"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 4 October 2012

ለኢትዮጵያ መንግስት ቢጫ ሊሰጠው ነው – ከአቤ ቶኪቻው






ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሙስሊሙ ህብረተሰብ በየቀበሌው ሄዶ ምርጫ ላይ እንዲሳተፍ ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑ ታይቷል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “ምርጫችን በመስጂዳችን” የሚል እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት በዚህ ሰዓት፤ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “የታሰሩ ወንድሞቻችን ይፈቱ” ብለው እየጠየቁ ባለበት በዚህ ሰዓት፤ መንግስት ግን የመስማት ፍላጎቱ በመቀነሱ ሳብያ ሊሰማቸው አልቻለም። ሊሰማቸው ባለመቻሉም የታሰሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሳይፈቱ ምርጫውንም በቀበሌ አድርጎታል።
በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ ትልቁ ችግሯ “መናገር እንጂ መስማት አለመቻሏ ነው” ብለው ተናግረው ነበር። እኔ የምለው ይህንን ችግር የሚያክም አንድ እንኳ ባለሞያ ይጥፋ እንዴ!? ሌላው ቢቀር ባህላዊ መፍትሄ እንዴት ይጠፋል? እሺ ሌላው ይቅር በፀሎትስ ቢሆን ይህንን ህመም ለማስታገስ ጥረት መደረግ የለበትም ትላላችሁ!
ለማንኛውም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በነገው ጁምዓ ለመንግስት ቢጫ ሊያሳዩት እየተሰናዱ እንደሆነ መስማቴን አልደብቃችሁም። እንደሰማሁት ከሆነ በአርቡ የሶላት ጊዜ በተለያዩ መስጊዶች ቢጫ ቀለም ያለው ወረቀት ወይም ጨርቅ በመያዝ ማስጠንቀቂያው ለኢህአዴግ ተጫዋቾች ይሰጣቸዋል።
ይህንን ማስጠንቀቂያ የመስጠት ስነ ስርዓት ክርስቲያን ወገኖችም ተሳታፊ እንደሚሆኑበት ሰምቻለሁ።
መንግስቴ ግን ይሄን ሁሉ የእልህ ጨዋታ እና ተደጋጋሚ “ፋዎል” መስራት ለምን እንደፈለገ ሊገባኝ አልቻለም። እስቲ የገባው ግራ ለገባው ያስረዳ!


No comments:

Post a Comment