"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 7 September 2012

አወዛጋቢዋ ድንግል ማርያም ነኝ ባይዋ ሴት በድጋሚ ወደ ዜና ብቅ አለች


  • በአዲስ አበባ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግድያ ወንጀል እና በተለያዩ ክሶች አቃቤ ሕግ ከሷታል፡፡
  • በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ውጪ በፊቼ ክስ ተመስርቶባታል፡:
  • ተከታዮቿ በአዳዲስ ምልምሎችም ከበፊቱ በዝተዋል፡፡
  • ተከታዮቿ ከደብረ ሊባኖስ  መስቀል ቤተ  በመግባት እና ደብሩ ቅዳሴ ላይ እያለ ቅዱሳኑን እና መስቀሉን በመሳደባቸው ግጭት  እና ብጥብጥ ፈጥረዋ፡፡ 
ከሰማናቸው በጣም አስገራሚ እና አሳዛኙ ከስተቶች መካከል የዚህች ድንግል ማርያም ነኝ ባይ  ሴት ጉዳይ ከሁሉም አስገራሚ እና አሳዛኝ እንዲሁ በደፈናው ተከታይ ማፍራት እንደሚቻልና የዋሐንን በቀላሉ በመያዝ እንደሚጠቀሙባቸው ያሳየል፡፡ ለካ በቀላሉ የሚታለል ሰው በዝቷልና ያሰኛል፡፡
ከዚህ በፊት በዚህችው ሴት ጉዳይ ካስነበብናችሁ ዋና ጉዳይ መካከል፡-
  •   እናቷ ከሞተች በኋላ ከእግዚአብሔር መልክት ልትነግራት እንደተነሳች ከዚህ ግዚ ጀምሮ ተከታዮች ይዞ ወደ ተለያዩ ገዳማት በመሄድ የማወዛገብ ስራዎች እንደሰራች
  •      በፆም ወቅት ሥጋ እንዲበሉ ማስገደዱን በሌሎች ጊዜዬም አብዝተው እንዲፆሙ ማስገደድ
  •   ተከታዮቿ ሰማያዊያን ነን የሚሉ እንደሆነ
  •      3ቱ ልጆቼንም የወለድኩት በመንፈስ ቅዱስ ነው ጠባቂዬ ተርፌሳ ዮሴፍ ማርያምን እንደሚጠብቃት የእኔ ጠባቂ ነው፡፡
  •      እየሱስ ክርስቶስ ከእኔ ይወለዳል…….
የሚሉ እና ብዙ የተለያዩ አስገራሚ ጉዳዮችን ሲባሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁንና አሁንም የማወዛገብ ስራዎቿን በመቀበል ብዙ የማደናገ እና የማወዛገብ ስራዎችን እየሰራች ትገናለች፡፡
በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከ36 በላይ የሚሆኑ የቅርብ ተከታዮቿ ጋር በመሆን በመስቀል ቤት በመግባት መስቀሉን  ጣዖት ነው በማለት ከፍተኛ ብጥብጥ በመፍጠሯ 36ቱም በፊቼ ከተማ እስር ቤት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ከፍተኛ ብጥብጥ በመፈጠራቸውም በላይ የማንነታቸን መለያ በሆነው መስቀለ ልይ ለፈፀሙት ተግባር  36ቱም በፍቼ ክስ መሰርተውባቸው ለትላንትለነሐሴ 10 ተቀጥረው ነበር ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የጣራውን ኮርኒሱን ሰንጥቄ አርጋለሁየሚሉ ቃላቶችን  መሰንዘሯ ታውቋል፡፡
በ2004 ዓ.ም  ከ5 ጊዜ በላይ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበች ሲሆን ተከታዮቿም ከበፊቱ የተለያዩ አዳዲስ ሰዎችም እንደተቀላቀሏት እና አብረዎት ያሉትንም ምስኪን ወንዶችንም በቅዱሳን ስም በመሰየም ተግባራቸውም የቅዱሳን ነው ማለቷ ተዘግቧል፡፡
እንዲሁም ክስ ከተመሰረተባት ጉዳይ ጥቂ
  •  ስጋ ወደሙ ነው በማለት ተከተዮቿን ደም እንደምታጠጣቸው በዓይናቸው የተመለከቱ እንደመሰከሩ
  • አንድ እናትም ልጄን ሳር እንዲበላ በማስገደድ እና በማጎሳቆል እንዲያርፍ አድርጋለች በማለት መስክረውባታል ክርክርም ላይ ናቸው
ሌሎች አያሌ ክስ  ያለበት ሲሆን በዚሁ ወርም ነሐሴ 18/19/ አዲስ አበባ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ መሆኗን ተረድተናል፡፡

ለምዕመናን የምናስተላልፍው መልእክት ቢኖር ምዕመናንን የማደናገርና የማሳሳት ስራ ዛሬ የተጀመረ ስራ ባይሆንም የተለያዩ ስለቶችን በመያዝ በአንዲቷ ሃይማኖታችን ስም  እየተነሱ ብዙ የዋህ ክርስቲያኖችን ሲያታልሉ ኖረዋል የኖራሉም ነገር ግን ለቤተ ክርስቲያናችን የሚያመጣው ገፅታ ከፍተኛ ችግር በመሆኑ   አጥብቀን ልንዋጋቸው የሚገባ ጉዳይ ነው በቅርቡም እንደምናስታውሰው እና እናንተም እንደገለፃችኁልን አንድ ከጎንደር የመጣች ሴትም በዚሁ አመቤቴ ታናግረኛለች በማለ ብዙ ታላለቅ ሰዎችም የተከረየችበት ቤት ድረስ እንደሚሄዱ እና ሴትየዋ እራሷን አለማዊ መናኝ ነኝ በማለት እና መንፈስ ቅዱስ እንደሚታያትእና እመቤታችን እንደምታናግራት ነው የምትናገረው ሁለት ልጆች ሲኖራት የመጀመሪያዋከሌላ ሰው የተወለደች ሲሆን ሁለተኛውም ከሌላ ወንድ የተወለደ ነው፡፡ ይህን ስራ ከጀመረችወደ 20 አመት ይሆናታል ካህን የሚያደርገውን ሁሉ ታደርጋለች ለምሳሌ ቄደር ማስጠመቅ፣ንስሃ ለሷ መናዘዝ፣ ቅባቅዱስ መቀባት የመሳሰሉትን ነገሮች ታደርጋለች ለምን ይሄ እኮ የካህንስራ ነው ስትባልም እመቤቴ በልዩ ትዕዛዝ ለኔ ሰጥታኝ ነው ካህናቶች ሴቶችን በሚቀቡበትጊዜ እየተሰናከሉ ስለሆነ ይህን ስልጣን ለሷ እንደተሰጣት ትናገራለች የንስሃ ልጆቼከምትላቸውም አስራት ትወስዳለች፡፡  ብዙ የዋሃን አስታለች እያሳተችም ነው እውነትን በመዘንጋት በየጉራንጉሩ በሚነሱ አጉል እምነቶች እና ዲያቢሎስ ስልቱን በመቀያየር ቁጥር የሚሸነፉ ቤት ይቁጠረው ይህ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ከሚሰሩት ሴራ ተለይቶ የሚታይ  አይደለም ሁሉም የአንዲት ቤተ ክርስቲያንን ጥፋት የሚፈልጉ ፡  የራሳቸው ጥቅም እና የሚከበርበትን መንገድ የሚሹ በመሆናቸው ምዕመናን አጥብቀን ልንታገላቸው እና ልንከላከላቸው ይገባል፡፡ ዲያብሎስ ዝናሩን እስኪጨርስ የእኛም ትጋት ሊቀጥል  ይገባል፡፡ 
አምላካችን አግዚአብሔር ያመንውን እንዲያጸናን ያላመኑትን እና በጥርጥር የሚጓዙትን ወደ አሚነ ስላሴ እንዲመልስልን ፈቃዱ ይሁንልን አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment