ቀኑ እሁድ ነሀሴ 27_ 2004 ሲሆን ሰአቱ በግምት ከቀኑ 8 ፣30 ይሆናል ። በእለቱ በኖርዌ የምንገኝ የኢህአፓ እና የ ዲሞክራቲሲ ለውጥ በኢትዮጵያ፡ አባላት እና ደጋፊዎች በጋራ ታላቅ ሰላማዊ አደረግን። የሰላማዊው ሰልፍ ዋናው አላማ የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር የሆነው ምላስ ዜናዊ በመሞቱ ምክንያት ሲሆን፧ ለ21 ዓመታት ሲያለቅስ፦ሲያዝን፦ሲራብ፦ ሲጠማ ፦ሲሰደድ ፦ሲታሰር ፦ሲገረፍና፡ሲገደል የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አለህ በማለት ደስታውን ለመግለጽ ነው። በፎቶው እንደሚታየው በዛ ያለ ኢትዮጵያዊ በዝግጅቱ ላይ ተገኝቷል። በዕለቱ የተገኙት ከሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲ እና ድር ጅት አባላት
ውጭ ደጋፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል። በመጀመሪያ የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ሰበሳቢ የሆኑት አቶ ዳዊት ዕንኳን ደስ አላችሁ በማለት የመክፈቻ ነግግር ሲያደርጉ በመቀጠለል የኢህአፓ ተወካይ የሆኑ አቶ ሞላ ንግግር አድርገዋል ። ፕሮግራሙን በመምራት ከኢህአፓ አቶ አርጋው ከዲሞክራሲ ለውጥ አቶ ማተቤ ሲሳተፉ ተስተውሏለል።በኖርዌ ከምንገኝ ኢትዮጵያውያን መካከል በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ተሳተፎዋቸው ጎልትው ከሚታዩት ውስጥ ዶክተር ሙሉ አለም፧ አቶ አምሳል ካሴ፧ አቶ ግደይ፧ ሁሉም በቅደም ተከተል ንግግር አድርገዋል። አቶ እንግዳሽት መች ደረስኩባችሁ የሚለል ግጥም ሲያቀርቡ፤ኧቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ደግሞ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዛብሄር ተዘረጋለች የሚል ግጥም አቀረቡ፤እንዴሁም አቶ ልዑል በ እንግሊዘኛ ግጥም አቅርበዋል ። ወይዘሪት ሜርሲ ቀስቃሽ የሆነውን ኢትዮጵያ አገራችን የሚለውን ዜማ አዜመዋለል
በዚ መሃል ጥቁር በጥቁር የለበሰ ማለትም መሪያቸው በመሞቱ በሃዘን ላይ የሚገኝ የወያኔ ደጋፊ የእለቱን ደስታችንን ለማበላሽት ፕሮገራሙን ለማቋረጥ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።ችግር ለመፍጠር ሞክሮ የነበረው የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተገኘውን ኢትዮጵያዊ ቪዲዎ በመቅረጽ ላይ እያለ ነው እጅ ከፍንጅ የተገኘው። ለምን ትቀርጸለህ ተበሎ ሰለተጠየቀ ነው ገርግር ፈጥሮ ተመታሁኝ በማለት ፖሊስ በማምጣት ችግር ለመፍጠር ሞከሮ የነበረው ግን ሳይሳካለት ቀርቷለ ። የእለቱ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቋል።በእውነቱ እኛ አንድ ስንሆን ህብረታችን በጠነከረ ቁጥር ጠላቶቻችንን ለማሸነፍና ለማጥፋት በዙ ጊዜ አይወስድብንም እንበርታ እንጠንክር። ዜናው የራሴ እይታ ነው ከ እንዳለ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment