፈጽምም›› አቶ አያሌው ጎበዜ



September 25, 2012   ·  


‹‹መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብዬ አልፈርምም፣ እናንተ ብትስማሙም እኔ አላስፈጽምም›› አቶ አያሌው ጎበዜ
 በ1999 ዓ.ም በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ተነስቶ የነበረውን የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ተከትሎ የተወሰኑ መሬቶችን ከጎንደር ላይ በመውሰድ ለሱዳን ለመስጠት በተደረገው ስምምነት ላይ ፊረማቸውን እንዲያኖሩ የተጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ በእምቢተኝነት ሲፀኑ በወቅቱ ምክትላቸው የነበሩት የአሁኑ አዲሱ ተሿሚ ም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል፡፡
አቶ አያሌው ጎበዜ በወቅቱ ‹‹መሬት ለሱዳን ይሰጥ ብዬ አልፈርምም፣ እናንተ ብትስማሙም እኔ አላስፈጽምም›› በማለታቸው አቶ በረከትን ጨምሮ የብአዴን አመራሮች ተበሳጭተውባቸው ነበር።
አቶ አያሌው ጎበዜ በችሎታና በልምድ ከአቶ ደመቀ መኮንን የተሻሉ ቢሆኑም፣ አቶ በረከት አቶ አያሌው ” በሱዳን ድንበር ላይ ባሳዩት አቋም” ቂም በመያዝ በእርሳቸው ስር ሆነው ሲሰሩ የነበሩትን አቶ ደመቀን ወደ ፊት በማምጣት አቶ አያሌውን እንደተበቀሉዋቸው ታውቋል። አቶ አያሌው አቶ በረከት እንደፈለጉ የሚያሽከረክሩዋቸው ሰው አለመሆናቸው ለከፍተኛው ስልጣን እንዳይታጩ እንዳደረጋቸው የውስጥ ምንጮች ገልጠዋል።
አቶ መለስ ” ምንም ይሁን ምን አቋም ያለው ሰው ይሻላል” በማለት አቶ አያሌው ጎበዜ በስልጣን እንዲቆዩ የተከራከሩላቸው፣ በእነ አቶ በረከት በኩል የሚታየውን የመሰባሰብ እንቅስቃሴ ለመከፋፈል እንዲመቻቸው እንደነበር ታውቋል።
አቶ መለስ የአማራ ክልልን ለሁለተኛ ጊዜ በፕሬዝዳንትነት በመምራት ላይ የሚገኙትን አቶ አያሌው ጎበዜን ከስልጣን እንዳይወርዱ ታድገዋቸው እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለጸዋል፡፡
 አቶ መለስ ‹‹እዚህ ተቋም ላይ ከሰበሰብካቸው ሰዎች ይልቅ ያ የግል ጋዜጣ የሚያዘጋጀው ልጅ የበለጠ ኮሚትመንት አለው፣ እሱ የሚሰራውን ያውቃል፣ ያንተ ሰራተኞች የሚሰሩትን አያውቁም›› በማለት አቶ በረከትን ወርፈዋቸው ነበር ።
 የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት ኢህአዴግ በፕሮፖጋንዳው መስክ ለደረሰበት ኪሳራ አቶ መለስ አቶ በረከትን ተጠያቂ አድርገው ነበር።
በአንድ የግንባሩ ስብሰባ ላይ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሠራተኞች ብቃት ማነስ የተበሳጩት አቶ መለስ ‹‹እዚህ ተቋም ላይ ከሰበሰብካቸው ሰዎች ይልቅ ያ የግል ጋዜጣ የሚያዘጋጀው ልጅ የበለጠ

ኮሚትመንት አለው፣ እሱ የሚሰራውን ያውቃል፣ ያንተ ሰራተኞች የሚሰሩትን አያውቁም›› በማለት አቶ በረከትን ወርፈዋቸው ነበር ።
አቶ መለስ ስም ሳይገልጹ በደፈናው ‹‹አንድ ጋዜጠኛ›› ሲሉ ማነፃጸሪያ ያደረጉት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነው በማለት ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
በኢህአዴግ ባለሥልጣኖች ዘንድ አቶ መለስ ዜናዊ በግምገማ እና ስብሰባ ወቅት የኮሙኒኬሽን መሥሪያ ቤትን አይተቹም እየተባሉ ይታሙ የነበረ ሲሆን ከላይ የተገለጸውን ትችት ያቀረቡትም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደነበር ምንጮቻችን አስረግጠው ገልጸዋል፡፡
አቶ መለስ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚንስትር ማዕረግ የሚመሩትን አቶ በረከት ስምዖንን ከሌሎች ሚንስትሮቻቸው እና የፓርቲያቸው አመራሮች የበለጠ እንደሚያቀርቧቸው ይታወቃል፡፡  (ምንሊክ ሳልሳዊ)









No comments:

Post a Comment