"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 3 October 2012

በጠ/ሚ/ር አሰያየም ላይ የታመሰው ኦሕዴድ ባለስልጣኖቹን ሊያንጓልል ነው


የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አለማየሁ አቶምሳ። ለረጅም ግዜ ታመው ከአልጋ ቢነሱም የውዝግቡ
ጉዳይ አስፈጻሚ መሆናቸው አልቀረም።
ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው ኦሕዴድ ማ ዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተቀምጧል። የኢሕአዴግ አንድ ክንፍ የሆነው ኦሕዴድ በጠቅላይ ሚ/ር አሰያየም ላይ ኦሮሚያ በትክክል አልተወከለም፤ ወይም ቦታው የሚገባው ለኦሮሞ ተወላጅ ነው በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ከገባ በኋላ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ይህንን አመለካከት ለማጥራት በሚል ስብሰባ አድርጎ ካለውጤት ተበትኖ ነበር። አሁን በድጋሚ ማ ዕከላዊ ኮሚቴው ተሰብስቦ እንደዚህ ያለ አመለካከት ያላቸውን በሙስና፣ በ አቅም እጦት፣ በዲሲፖሊን፣ አውራ ድርጅታቸውን ኢሕአዴግን አደጋ ላይ በመጣል በሚል ከስልጣናቸው ሊያንጓልል፣ አንዳንዶቹንም ዝቅ አድርጎ ሊያሰራ፣ ቀሪዎቹን ያለመከሰስ መብታቸውን አንስቶ እስር ቤት ሊወረውር መሆኑ ተሰምቷል። የሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባ በ ኦሕ ዴድ/ኢሕአዴግ ውስጥ ያለውን ውጥረት ፍንትው አድርጎ ያሳያል፤ እንደወረደ ያንብቡት።
በዘሪሁን ሙሉጌታየኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው።
ድርጅቱ
በግምገማው የሰላ መደባዊ ትግል ማድረጉንና የአመራር ሽግሽግና ሹም ሽር በተጨማሪ በሕግ የሚጠየቁ አመራሮች እንደሚኖሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል።

ለውዝግቡ መነሻ የሆኑት ሶፊያን አህመድ። ሶፊያን አህመድ በኦሕዴድ አባላት ሳይሆን በወ/ሮ አዜብ
ጥቆማ ለጠ/ሚ/ርነት ተወዳድረው ተሸንፈዋል። ኦሕዴዶች የሚሉት ለጠ/ሚ/ርነት ብቁ የሆነው
ሰው መምረጥ የነበረብን እኛ ነን እንጂ አዜብ አይደለችም። በትክክል አልተወከልንም።
ድርጅቱ የሰላ መደባዊ ትግል አድርጓል ሲባል እርቅ የሌለው ትግል መሆኑን የጠቀሱት ምንጮቻችን ስርዓቱን ለማኖር ሲባል የድርጅቱን መስመር በርዘው በሚንቀሳቀሱ አመራሮች ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወስድበት ትግል መሆኑን የሰንደቅ ምንጮች ጠቅሰዋል። ግምገማው በማለባበስና በመደባበቅ የሚታለፍ አመራር አለመኖሩን አያይዘው ገልፀዋል። ኦህዴድ ለሦስት ቀናት እያካሄደ ባለው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የአመራር ውስንነት ባሳዩ አመራሮች ላይ ሦስት አይነት እርምጃ እንደሚወስድም ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን፤ እነሱም በማስጠንቀቂያ የሚታለፉ፣ በሕግ የሚጠየቁና የፖለቲካ ውሳኔ የሚወስንባቸው አመራሮች እንደሚኖሩ አመልክተዋል።
ኦህዴድ ለሦስት ቀናት ባካሄደው የሰላ መደባዊ ግምገማ ለየት ባለ ሁኔታ መካሄዱን የጠቆሙት ምንጮች ግምገማው ስራንና አመለካከትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ከድርጅቱ መስመር ውጪ ሲሰሩ የነበሩ የአመራር አካላት ላይ ሕጋዊና ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚወስድበት አግባብ እንደሚኖርም ተጠቁሟል። በግምገማው ሂደት በይቅርታ የሚታለፉ እንደሚኖሩ ሁሉ የማያዳግም እርምጃ እና የቦታ ሽግሽግ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
በግምገማው ሂደት የሚጠየቁ አካላት የዲሲፕሊን ጉድለታቸው ከፍተኛ ከሆነም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በስራ አስፈፃሚው ለጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት የሚቀርብ ከሆነ ጨፌው የቀረበለትን ጥያቄ ገምግሞ የሚወስን ይሆናል ሲሉ ምንጮች ጠቁመዋል።
የኦህዴድ ከአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች በተለየ ግምገማ ሊጠመድ የቻለው ከጠቅላይ ሚኒስትርነት አሰያየም ጋር በተያያዘ የተነሱ አሉባልታዎችን ለመመከት መሆኑን ምንጮች የጠቀሱ ሲሆን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር አሰያየም ጋር በተያያዘ የሚነሱ አሉባልታዎች በጊዜ ካልተሰበሩ የፌዴራሊዝም ስርዓቱ አደጋ ላይ ስለሚወድቅ ትግሉ ያለ እርቅ እንዲካሄድና ግንባሩ እስካለ ድረስ የግንባሩን አላማ ማራመድ የግድ መሆኑ መጠቀሱንም የሰንደቅ ምንጮች ገልፀዋል። ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና በይቅርታ የሚታለፉ የድርጅቱ አመራሮች በተመለከተ እነማን እንደሆኑ ምንጮቻችን ባይገልፁም
ግምገማው ግን ለህትመት እስከገባንበት ትናንት ማምሻውን ድረስ መቀጠሉን ለመረዳት ችለናል። ይህ በ እንዲህ እንዳለ ግንቦት 7 “ጥሪ ኦሕዴድ አባላት” በሚል ርዕሰ አንቀጽ አውጥቷል። ለግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ ከዚህ ዜና አጋር አያይዘነዋል። እነሆ።
ተዋርዶ ከማዋረድ መላቀቂያችሁ አሁን ነው!!!

ጁነዲን ሳዶ። በቶሎ ይንገዋለላሉ ወይም ዝቅ ብለው ይሰራሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል አንዱ
ናቸው። ጁነዲን ባለቤታቸው ከኢትዮጵያውያን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ታስራለች።
የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ታላቁን የኦሮሞ ሕዝብ እወክላለሁ ይላል። ኦሮሞ ደግሞ የኢትዮጵያ ምሰሶ ነው። ከዚህ ታላቅ ሕዝብ ወጣሁ የሚለው ኦሕዴድ ግን እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ ጥቅም ሊጠብቅና ሊያስጠብቅ ቀርቶ ለራሱ እንኳን መሆን ያልቻለ፤ የተናቀና የተዋረደ የወያኔ ሎሌ ሆኖ ድፍን 21 አመት አስቆጠሮአል።
ወያኔ ደግሞ ስሙ እንደሚያለክተው ከውልደቱ ጀምሮ የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ነው። ወያኔ ትግራይን “ነፃ” ካወጣ በኋላ ለመቋቋሚያ የሚሆነው ግዛት አስፈለገው። ወያኔ ኦሮሚያን መግዛትና መበዝበዝ ለሕልውናው አስፈላጊ እንደሆነ ተገነዘበ፤ ለዚህም ተንቀሳቀሰ። በኦሕዴድ ሎሌነት የኦሮሚያን ሕዝብና መሬት በቁጥጥሩ ሥር አደረገ። “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” እንዲሉ በዘር ፊደራሊዝም ስም የኦሕዴድ ካድሬዎች ኦሮሚያን ለወያኔ ዘረኞች
አሳልፈው ሰጧት። ኦሕዴድ ባይኖር ኖሮ ኦሮሚያ የወያኔ መፈንጫ ባልሆነችም ነበር። የኦሕዴድ ክህደት ግን በዚህ አላበቃም። የወያኔ ሹማምንት በኦሮሞ ለም መሬት፣ ደን፣ ማዕድንና ውሃ ሲከብሩ የኦሕዴድ ሎሌዎች ለፍርፋሪ ሲሉ ብዘበዛውን ማሳለጥ ጀመሩ። የኦሕዴድ ካድሬዎች የገዛ ወገናቸውን አሳረዱ፤ ያደጉበትን መንደር፤ የሮጡበትን ሜዳ አዘረፉ።
በኦሕዴድ ሎሌነት ሳቢያ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ እስር ቤቶች በኦሮሞዎች ተሞልተዋል። የኦሮሞ ለም መሬቶች ለወያኔና የወያኔ ወዳጆች ለሆኑ ባዕዳን በብላሽ ታድሏል። የኦሮሞ ደኖች ተመንጥረዋል። የኦሮሞ ማዕድናት ወያኔ እንዳሻው የሚያፍሰው ባላቤት ያጣ ንብረት ሆኗል። በኦሕዴድ ሎሌነት ሳቢያ ዛሬ የኦሮሞ ገበሬ ብቻ ሳይሆን የዱር አራዊቱም ተሰደዋል። ይህ ሁሉ የሆነው የኦሮሞ ልጆች ነን በሚሉ የኦሕዴድ ካድሬዎች ሎሌነት መሆኑ እጅግ የሚያስቆጭናበጠ/ሚ/ር አሰ1ያየ0ም/3/ላ1ይ2የታመሰው ኦሕዴድ ባለስልጣኖቹን ሊያንጓልል ነው  የሚያንገበግብ ነገር ነው።
አሁን ደግሞ የባሰ አሳፋሪ ነገር እየታዘብን ነው። ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በመሞቱ በረከት ስምኦንና ግንባር ቀደም ወያኔ ደቀመዛሙርቱ የወታደሩንም የሲቪሉንም ሥልጣን እየተቀራመቱ ነው። እስቲ እንጠይቅ።
•ከዚህ ቅርምት ለኦሕዴድ ምን ደረሰው? ምንም።
•የጄኔራልነት ማዕረግ ለሕወሓት ሰዎች ሲታደል ኦሕዴድ ምን አደረገ? ምንም።
•የአገሪቱ የደህንነት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በወያኔ ሲያዝ ኦሕዴድ ምን አለ? ምንም።
•የአገሪቷ ንብረት በሙሉ ወያኔ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ሲያዝ ኦሕዴድ ምን አለ? ምንም።
•ሟቹን መለስ ዜናዊን ለመተካት በነበረው ሽኩታ የኦሕዴድ ሚና ምን ነበር? ምንም። ይህ ከምር ያሳፍራል።

የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አለማየሁ አቶምሳ። ለረጅም ግዜ ታመው ከአልጋ ቢነሱም የውዝግቡ
ጉዳይ አስፈጻሚ መሆናቸው አልቀረም።
አሳፋሪነቱ ደግሞ ለኦሕዴድ አባላት ብቻ ሳይሆን ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ ከዚያም አልፎ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተርፎአል ። የኦሮሞ ሕዝብ ኦሕዴድን የመሰለ አሳፋሪና ከሃዲ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኦሕዴድን ከአባላቱ ለይቶ ማየት ይሻል። ከዚህም በተጨማሪ የኦሕዴድን ከፍተኛ አመራር አባላትን ከበታቾቹ ለይቶ ይመለከታል። ሥጋቸውን ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸውንም ሳይቀር
ለወያኔ አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ኦሕዴድ ውስጥ መኖራቸው ምንም ጥርጥር የለውም። በአንፃሩ ደግሞ ራሳቸውን ከወያኔ ባርነት ነፃ አውጥተው የበደሉትን ሕዝብ በመካስ ላይ ያሉ ጀግኖች መኖራቸው ግልጽ ነው። ግንቦት 7፡ ከውስጥ ሆነው ወያኔን እየታገሉ ላሉም ሆነ ድርጅቱን ጥለው የነጻነት ትግሉን ለተቀላቀሉ ለእነዚህ ቆራጥ የቀድሞ የኦሕዴድ አባላት፤ የዛሬአርበኞች ትልቅ አክብሮት አለው። በሚያደርጉት ትግልም ከጎናቸው ቆሟል፤ ወደፊትም ይቆማል።
ግንቦት 7፣ ብዙሃኑ የኦሕዴድ አባላት ራሳቸውን ከወያኔ ዘረኛ አምባገነን አገዛዝ ነፃ የማውጣት የግል፣ የወገንና የአገር ግዴታ አለባቸው ብሎ ያምናል።
ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለብዙሃኑ ኦህዴድ አባላት የሚከተለው ጥሪ ያደርጋል።
የኦሕዴድ አባላት ሆይ!
ከወያኔ ዘረኛ አምባገነን አገዛዝ ሎሌነት ነፃ ለመውጣት መንገድ መሻት የራሳችሁ ኃላፊነት ነው። የገዛ ራሳችሁን፣ቤተሰቦቻችሁን፣ የኦሮሞን ሕዝብ እና ኢትዮጵያን እያዋረደ፤ ሃብቷን እያዘረፈ ካለው ወያኔያዊ ኦሕዴድ ተላቀቁ። አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ድርጅቱን ግደሉት። የኦሕዴድ መኖር ለወያኔ ካልሆነ በስተቀር ለእናንተ፣ ለቤሰቦቻችሁ፣ ለክልላችሁ ለኦሮሚያና ፣ ለኢትዮጵያ አይበጅም። በአሁኑ ሰዓት የወያኔን እድሜ እያራዘማችሁ ያላችሁ እናንተ ናችሁ። በፓርላማው ሳይቀር ለወያኔ የማሳሳቻ ጭንብል የሆናችሁለት እናንተ ናችሁ። ተዋርዳችሁ ሕዝባችሁን አታዋርዱ። ይልቁንስ ታሪክ
ሥሩ። ዛሬውኑ የነፃነት ትግሉን ተቀላቀሉ። አለበለዚያ ወያኔ ያለበሳችሁን የውርደት ካባ ለማውለቅ እንኳን ጊዜ አይኖራችሁም።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

No comments:

Post a Comment