"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Saturday, 2 June 2012
የማያልፍ ከሆነ እኛ እንለፍ
የማያልፍ ከሆነ እኛ እንለፍ – ተድላ ጌትነት ታፈረ Www.Maledatimes.Com
SHARE THIS
TAGS
ለ20 ዓመታት ቀንን ቀን እየወለደው ነገን ተስፋ አድርገን ግፍና መከራን በፅናት ተሸክመን ያልፋል ብለን ግን ሳያልፍ አገር ጥለን ተሰደድን አንድ የሐይማኖት መጽሐፍ የተኮነኑ ነፍሶች አርብ ወጥተው ሰኞ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ይመለሳሉ ይህ የሚሆነው ሰንበትን ለአከበረ ሰው ነው ይላል ስለነገረ ሰንበት በተነገረ መጽሐፍ ይህ የሚያሳየው ከሲኦልም ዕረፍት ከዲያቢሎስም ምህረት ይገኛል
ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ከዲያቢሎስ የከፋ ከሲኦልም የባሰ የሥቃይ ቦታ የት አለ ከተባለ ከዲያቢሎስ የከፋ ጳውሎስ ከሲኦል የስቃይ ቦታ የባሰ የስቃይ ሀገር ኢትዮጵያ መሆኑዋ አየጠራጥርም ሀገር በተፈጥሮ ክፉ ልትሆን አትችልም ይልቁንም የሚመሯትና የሚኖሩባት ክፉ ያደርጓታል እንጂ በኢትዮጵያ በሁለት አሀዝ ኢኮኖሚው ወድቋል /20/ ሁለት አሀዝ ካልን ወያኔ ይችን ሀገር ለመምራት የተቆጣጠራረበት ጊዜ መሆኑእደሆነ አያጠራጥርም ፡፡ ኢትዮጵያ በዘመኗ ካጋጠማት የሰው ሰራሽ ችግርም ይሁን የተፈጥሮ ከአሁን የባሰ ጊዜ በታሪክ አይታወቅም የነበሩት ችግሮች ጊዜያዊና የሚያልፉ ነበሩ አሁን ግን የነገሮች አቅጣጫና ስልት እየተቀያየሩ መከራውን ማበስ እንጂ ማቃለል ስቃዩን ማጽናት እንጂ ማላላት አልተቻለም ለምሳሌ የሀይማኖቱ መሪ እንመልከት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሀገርን ሀገር
አድርጋ ተከብራና ታፍራ እንድትኖር አሁን የምንዘምርላቸውን የሰው ልጅ እኩልነትንና ተባብሮ መኖርን ተከባብሮና ተቻችሎ መኖርን ያስተማረች የነፃነት አርማ የታሪክ መሠረት መሆኗ አያጠያይቅም መሪዎቹም ቢቻለው ከክፋት ይራቁ በዕውቀት የጠለቁ ለመንፈሳዊ ሥርዓት ቀናኢ የነበሩ ነበሩ አባ ጳውሎስ በቅርቡ < አቶ ታምራት ላይኔ እንደተናገሩት ወደ ስልጣን የወጡት በጦር ታጅበው በቀኖናው ሳይሆን ህጉና ሥርዓቱን አፍርሰው የሕግና የስርዓት ጠላት የሆነው ወታደራዊ ኃይል መከታ አድርገው ወደ ስልጣን ከወጡ 19 ዓመታቸውን ይዘዋል ከዚህ ዘመን የማለፋቸው ጉዳይ ባያስተማምንም
የክፉ እና የአጥፊ ዘመን እረጅም ሰለሚሆን ከዚህም ሊያልፉ ይችላሉ፡፡
በዘመናቸው የቤተክርስቲያንን አንድነት ንደዋል የቅዱስ ሲኖዶስን ስልጣን ሽረዋል ወሮበላ ወንበዴ ቀጥረው አበው ሽማግሌዎችን አስደብድበዋል፡፡ በጋለሞታ የጳጰሳት ክብር ለውጠው የጳጳሳት ውሳኔ በተለያዩ ጊዜ ስለ ጋለሞታዋ ሲሉ ሽረዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የቤክርስቲን ገንዘብ ዘርፈዋል፣ አባክነዋል ገዳማት ቅርሶቻቸው በረቀቀ ስልት ከባዕዳን ነጮች ጋር በምስጢር እንዲሰረቁና በምትኩ ለሳቸው በስማቸው በሲውዝ ባንክ ገንዘብ ገቢ እንዲደረግላቸው እድርገዋል ብዙ ቅርሶች ተዘርፈዋል የስርቆት መረቡ የተዘረጋው ከሳቸው በሚሰጠው መመሪያ መሆኑን በአክሱም ዕቃ ቤት፣ በደብረዳሞ ዕቃ ቤት፣ በአዲስ አለም ዕቃ ቤት፣ በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ዕቃ ቤት የተፈፀመው የከበሩ ዕቃዎች ስርቆት የሩቅ እና የቅርብ ጊዜ ትውስታዎች ናቸው፡፡ ለግብጽ ጳጳሳት ስጦታ ሰጠን እንጂ ንብረቶቻችን ተሰርቀው አልሂዱU ተጠብቀው ነበረ የነበረው አሁን ግን መልኩ ኢትዮጵያ ግብሩ ዲያቢሎሳዊ የሆነ ፓትሪያሪክ ለታሪክ የተቀመጡ ቅርሳችንን በፖሊስ እንዳይያዝ ፖሊሱ እሱ በህግ አንዳይዳኙ ከህግ በላይ የሆነ ዘመን ያደነደነው የተቆራኘው ክፋትና ጥፋት ዕውቀትና ክብሩ የሆኑ ቅርሶችን ለሽያጭ ምሁራንን ለስደት እየደረገ ድፍን ሁለት 10 ዓመታት አስቆጠርን በርግጥ ጥላችን ስርአቱ ነው ይህን ክፉ ሰው
የወለደው ይህ የጭቆና ሥርዓት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የት እንጩህ ዘመን ከዳን እግዚአብሔር ዝም አለን በሀገራችን እንደስደተኛ ተቆጠርን ለእኛ ሁሉም አለም ተመሳሳይ ነው የሀይማኖት መሪ ሲበድል የሀገር መሪ ዘንድ ይከሰሳል የሀገር መሪ ሲበድል በሀይማኖት መሪ ይወቀሳል መሰማማት ይኖራል እኒህ የተወለዱ ከዚያ መንደር ያደጉት በዚያ ዘመን የሚያለሙት ጥፋትን በሀገር ላይ የሚዶልቱት መበታተን የሚደሰቱን ዜጎችን በማሰቃየት ነው ሌላው አለም የሚአውቃቸው አስመሳይነታቸው እንጂ የረቀቀ ክፉነታቸውን አይደለም. ሀገር እየበታተኑ ዜጎችን እያሰቃዩ በዕስር ወይም በርሀብ መገደልን
ጀብድ አድርገው የሚኖሩ ናቸው ታዲያ የት እንጩህ አስመሳይነታቸውን ለማጋለጥ ሰው የሚመስሉ ሰይጣኖች መሆናቸውን ለመግለጽ ቃላት አጠረን ጊዜ አፍን የገንዘብ ኃይል አቅማችንን አደከሙን እየጮኸን ብዙ ጊዜ የስሙን አቅማቸው አነሳ እንደኛው ከመጮህ ያለፈ አቅም የሌላቸው ሰብዓዊ መብቶች ናቸው ኃያላኑ ፀረ – ሽብር በሚለው ሀሳብ ተዋጡ ርካሽ የሚሞት ኢትዮጵዊ ወታደር ፍላጎት ያዛቸው በሰው ሀገር ያለ ያላአንዳች ጥቅም ዜጎችን የሚያስጨርስ ጨርሶ ስለማያገኙ የኛዎቹ ጨካኞች በጭካኔያቸው ወዳጅ አፈሩ ታዲያ የት እንጩህ ሓያላኑ ለጥቅማቸው ዝም ካሉ የኛም ጩኸት
ከንቱ ከሆነ ጎበዝ እኚህ ጨካኞች የመጡበትን በርሀ እኛም እንጓዝበት እንጂ ምን ትላላችሁ!!
Abune Paulos, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, visiting his monastery in Tigray. Ethiopia www.maledatimes.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment