"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 30 August 2012

ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በህይወት አሉ



ሰሞኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በተያያዘ መጥፋታቸው ሲነገርላቸው የነበረው እና ቀጥሎም ሞተዋል በሚል በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ሲነገር የቆየው የባለሃብቱ ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ  በህይወት መኖራቸው ተረጋገጠ ።  የባለ ብዙ ኩባንያ ባልተቤት እና የገቢ ምንጫቸው በአረብ አገር የሚገኘው የነዳጅ ኩባንያ እንደሆነ የሚነገርላቸው እኝሁ ባለሃብት በዚህ ሳምንት ውስጥ አዲስ አበባ ገብተው መታየታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል ።በዛሬው እለትም የጠቅላይ ሚንስትሩ አስከሬን ለማየት ወደ ቤተመንግስት አምርተው የህሊና ጸሎት አድርገው መመለሳቸውን የማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቦአል ።ሼኩ ምክንያቱ ምንም ባልታወቀበት ምክንያት ከወዳጃቸው ጠ/ሚንስትር ሞት በሁዋላ ያለመታየታቸው ብዙ ስጋትን በህብረተሰቡ ውስጥ ፈጥሮ እንደ ነበር የገለጸው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ በአሁን ሰአት የህወሃት አባላት ክፉኛ ታመዋል እየተባለ አገር በሚታመስበት ወቅት እሳቸውም ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸውም ታምው ነበር፤ በህይወት አልፈዋል የሚለው በሃገርቤት እና  እንዲሁም ኢሮጵ እና አሜሪካ ተሰራጭቶ መወራቱ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ነበር ።ይበልጥ በሼክ መሃመድ ሁሴን አላህሙዲ ስር የሚተዳደሩት ከ20.000 በላይ የሚጠጉት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ሊገቡ ይችላል በሚል ስጋት ህብረተሰቡ ስጋታቸውን በግልጽ አንጸባርቀዋል። የሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በምርጫ 97 አ.ም የንብ ምልክት ያለበትን ቲ-ሸርት ለብሰው መታየታቸው ህብረተሰቡን አስከፍቶ የነበረ ቢሆንም ለሃገሪቱ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ስራ  እና ደሃውን ህብረተሰብ ከስራ አጥነት ማላቀቃቸው ትልቁ ራእያቸው ነው ሲሉ አንዳን ወገኖች ገልጸዋል። ሆኖም ግን በሚድሮክ ኢትዮጵያ የወርቅ ማእድን ስራ በሚደረገው የሰራተኞች ጉልበት ብዝበዛ እና የወርቅ ማእድን ወደ ሌሎች ሃገሮች ቅድሚያ ተሰጥቶ መላኩ ደግሞ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት ማራቆት ነው የሚሉም አልታጡም ። ይህም ሆኖ ግን በህዝብ ዘንድ መከበር እና መወደዳቸው እስካሁንም ድረስ እንደጸና ነው ።     l



No comments:

Post a Comment