"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 22 April 2012

     ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲያዜም ኢትዮጵያ ትከበራለች 

  አበሻ አንገቱን በሀዘን በሚደፋበት ወቅት ብቅ የሚሉ ፈርጦች አሉ፣ እንባችንን አብሰን ሀዘናችንን ተወት አድርገን ቀና እንድል

የሚያደርጉን ። ከትንሳዔው በዐል ጋር የሞራል ትንሳዔ የሚሰጥ ውብ ዘፈን ከጥግ አስከ ጥግ ድረስ ተሰማ። ብላቴናው ጥበብ ከላይ

ይፈስለታል። አመስግኖ ይቀበልና ቤት እያስመታ ይገጥማል፤ የገጠመውን ደግሞ ወደ ዜማ ይቀይርና ሰው መሆኑን እስክንረሳ ድረስ

በደስታ ያስጨፍረናል። ለዚህ ነበር ከዚህ ቀደም የቴዲ ዜማዎች ጥላቻን የሚያከስሙ የፍቅር ቅመሞች ናቸው ብዬ የመሰከርኩለት

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/1627 በዚያን ጊዜ ከትንሿ እስር ቤት ውስጥ ነበር።
የሰሞኑ ነፋስ ደግ አልነበረም የሀዘን ድባብ አጥልቶብን ነበር። ቅስም ለመስበር የተባበሩ የሚመስሉ የክፋት ሀይሎች ሸቃባነታቸው
ከፍቶብን ነበር። መስጊዱ በጸጉረ ልውጥና ተንኮል ተንኮል በሚሸት የቀኖና መስመር አንሄድም በሚሉ የእስልምና ሀይማኖትተከታዮችጩኸት ተሸብሯል። አላሁ አክበር ሲሉ ደመና እየሰነጠቀ ጩሀታቸውን አሞራም የተቀበለው ይመስላል። አሸባሪ ነህ ካልከኝ አዎን
አሸብረሃለሁ ላንተ መሰሪነት ስል ከኢትዮጵያዊነት ግን አላንስም የሚለው መሀላ በአላሁ አክበር ሲታጀብ ክርሰትያኖችም የወገኖቻቸው
ጩኸት ተሰምቷቸው በልባቸው ከነርሱ ጋር መሆናቸው እውነት ነው። ይሁን እንጂ እነርሱም ፋታ አላገኙም። ደብር አፍርሰው ለነዳጅ
የሚሆኑ እጽዋትን በስኳር ስም ሊያመርቱ ትራክተሩን እያስጓሩባቸው በጭንቀት ላይ ናቸው
። መስቀላቸውን ደረታቸው ላይ ይዘው
በጠላት ጥይት የተደበደቡት አቡነ ጴጥሮስና ስማቸውን የኢትዮጵያ አፈር ብቻ የምታስታውሳቸውን ያልተጠሩ ጀግኖችን እያሰቡ ከነርሱ
አንዱን ሆኖ ወደ ጌታ መሄዱን በመምረጥ ላይ ናቸው፣ ደግሞ ያደርጉታል። ሰይጣን በሰው ተመስሎ እንጂ ራሱ እንደማይመጣ ሁሉ
መለስና ጀሌዎቹ ስምና መልካቸውን የተጋሩ ሰይጣኖች እንደሆኑ አሁን በደንብ አውቀውታል። ደብር ፈርሶ ብህትናስ እንዴት ይኖራል? 
ክርስትያኑስ ከዚህ ወዲያ ምን እስክንሆን እንጠብቃለን ባሉበት ሰዐት ነው ቴዲ ከዳር እስከዳር የሚሰማ ውብ የጥበብ ውጤቱን
እንካችሁ ያለን።
ከደርግ የባሰ አይመጣም ብለው መንገድ መርተው ያመጡ አማራና ኦሮሞዎች ዛሬን ከጠላት ተቆጥረው ከመንደራቸውና ከሀገራቸው
እየተፈናቀሉ መበተናቸው አብልጦ ባሳዘነን በዚህ መጥፎ ጊዜ፤ መለስና አጋሮቹ አይናቸው እያየ የራሳቸውን መቃብር ራቅ አድርገው
ሲቆፍሩ እያዘንን በምንተክዝበት ጊዜ ነው ብላቴናው ጥቁሩን ሰው ያበረከተልን። ይቺ አገር ቀና የማለት ተስፋዋን በእጃችን ይዘናል
ለሚሉ የኢትዮጵያ ልጆች ብርታት ይሆናል።
ታድያ ደግሞ ቴዲ ወጣት ልጅ ነውና ቃል ገደፈ ብለን ጣርያ ልንነካም አያስፈልግም። የታሪክ ተመራማሪ አይደለም፣ ስነግጥም ደግሞ
ባህር ነው ብለናልና ገጣሚው መንፈሱን ሲቃትት ሃሳብ ቢያሳስት እንጂ ቃል ቢስት አጎደለ ብለን ዋናውን ፍሬውን አንጠየፍም።
አድራሻ አለውና ይቺን አርማት ወይም አመሳክራት ብሎ በግሉ መላክም መንገርም ይቻላል። በትኩሱ ማርከሱ ደግ ላይሆን ይችላል።
ደግሞም በ10 መስመር ግጥም የምዕተ አመት ታሪክ ማስነጠብ ቀላልም አይደለም። ግጥም ለሚገባው ሰው ባልቻ አባቱ ነፍሶ ስላለ
የፈረሱን ስም ለአባቱ ሰጠ የሚል አይኖርም ለታሪክ ባዳ ካልሆነ በቀር። የዚያኑ ያህል ደግሞ ተራርሞ መሄድና መማማር ሊያስፈራ
አይገባውም። እሱን ይዞ ዋናውን ነገር ለመርሳት የጫጫታ ምንጭ እንዳይሆን ማድረጉ ተገቢ ነው። በሚኒሊክ ዘመን በሆነው ጉዳይ
ላይ የዛሬዎቹን ባለሀውልቶች ደባልቆ ቢሆን ኖሮ ዘመናትና ታሪክ አሳክረሀል ልንለው እንችል ነበር። ሌላው በዘዴ የሚነገር ነው።
በሁዳዴና የተራበ ወገን ሆዱ የእህል ያለህ እያለ በሚጮህበት በዚህ ወደን ከጾምንበት ተገደን ወደ ም’ንራብበት ጊዜ ስንሸጋገር ለፋሲካ
ዶሮ መብላት ቢያቅታችሁ ተስፋን ተመገቡ ብሎ ቴዲ ሲያዜም የእግዜር መንፈስ የላከው የሚመስለን የዋሆች አበጀህ ብለነዋል። ሰው
ከሃገሩ እየተገፋ በሀገሩም በረሀብና በበሽታ እያለቀ የሚላስ የሚቀመስ ባጣበት ጊዜ ከማሳው ላይ አትክልትና ፍራፈሬ እየተጫነ ከብቱ
እየተጋዘ የአረብ ባለጸጋ ሲመግብ፣ የአበሻ ልጆች በባርነት የኛኑ ስጋና ጎመን በልቶ ለጠገበ የሴሰኛ አረብ የወሲብ መፈንጫ በሆኑበት
በዚህ ክፉ ሰዐት፤ የሀገሪቱ ምርጥ ልጆች እግርተወርች ታስረው በየእስርቤቱ በተጣሉበት በዚህ ሞት ሞት በሚሸት ሰዐት መንፈስ
የሚያነቃ ነገር መስማት ታላቅ ነገር ነው። ከምችለው በላይ ከሚገባሽ በታች ሲል ስርስር አድርጎ የሚገባ መጽሀፍ የሚወጣው ትልቅ
ሀሳብ ነው በአንዲት ስንኝ የቋጠረው።ለዚህ ነው ቴወድሮስ ካሳሁን ሲያዜም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ይከብራሉ ማለት አለቅጥ
ማገዘፍ የማይሆነው።
ለመተቸት የሚቸኩሉ አንደበቶች ታቅበው ግጥም ባህር ነውና  ካንድ ጫፍ የቀዱ በሌላኛው ጫፍ ያለውን ላያውቁ እንደሚችሉ
አውቀው ከትችታቸው ቆጠብ ካንደበታቸው ሰብሰብ ሲሉ ነው ከመልዕክቱ ጋር መጣጣም የሚችሉ። ደስ የሚል ስቃይ ውብ ነው።
ደግሞ ደጋግሞ መውደድና ዛሬም ባማረ መልኩ ባይገርምሽ አሁንም እወድሻለሁ ማለት ከትናንት ያለመሻል ማለት አይደለም። ጥልቅ
ነው ጠልቆ መቅዳት ለሚችሉ ልባሞችና ዛሬን ለዚህች ሀገር ደግመው ደጋግመው መከራን እየተቀበሉ ላንቺ ከሆን ይሁን ለሚሉቱ ውብ
ነው አዲስም ነው። ወንድ ልጅ ስለ ፍቅር ሲያዜም ከቀሚስ ሻገር ብለው የማይመለከቱ ሀሳባቸው የተገደበ ይሆናል። ደግመው
ደጋግመው ለወደዱና ላንቺ ከሆነ ስቃዩም ደስ ይለናል ከኛ በላይ ሆነብን እንጂ ላንቺ ከሚገባሽ በታች ነው ለሚሉ ግን ድንቅ ነው።
የሚገባትን ያህል አድርገን ቢሆን ኖሮ የሀዘን ማቅ መልበሱ ባላስፈለገን ነበር። ከዚህ በበለጠና ባማረ መልኩ መግለጽስ እንደምን
ይቻላል?
ሙሉ ዘፈኖቹን ብሰማ ምንኛ ደስ ባለኝ። ጥቁሩ ሰው ደግሞ እምዬ ሚኒሊክን ከፍ ያደርጋል። እምዬ ሚኒሊክ ለብቻቸው ሳይሆን
ከሀገራችን ከጫፍ እስከ ጫፍ በተነሱ ጀግና ልጆቿ አማካይነት ነው አገር ያቆዩን። እምዬ ሚኒሊክ ብልህና ሴት አክባሪ በመሆናቸውጣይቱን ያህል አጋዥ፣ ጣይቱን ያህል የጦር አበጋዝ ይዘው የገሰገሱ የዚያ ዘመን መሪ እንጂ ጣልያን በሰራላቸው ቀንድ እርዝማኔ
የሚለኩ እርኩስ አይደሉም። በተለይ ታሪክ ተዛብቶ ጣልያን ለሻዕብያ፣ ሻዕብያ ደግሞ ለወያኔና ለሌሎች ያወረሰውን ከንቱ የውሸት
ድሪቶ እንደመረጃ አጣቅሰው ወገናቸውን አምርረው የሚጠሉ ወገኖች ኢትዮጵያ ሀገር መሆን የቻለችው በነርሱም አያቶች ደም እንደሆነ
ስላወቁት ምንኛ ደስ ብሎናል። ታሪክን ተሻግረው የራሳቸውን ጥሩ ታሪክ ለሚሰሩ ሁሉ ክብር ይሁን። ለዚህ ነው አማርኛና ኦሮምኛ
ሕብር ፈጥረው ጀግኖች እየተሞገሱ ሲዘፈን ደስ የሚለው። አማርኛና ኦሮምኛ አንድ ላይ ሲዘፈን ደግሞ የረጨነው መርዝ ረከሰብን
የሚሉ በየጎራው አሉና እንኳን ቅር አላችሁ እንላቸዋለን። ገና ደግሞ ብዙ ቋንቋ ባንድ ዜማ ከትግራይ ከበሮ እስከ ቤንሻንጉል
እምቢልታ ድረስ ኢትዮጵያዊነትን እያስዋበ ይዘፈናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ ናቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ዛሬ
አለኝታ የምንላትን ሀገር የፈጠሩልንና ስማቸው የተከበረ ይሁን። ይህን ታሪክ አገዝፈው በዚህ ግለኝነትና ባለፀጋነት ከአገርና ከወገን
ያስበለጡ፣ ጥበብን ለእለት ጉርስ ከያዙት ለየት ብሎና ከፍ ብሎ የሚወጣውን ብላቴናውንና መሰሎቹን ልናመሰግን ይገባናል። ተማር፣
ተመራመር፣ ተቀኝበትና አዚምበት ብለን ለመልዕክቱ ታላቅነትና ለክብሩ ደግሞ ሲዲውን ገንዘብ ከፍለን ልንገዛና ልናበረታታው እንደ
ፋሲካ ስጦታም ለወዳጅ ለጓደኛ ልናበረክተው ይገባናል። ቴዲ አንተ ስታዜም ኢትዮጵያ ትከበራለችና ከምትችለው በላይ ስጣት
ከሚገባት በታች ያደረግንላት እኛን ይቆጨን።
biyadegelgne@hotmail.com

No comments:

Post a Comment