"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 5 September 2012

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ግሽበት አይሎአል ፣ነጋዴው በእለታዊ የምግብ እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቶአል።



በከፍተኛ ደረጃ የኑሮ ውድነት እያጠቃው የመጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ከቀድሞው በበለጠ ሁኔታ በዚህ ሁለት ሳምንታት ውስጥ በከፍተኛ የዋጋ መጠን የኑሮ ውድነቱ መጨመሩን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ያደረሰን ሪፖርት አመላክቶአል ። በዛሬው እለት በተለያዩ የንግድ ተቋማት ተንቀሳቅሶ የንግዱን ሁኔታ የተመለከተው ዘጋቢያችን በሽንኩርት እና በቲማቲም ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዳለ የገለጸ ሲሆን ህብረተሰቡ የመኖር አቅሞ እጅጉን እንደከፋበት አስታውቆአል ። ምንም ገቢ የሌላቸው የዜጎች ወደ ጎዳና ከመውጣት በስተቀር ምንም እድል የላቸውም ፣መንግስት የስራ ፈጠራን አድጌአለሁ እድገት ከ11 በመቶ በላይ እያሳየሁ ነው ሲል የውጭ መገናኛ ብዙሃኖች እና አይኤምኤፍ ደግሞ 7ከመቶ የኢትዮጵያ እድገት እንደተመዘገበ ይጠቁማሉ ። ይህም ሆኖ የተቸገረው ህዝብ ብዛት ከ30፣ኢሊዮን በላይ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ ይህም ማለት የአንድ አፍሪካ ሙሉ የሃገሩን ህዝብ እንደማለት ሲሆን የኢትዮጵያ የሃገሪቱን ከ1/4 በላይ የሚሆነው ህዝብ በረሃብ እንደተጠቃ  የሚያሳይ ነው ሲሉ ተንታኞችም አክለዋል ። በተለይም ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሞት በሁዋላ እየታየ ያለው የሃገሪቱ የኑሮ ውድነት እና የኢኮኖሚ ግሽበት የተከሰተው ከ2 ሳምንታት በላይ ያለምንም ስራ የሃዘን ቀን ተብሎ ህዝቡ ስራ መፍታቱ እና የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን ማቆማቸው እንደሆነ ይናገራሉ በሌላም በኩል አንዳንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የምሽት ክለብ ባለቤቶች እንደሚናገሩት ከሆነ ያሳለፍነው የመከራ ሳምንታት ነበር ከስራችን ተስተጓጉለን ቆይተናል ብዙም ኪሳራ ደርሶብናል ፣አሁንም ምንም ገበያ የለንም ፣ እንደዚያም ሆነን ላልሰራንባቸው ቀናቶችም ገና ታክስ ጭነው ያመጡብናል የቤት ኪራይ እና የኑሮው ውድነት እኛ ከምንጠብቀው በላይ ስለሆነ አንደበታችንን  እንደ ዘጋን በግፍ ዘመን መኖርን መርጠናል ምንም አማራጭ የለንም ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል። በሌላም በኩል አንድ አባ ወራ እንደ ተናገሩት ከሆነ ህይወታችንን ለማሳመር ስንል ያሉንን ሁሉ እያደረግን መኖር ጀምረናል የደርግ ስርአት እራሱ ተመልሶ በጓሮ በር መጣ ሲሉ ለማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ለ ጋዜጠኛ ወንደሰን ሃሳባቸውን ማካፈላቸውን ሪፖርተራችን  በላከልን መልእክት መሰረት  ለመገንዘብ ችለናል ።ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃዘን ምክንያት በከተማይቱ ዝቅ ብሎ የነበረው የሰንደቅ አላማ ከነገው እለት ጀምሮ ከፍ ብሎ እንደሚውለበለብ የተገለጸ ሲሆን ወደ ቀድሞው የኑሮ ይዘት ለመመለስ ግን ከፍተኛ የሆነ የልፋት ቀናቶች ይጠብቁናል ሲል አክሎ ገልጾአል።

No comments:

Post a Comment