"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 2 June 2012

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!”


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Friday, June 1st, 2012 | Posted by zelalem
ትንሽ ቡጨቃ፤ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!”
3
Share
ሰፈሬ ሽሮሜዳ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠን በርካታ ግዜ በአጋንንት የተለከፉ ፀበልተኛ ወገኖች “ትለቃለህ አትለቅም” በሚለው አስገምጋሚ የአስጠማቂው ቁጣ ሁልግዜም መልሳቸው ከተረበሸ ድምፅ የሚፈልቅ “እለቃለሁ!” የሚል ሲቃ እንደነበር አይቻለሁ። ችግሩ ግን ብዙ ግዜ “እለቃለሁ” ካሉ በኋላም በነጋታው “አብሬያት አድጌ፣ አብሬው ከርሜ” ለማን ትቼው እለቃለሁ” ብለው ድጋሚ ያገረሻሉ። አሁንም አስጠማቂው “አንተ ክፉ መናጢ ትለቃለህ አትለቅም…!?” ሙግታቸውን ይጀምራሉ። መስቀል እና ፀበል ለአጋንቱ ፀር ናቸውና “እለቃለሁ እለቃለሁ…” እያለ ይለፈልፋል። ምሱን ተናግሮ ቀምሶ ጨርሶ እስኪለቅ ድረስ ግን “እለቃለሁ” ስላለ ብቻ አይታመንም!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዘንድሮም “እለቃለሁ!” እያሉ ነው። በእርሳቸው ፍቅር የተለከፍን እኛ፤ “ያለ እርስዎ በሳል አመራር ችግር እና ጉስቁልና ያበስለናልና እባክዎ ይሄንን አሳብ ወደ አዕምሮዎ አያምጡት!” ብለን ብንመክርም፤ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!” እያሏቸው ይገኛሉ።
በተደጋጋሚ እንዳየነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አስለፍላፊያቸው ብዙ ነው። ከዚህ በፊት በፓርላማ ውስጥ፤ ከዛም በተለያዩ የውጪ ሃገር ጋዜጠኞች “ትለቃለህ አትለቅም!” የሚሉ አስለፍላፊዎች አጋጥመዋቸዋል። ያው የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትራችንም ደንብ ነውና፣ ስርአቱ ነውና “እለቃለሁ!” እያሉ በተደጋጋሚ ለፍልፈዋል።  ነገር ግን አለቀቁም።
እኔ የምለው ግን ክቡርነታቸው በርካታ ግዜ “ለቃለሁ” እያሉ ሲተዉት፣ “ለቃለሁ” ሲሉ ሲተዉት ሰዉ ንግግራቸውን አጓጉል ከእርኩስ መንፈስ ጋር እያዛመደባቸው እኮ ነው…!
በነገራችን ላይ ከላይ ያለውን የኪዳነምህረት ፀበል ትዝታዬን ያመጣሁት እንደው ነገር ለማሳመር ብቻ ብዬ አይደለም። በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድ የውጪ ሀገር ጋዜጠኛ “ትለቃለህ አትለቅም?” ብሎ ሲጠይቃቸው “እለቃለሁ!” ብለው በመናገራቸው (“እለቃለሁ” ብለው ሲለፈልፉ…” ልላቸው ነበር! ይቅርታ ከላይም “ለፈለፉ” የሚል ቃል ካለ ከፀበልተኞቹ ጋር ተምታተውብኝ ነውና በጅምላው ይቅርታ ጠይቄ እቀጥላለሁ)
እና ታድያ ጋዜጠኛው በጠየቃቸው ጊዜ “እለቃለሁ!” ብለው ሲመልሱ አንዱ ወዳጄ “አፈር ስሆን ‘ምስህ’ ምንድነው? በለህ ጠይቃቸው እና ያሉትን አቅርበን ቀምሰው በደንብ ይልቀቁን ሁሌ “ለቀኩ እያሉ አያስጎምጁን!” ብሎ የተናገረውን አስታውሼ ነው።
እኔ የምለው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣን መልቀቅ ከአጋንንት መልቀቅ ጋር ማመሳሰል ፍትሃዊ ንፅፅር ነው ትላላችሁ…!?

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!” tokichaw

No comments:

Post a Comment