"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 7 September 2012

ዘማሪት ዘርፌ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልጠበቀ ጋብቻ


ሁሌም ቢሆን ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ እያየን ዝም የሚል ልብ የለንም፡፡ በተለይ በመድረክ አገልግሎት ላይ በመናያቸው ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ ማየተ ደግሞ በጣሙን የቆስላል፡፡ መቼም ሳይገባው የቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ለመውጣት የሚደፍር አለ ብለን አናስብም ትንሽም ቢሆን ምስጢራትን የተማረ እና የስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያወቀ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትማ ካየንው አንድ ሰው ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት በፈሪሐ እግዚአብሔር ሊቀርብ ይገባዋል::“በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።” ዘዳ.12:28፤ እንደተባልንው ስንመላለስ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚያዘንን በመፈጸም መሆን ይኖርብናል:: 
እግዚአብሔርን የሚፈራ ትውልድ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል ይገዛል በእግዚአብሔርም የባረካል፡፡ በንስሃ ህይወቱም ሁል ጊዜ ተጠብቆ መኖርም ይገባል “እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ” ራእ.3:3 ንስሃ የሚገባ ሰው ደግሞ ህይወቱ በጸሎት የመሰረታል ሁል ጊዜም ይሰግዳል ይጾማልም ለአገልግሎቱም መቃናተ ፈቃደ እግዚአብሔርን በመጠየቅ ይኖራልም፡፡ እነኝህ ያነሳናቸው በጣም ጥቂቱን ግዴታዎች ነው ይህቺን ትንሻን ህይወት የሌለው ክርስቲያን አገልጋይ አይደለም ክርስቲያን ለመሆኑም ጥርጣሬ ውስጥ ይገባል፡፡ 


ይሁንና ይህቺን በጥቂቱ ያልነው የዘማሪት ዘርፌ አይን ያወጣ ጋብቻ ነው፡፡ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ማናት? በዘፋኝነት ህይወት እያለች ምን አይነት ህይወት ነበራት? የሚሉትን ሁሉ እንተወውና በቤተ ክርስቲያናችን ወደ አገልግሎት ከመጣች ብኋላ በኢትዮጵያ እያለች ከፕሮትስታንት ተሃድሶ አራማጆች ጎን ብዙ ጊዜ ስሟ ሲነሳ የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካም ከሄደች ወዲህ ከአባ 

ወልደ ትንሳኤ ጋር በአንድ ጉባኤ ለአገልግሎት እንደምትሳተፍ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡


በሚታየው አገልግሎት የማይታየውን ፀጋ ከምናገኝባቸው ውስጥ ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ የማይደገም ምስጢር ምስጢረ ተክሊል ነው ፡፡ ምስጢረ ተክሊል የሚፈፀመው በፍትሃ ነገስት አንቀፅ 24፡ 906 ላይ እንደተገለፀው የመጀመሪያው ሥጋው ድንግልና ነው ፡፡ ከሁለት ተጋቢዎች አንዱ ድንግልናውን ያጣ እንደሆን በድንግልና ላለው ስርአተ ተክሊሉ ተፈፅሞለት ተክሊል የሚያደርግ ሲሆን ድንግል ላልሆነው ግን ፀሎተ ንስሃ ተነቦለት ቅዱስ ቁርባኑን ተቀብለው ጋብቻቸው ይፈፀማል ፡፡
ልላው ድንግልናቸውን በተለያዩ ምክነያቶች ላጡ ለምሳሌ በሕክምና የተነሳ፤ በተፈጥሮ ሲወለዱ የድንግልና ምልክት የሌላቸው፤ ለአቅመ ሔዋን ሳይደርሱ ተገደው የተደፈሩ፤ ከአቅም በላይ የሆነ ስራ በመስራት ድንግላናቸውን ያጡ ስርዓተ ተክሊል ሊፈፀምላቸው ይችላል፡፡ ይህ በዚሁ እንዳለ ስርአተ ተክሊል የሚፈፀመው የሃየማኖት አንድነት ላላቸው 2ኛ ቆሮ. 6፡ 14-18፤ ፍቃደኝነታቸውን ለገለፁ ተጋቢዎች እና ከ 20 አመት እድሜ በላይ ለወንዱ ፡ከ15 እድሜ ኣመት በላይ ለሴት ከሆኑ እንድሆነ ሰረዓተ ተክሊል ይፈፀምላቸዋል፡፡ ይህንንማ ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 24 ፤883-884፤894 እና 906 ላይ በስፋት ተዘርዝሯል፡፡
በድንግልና ለመኖር ወስኖ ቃልኪዳኑን ትቶ አፍርሶ ያለ አንድ ሰው ፀሎተ ተክሊል ሳይፈፀምለት በቁርባን ብቻ ማግባት የተፈቀደ ነው፡፡ ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 24፤ 834 “ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱ በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።”ዘኊ.30:2::
በስዓርተ ተክሊል ተጋብተው ባል ወይም ሚስት አንዱ የሞተ እንድሆን እና በሕይወት ያለው ለማግባት ቢፈልግ ግን ሚስቱ የሞተችበት ከአንድ ዓመት ብኋላ፤ ባሏ የሞተባት ከ10 ወር ብኋላ ከሐዘናቸው ተፅናንታ ማግባት ይችላሉ ይህም በፍትሐ ነገስት አንቀፅ24 ፤ 916 ተገልጧል፡፡በጥቂቱ ስለ ስርዓተ ተክሊል ካየን ዘማሪት ዘርፌን ከላይ ከጠቀስንው የሚገልፃት የቱ ነው፡፡

2. ከበፊቱ ባሏ ወደ ልላ ካህን ባል ማግባቷ?
3. የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት በአደባባይ መጣሷ እና ማስጣሷ?
4. አርአያ በመሆን ፋንታ ብጣሽ ጨርቅ ለብሶ ገላን እያሳዩ ከበሮ መምታቷ?
5. ማህተብ ሳታስር መታየቷ?
ሌላም ሌላም ሌላም ብቻ ሁሉም ስርአተ ቤተ ክርስቲያን ለምን አልተከበረም?  በውጪ ያሉ አብያተ ክርስቲያናተም በስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተብለው ለስርአቷ መከበር ከመድከም ይልቅ ስርዓቷን ለማጥፋት ለመቀየር ጥረቶችስ ለምንድን ነው? ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች ናቸው::
ለቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መከበር ያለሰለሰ ጥረት እናድርግ ፡፡
ይህን እንድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
ለቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መከበር ያለሰለሰ ጥረት እናድርግ ፡፡
ይህን እንድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
ዘማሪት ዘርፌ በኢትዮጵያም እያለች ከጋምቤላ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ረዳት የሆነውን ዲ/ን አይናለምን ከጋምቤላ ከተማው ውጪ በለ አድባር በቅዱስ ቁርባን ማግባቷ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ ከዚየም ወደ አዲስ አበባም ሲመጣ አብረው እንደነበሩም የሚታወቅ ነው::

  ከኢትዮጵያ ከወጣች ብኋላ ደግሞ በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሐምሌ ወር ቅዱስ እሰጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ያገለግልየነበረውን ዲ/ን ዘገብርኤል ጋራ በስርዓተ ተክሊል ሁለተኛዋን ጋብቻ ፈፅማለች፡፡



መጀመሪያ በቅዱስ ቁርባን ሁለተኛውን ደግሞ በስርዓተ ተክሊል ልብ በሉ በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት ጋብቻ ሲፈፀም ከቤተ ክርስቲያን ከወጣ ብኋላ ምን አይነት አለባበስ የኖረዋል የሚለውን ለእናንተ ትተን ስርዓተ ተክሊል በቤተ ክርስቲያን ስርዓት መስረት እንዴት ይፈፀማል የሚለውን ጥቂት እንመልከት፡፡


1. በጋብቻ ላይ ጋብቻ መፈፀሟ?
ለአንድ አገልጋይ ነኝ ባይ ደግሞ ይህቺን ጥቂቷን የቤተ ክርስቲያን ግዴታ መወጣት ግዴታው ነው ባዮች ነን፡፡ የእኛ ድርሻመሆን ያለበት እንዲህ መሰሉን ኢሰርአተ ቤተ ክርስቲያን ሲፈፀም ተመልክተን ማለፍ ሳይሆን እንዳይደግም የየራሳችንን ጥረት ማድረግ የጠበቅብናል፡፡                    ለቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መከበር ያለሰለሰ ጥረት እናድርግ ፡፡ 
ይህን እንድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

No comments:

Post a Comment