"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 31 May 2012

ብዙሃን በጥቂቶች አይን

ብዙሃን በጥቂቶች አይን




SHARE THIS
TAGS
Share in top social networks!

ሚያዝያ 30 1997 ዓ.ም የኢትዮዽያ ህዝብ ከዘመናት በሗላ በአገኘው የአንድ የነፃነት ዕድል ሰላማዊ መሆኑን፣ ፍትህ መፈለጉን፣በዲሞክራሲ ማመኑንና ያሻውን የተናገረው ለውጥ ፈላጊነቱን በከፍተኛ ደረጃ ያመላከተበት ለወያኔ ጠባብ ዘረኝነት የጠለቀ ጥላቻ እንዳለው ያሳየበት ቀን ነበረች ሚያዝያ 30 መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ እንደገመቱት ያልተከፋፈለ መሆኑን ያረጋገጠበት ከጦርነት
ይልቅ ሰላማዊ ሽግግር ዘመኑ የሚፈቀደው የፖለቲካ አካሄድ መሆኑን ህዝብ ጠንቅቆ የተረዳ መሆኑን የዘረኛዉ የመለስ ብድን ያወቀበት እንዲሁም ወያኔ እርቃኑን የቀረበት በታሪክ አንድ የነጻነት ቀን ነበር፡፡
ያሰበውና ያለመው በአንድ ቀን እንደ ጉም በኖ የጠፋበት ወዲ ዜናዊ በሳምንቱ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ካየ በሗላ የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ለማፈንና የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም አዲስ አበባን በታንክና በመድፍ ካስወረረው በሗላም ከህፃን እስከ አዋቂ ሴት፣አሮጊት ሳይል በጅምላ የጨፈጨፈው ህዝብን እየዋሸና ባዶ ተስፋ እየሰጠ መቆየት የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም በማወቁ ቀጣዩን የስልጣን ዘመን በሃይል ለማስጠበቅ በማሰብ እነ ሽብሬንና ለሌችንም ንጽሃን ዜጌች ገደለ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ወደ ደዴሳ፣ ዘዋይና ሸዋሮቢት እስር ቤቶች አጋዘ፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በራስ መተማመኑ የጠፋበት አምባገነኑ 
ብድን ከምርጫ 97 በፊት በትንሹ ጭልጭል ትል የነበረችውን የዲሞክራሲ ተስፋ ጭራሽኑ አጥፍቶ በሃይል በስልጣን ላይ ለማቆየት በሚያስችለው መልኩ የጦር ሰራዊቱን በአንድ ዘር በመደራጀት ሥራ ተጠመደ፡፡ ቀደም ሲልም ከትግረኛ ቋንቋ በቀር ሌላ የማይናገሩ ከትግራይ አርሶ አደር ልጆች የተመለመሉ የአጋዚ ሰራዊት ምንም አይነት መረጃ የማይደርሰው ምንም ነገር እንዲያቅ የማይፈለግ ለመለስና ለጭፍሮቹ ፍፁም ታማኝ የሆነና የአለቆቹን ትዛዝ ለመፈፀም ሰልቶ የተቀመጠ ቅልብ ጦር ነው፡፡ የአ/አ ህዝብ የጨፈጨፈው ይህ ጦር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሌላም በኩል መደበኛ ሰራዊቱም ቢሆን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ውስጥ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የሌላው ቢሄር ተዎላጅ ግን በተለያየ ምክንያት እየተገፋ ከስራው እየተባረረና በሰበብ በአስባቡ ወህኒ እየተወረወረ ዘመኑን በስቃይ ይገፋል፡፡ በኢኮኖሚው በኩል በይበልጥ ከምርጫ 97 በሗላ ኢትዮዽያ የነሱ ብቻ እንደሆነች በመቁጠር ዋናዋናውን ወያኔዎች ትርፍራፊውን ታማኞቻቸው በቡድንም ሆነ በነጠላ በማህበር ተደራጅተው ያገሪቱን አንጡረ ሀብት ይቀራመቱታል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ለዘመናትና በብዙ መሰዋትነት ተከብራ የኖረች አገርን ደሃ ዜጎችዋን እያፈናቀሉ በአራት ትዉልድ ለሚለካ ጊዜ ያዉም ይዞት
እስከሚመጣዉ ለትዉልድ የሚተርፍ ችግር ለም መሬታችንን በማን አለብኝነት ለባህዳን ቸብችበዉታል፡፡ የአገሪቱ የማምረቻ አዉታሮች የንግድ ድርጅቶች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሁሉ ወያኔና በወያኔ የዘር ማህቀፍ ውስጥ ያሉ በሞኖፖል ተቆጣጥረውታል ሌላውን ህዝብንም እንደ ባሪያ በመቁጠር ከጫማቸው በታች በማዋል ሲፈልጉ ይሰጡታል ካለያም ይነሱታል በመያዣነት በመጠቀም ድጋፉን እንዲሰጣቸው ያደርጉታል፡፡ ከዚያም ባለፈ የሌላ የፖለቲካ ቡድን ቢደግፍ፣ ቢተባበር በዜግነቱ ማግኘት የሚገባውን የሱ የሆነን ነገር በመንጠቅ ኑሮዉን ያከብዱበታል፡፡
በተለይ በተለይ ከተፈጥሮ ጋር እየታገለ የቀን ጉርሱን የአመት ልብሱን መሸፈን አቅቶት ከአመት አመት በድህነት የሚማቅቀው ገበሬ ዋነኛው የወያኔ የጥቃት ሰለባ ነዉ፡፡ የግብርና ግብአት ለማግኘት ወያኔን መደገፍ ይጠበቅበታል፡፡ ትዝ ይለኛል አንድ ሰሞን ከቻይና የተገኘ ልምድ ተብሎ ውሃ ማቆር የሚባል ፕሮጀክት ተጀምሮ ነበር፡፡ እዚ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ በገበሬ ማህበሩ የወያኔ ድጋፊ (አባል) መሆን መመዘኛው ነበር እሱንም በሗላ የመለስ ቡችሎች ስሚንቶ መነገጃ አደረጉት በአጠቃላይ ግን ግዜ ያልወጣለት የኢትዮዽያ ገበሬ ህይወቱ ሁሉ ያለዉ አሁን ባለዉ ሁኔታ በወያኔ መዳፍ ላይ ሆነዋል፡፡ የሚያርሰዉ መሬት የነሱ፣ ዘር የነሱ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የነሱ፣ አዝመራው አልሆን ብሎት ለርሀብ ቢጋለጥ እንኳን የሱንና የቤተሰቡን ነፍስ የሚታደገዉን እርዳታ የሚያገኘው ያው ከወያኔ ነው በራሱ በገበሬው ስም ተለምኖ ቢመጣም በክፍፍሉ ላይ የዘረኛው ብድን እጅ አለበት፡፡ ይህ ሁሉ ከላይ የተዘረዘረውን አንድ ገበሬ ሊያገኝ የሚገባዉ በዜግነቱ ማግኘት ስለሚገባው ሳዩሆን አሁንባለበት ሁኔታ የዘረኛው ቡድን አባል ፣ደጋፊ ሲሆን ብቻ ነው ካልሆነ ልጆቹን በሞት ይነጠቃል ከዛም እራሱ፡፡ በከተማውም ከምርጫ 97 በፊት ይህ አይነቱ ክፋትና ጨካኔ ቢኖርም የባሰበት ግን ከ97 ወዲህ ነው፡፡ የከተማው ነዋሪም ቢሆን አንድም በበቀል አልያም የወያኔ ተፈጥሮአዊ ባህሪ በሆነው ማን አለብኝነትና አምባገንነት ላለፉት 7 አመታት መከራውን ሲያይ ኖርዋል አሁንም እያየ ነው ፡፡የከተማው ሰራተኛ ክፍል ካሁን በፊት ባልነበረ ሁኔታ በመለስ ተቆጣጣሪነትና አዘዥነት ስራውነ ከማከናወን ለወያኔ ካድሬዎች ከመታዘዝና የለት ተግባሩን ከመከወን የዘለለ የተለየ አመለካከት ቢኖርው ውይም የተቃዋሚ
ድርጅት አቀንቃኝ ቢሆን ቢሳተፍ ቢጠረጠር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከስራው ተባሮ እሱንና በተሰቡን ለችግር ይዳርጋል ባስ ሲልም ስም ወቶለት ወህኒ ይወረወራል፡፡ ለዚህ ከላይ ለጠቀሰኩት መስረጃ እንዲሆነኝ በ አንድ ወዳጄ ላይ የደረሰውን ላወጋችሁ ፡፡ይህ ወዳጄ የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅራቢ ኮርፐሬሸን ውስጥ በከፍተኛ መጋዘን ክፍል አላፊነት ነበር ያገለገለው፡፡ ድርጅቱም ለግብርና ግብአት የሚሆኑ የተለያዩ ማለትም ማዳበሪያ፣ ምርት ዘር፣ የጎሮ አትክልት ዘር እንዲሁም የእንሰሳ መድሃኒቶችንና ፀረ -ተባይ ኬሚካሎችን በማስመጣት ለገበሬውና ለነጋዴዎች የሚከፋፍል ነው ፡፡ ወዳጄም አላፊነቱን በብቃት እየተወጣ ስራውን ያከናውን ነበር ከጊዜ በሗላ የወያኔእረጅም እጅ ስራ ውስጥ እየገበባ አሰቸገረው በመቀጠልም የድርጂቱ አባል ሁን የሚል ተደጋጋሚ ጥሪ ይቀርብልት ጀመር ፡፡ሆኖም
አንድም ስለማያምንበት አልያም በግል እምነቱ ስለማይፈቅድለት ጥያቂውን ሳይቀበል ይቀራል ፡፡ በዚህ ያልተደሰተው የወያኔ የማፍያ ቡድን በመጋዘን ውስጥ ከተቀመጠው እጅግ ውድ ከሆነው የእንሰሳት መዳሃኒት ካልተሳሳትኩ (trypamidium) የባለውን አንድ በዘሩ ትግሬ ከሆነ አለቃው በስልክ እሱ ለሚልከው ሰው እንዲሰጥ ትህዛዝ ይመጣለታል ይህ መድሃኒት ይዘቱ ትንሽ ሆኖ ዋጋው ግን እጅግ በጣም ውድ የሆነ ነው ይህንን ትህዛዝ ለመቀበል የተቸገረው ወዳጄ በስልክ ከሚሆን በደብዳቤ ይሁን ለስራው እንዲያመች በማለት ትህዛዙን ሳይቀበል ይቀራል ይህ በሆነ ሳምንት ባልሞላ ግዜ ውስጥ መጋዘኑ እጅግ በረቀቀ መንገድ ተከፍቶ ይህ የተባለው መዳሃኒት ተዘረፈ ፡፡የወትሮ ስራውን ለመከወን መጋዘኑን ሲከፍት ያስቀመጠውን ያጣው ወዳጄ በሁኔታው ተደናግጦ ለፖሊስ ለማመልከት ከባልደረቦቹ ጋር እየተመካከር ባለበት ሁኔታ ከመቅስፈት የደህንነት ሰዎች መጥተው ይዘውት ሄዱ እናም ቤተሰቡን በትኖ በማያውቀው ነገር እስር ቤት ተወርውሮ በዘሩ እየተሰደበና እየተደበደበ የዘረፋቸው እና የነውራችው መሸፈኛ አደረጉት፡፡ ይህ ነው ባርነት የህይወት ዋስትና ማጣት እኔ ለማሳያ ይህንን አልኩ እንጂ ከዚህ በከፋና በባሰ መልኩ ውድ ህይወታቸውን በዚህ ዘረኛና ማፊያ ቡድን የተነጠቁ ፣ቤተሰቦቻቸውን በትነው ያሉበት የመይታወቁ ወገኖቻችን ቤት ይቁጠራቸው ፡ ፡ በመሆኑም እናታችን፣ መመኪያችን ፣ክብር፣ ኩራታችን እያልን የምናዜምላት ኢትዮጲያ የጥቂት የማፍያ ቡድን መፈንጫ ከሆነች እንሆ 21 አመት ሆናት፡፡ይህንን መቀበልና በ አገሩ ላይ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ አልሆንልህ ያልው ወኔውን አግኝቶ ሲተነፍስ ሲፅፍ ወያኔ እጅግ ከሚፈራቸው ተቃዋሚ ተርታ ይፈረጅና በ አሸባሪነት ተወነጂሎ ቃሊቲ ይወረወራል፡፡ አበዛኛው ግን በ አገሩ እደዜጋ የመኖር ዋስትና ሲያጣ በደህነት እየማቀቀ ፍትህ አጥቶ የበይ ተመልካች ሆኖ በገዛ አገሩ በባርነት ከመኖር በማለት ገሚሱ በ አገሩ ያጣውን ነፃነት ፍለጋ ባህር እያቁረጠ ከፊሉ በረሀ እየሰነጠቀ አገርና ቤተሰቡን ትቶ ይሰደዳል ፡፡ ጥቂቱ በህይወት ቢተርፍም በባህድ አገር እሰር ቤት ይማቅቃል የበዛው ግን ባህር ሰጥሞ አሸዋ ውጦት ይቀራል፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ የሚደርስበት ህዝብ በሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየ አሳቡን በነፃነት የመግለት ሰባዊ መብቱ ተነፍጎት ሲናገርና ሲቃወም አንዴ አደገኛ ቦዘኔ ሌላ ግዜ አሸባሪ እና የመሳሰሉ ስሞች እየተለጠፉበተ ስብእናው እየተገፈፈና እየተጣሰ በተለያዩ እስር ቤቶች ይወረወራል፡፡ በዚህ አይነት
ሁኔታ በ አገር ውስትም ሆነ በውጪ የሚሰቃየውን አበሻ ቤት ይቀጠርው፡፡ የማፍያው ቡድን መሪ ወዲ ዜናዊ የህዝብ የተቃውሞ ድምፅ መስማት አይስማማውም ብዙ ብንሆንም ለ እሱ ጥቂት ነን፡፡ ለ አብነት ያህል ከኑሮ ውደነት ጋር በተያያዘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያቀረቡት የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄን የስርአቱ መሪ የሆነው መለስ ሲመልስ በንቀትና በትህቢት የጥቂት የማስተማር ሞያ ያልተሳካላቸው መምህራን ችግር ነው አለን አንድ ብሉ የህምነት መብታችን ይከብረ ፣መንግስት ከ እምነታችን ላይ እጁን ያንሳ ብልው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለጠየቀው የመብት ጥያቄ ያው በለመደ አፉ ሚሊዮኖችን ጥቂት የ አለቃዪዳ ሴል ያላቸው አክራሪ ውች ጥያቄ ነው አለን
በ አጠቃላይ በዋል ድባ ገዳም ሆነ በጋንቤላ ከመሬታቸው የተፈናቅሉ ንፁሃን ዜጎችን ጥያቄ እነዲሁም ወያኔ በዘራው የዘረኝነት መርዝ ግንባር ቀደም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት በደቡብ ኢትዮጲያ በጉራ ፈርዳ ሀብት ንብረት አፍርተው ከሚኖሩብት ሁሉን ነገር በትነው በግፍ የተፈናቀሉ(የተባረሩ) በሺዎች የሚቆጠሩ የ አማራ ብሄር ተወላጆች ላነሱት ጥያቄ እጅግ ጭካኔው ያልቅጥ ከበዛው መለስ ዜናዊ ያው እነደ ልማዱ ጥቂት በደን ውድመት ላይ የተሰማሩ አማሮች ሲል ነው ለህዝቡ ያለውን ንቅት በሚያሳይ መልኩ የገለፀው ፡፡ ከሁሉም በፊት ነፃነትና ዲሞክራሲ ለዜጎች መልካም አስተዳደር ፍትህና እኩልነት በሃገሪቱ ይስፈን ህዝብ በተለይ ወጣቱ የ አባቶቹን አደራ ይጠብቅ እያለ እያወጀ እየለፈለፈ በመጨረሻም በቃኝ ፍትህ እኩልነትና ነፃነት በሌለበት ሀገር አልኖርም እያለ በራሱ ላይ ቤንዚል አርከፍክፎ አራሱን ያቃጠለው የኔሰው ገብሬ ከዛም በተከታታይ ፍትህና እኩልነት በሌለበት ሀገር አንኖርም ብለው ሰማአት የሆኑት ወንድሞቻችን ነብስ በምን ከቱኒዝያዊው መሃመድ ቡዋዚዝ ነብስ ያንሳል ፣ስለምን ሻማ በማብራትና በወር በመዘከር ብቻ ተወሰንን ዘረኛው የመለስ ቡድን ክቡር ነብሳቸውን ፣ለፍትህና ለ እኩልነት አሳልፈው የሰጡትን ሌላ ስም እየለጠፈ ምግባራቸውን ሲያቆሽሽ ስለምን ዝምታን መረጥን………..  አንድ ሙሃመድ ቡዋዚዝ የለኮሰው ፍትህ የመሻት ነፃነት የመፈለግ ሻማ በጣም የተደራጁና የታጠቁ አራት አመባገነኖችን እየለበለበ ሲያቃጥል ስለ ምን የእነ የኔሰው ገብሬ መሰዋትነት ውሃ በላው የሚደርስብን ግፍና የህዝባችን ሰቆቃ እንደሆን ቢብስ እነጂ አያንስ ኢትዮጲያ የምትባል መልካምድር ውስጥ የተፈጠርን ሁላችን ኢትዮጲያዊ ነን እኛን በዘር በጎጥ በታትኖ በኛ ፍጅት የራሱን እድሜ ሊያራዝም ለሚፈልግ ለዘረኛው የወያኔ ቡድን መሳሪያ ሳንሆን ጥቂት ሆነው ጥቂት የሚሉንን በፅናተ በ አንድነት እንታገል ወያኔ የኛን ዝምታ በመጠቀም ያልነካው ያላቦካው ነገር የለም የኛ የምንላቸው ሁሉ የጥቂት ዘረኛ ቡድን ሆነዋለ ክብራችንን ማሰመለስና ፍፁም ሰላም ፣ዲሞከራሲ፣መልካም አሰተዳደር የሰፈነባት ለሁላችንም እኩል የሆነች ኢትዮጲያን ከዘረኛው የወያኔ ከፋፋይ ቡድን እንቀማው
ኢትዮጲያችን የኛ ነበረች ሁሌም የኛ ትሆናለች፡፡
25-05.2012
ድል ለ ኢትዮጲያ ህዝብ ሞት ለወያኔና ለባነዶች
ከተስፋዬ ዘነበ ከኖርዌይ በርገን

ላሰተያየተዎ፣ ftih_lewegen@yahoo.com  

No comments:

Post a Comment