"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Wednesday, 29 August 2012
ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ? ወይስ የለም
የ ”ኢትዮጵያን ሪቪው” ድረ-ገጽ የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዳጅ (አረቡ ቱጃር) ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ ሞተዋል! ሲል የዘገበ ሲሆን ማምሻውን ደግሞ “ኢ ኤም ኤፍ” ድረ-ገጽ የለምሰውየው አልሞቱም ይልቁንም ለመለስ ዜናዊ ቀብር አዲስ አበባ ገብተዋል ባይ ነው።
ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ የለም?
(ኢ.ኤም.ኤፍ.) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የቅርብ ወዳጅ የነበሩት ሼኽ መሃመድ አል አሙዲ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል። “ሼኽ አላሙዲ ሞተዋል” የሚል ዜና በሰፊው ተሰራጭቶ የቆየ ቢሆንም፤ ከአገር ቤት የደረሰን ዜና እንዳረጋገጠው ከሆነ ሼኩ በህይወት መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል። የቅርብ ምንጮች ለኢ.ኤም.ኤፍ. እንደገለጹት ከሆነ፤ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ አዲስ አበባ የገቡት በመጪ እሁድ በሚደረገው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት፤ ሼኽ አላሙዲ ወጪውን ሸፍነው ለማሳከም ጥያቄ ቢያቀርቡም የቀድሞዋ ቀዳማዊ ሴት አዜብ መስፍን ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ፤ አስፈላጊውን ወጪ በማድረግ በሼኹ በኩል ሊደረግ የነበረ ህክምና ሳይደረግ ቀርቷል።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ እና ሼኽ መሃመድ አላሙዲ ወዳጅ የመሆናቸውን ያህል፤ የቀድሞዋ ቀዳሚዋ ሴትዮ ከሼኽ አላሙዲን ጋር አግባብ የላቸውም። ወደፊት በሚኖረው የስልጣን ሽግሽግ እና ሽግግር ወቅት አዜብ መስፍን ወደ ስልጣን የምትመጣ ከሆነች በሼኽ አላሙዲ የንግድ ድርጅቶች ላይ ግልጽ የሆነ ጥቃት እንደምትፈጽም ይጠበቃል። በዚህም ምክንያት በህወሃት አማካኝነት፤ አዜብ መስፍን እንደገና ወደ ስልጣን መውጣቷን እንደስጋት የሚቆጥሩ ውስጥ አዋቂዎች በርካታ ናቸው። እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች እንደገለጹልን ከሆነ፤ “ከእሁዱ ቀብር በኋላ፤ ሼኽ አላሙዲን እንደቀድሞው ወደ ኢትዮጵያ የመመላለሳቸው ጉዳይ ሊቀንስ ይችላል።” ብለዋል በሃዘን።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment