"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 7 November 2012

አስቸኳይ እና አንገብጋቢ ዜና

ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ፌድራል  በሽብር ላይ
ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን መረጃ እውነትን እና ፍትህን ለሚሹ ሁሉ በማዳረስ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ ፡፡ኢትዮጵያ ሙስሊሞች እየደረሰባቸዉ ያለው የመብት ረገጣ ለማስቆም ለሚመለከተው የመንግስት አካል ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ እና መፍትሄ እንዲያፈላልጉ በሃገር እና ከሃገር ውጭ በሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የተወከሉትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን መንግስት በማን አለብኝነት ወህኒ ቤት እንደወረወራቸው ይታወቃል ፡፡ፍርድ ቤት አቅርቦም ስላም እና ፍትህ ሲሰበኩ የቆዩትን ተወካዮቻችንን ሰላም አደፍራሽ ናቸው ፤አሸባሪ ናችው ፤ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነበር ፤በማለት በሃሰት ክስ አቅርቦባቸዋል ፡፡
ለዚህም ቅጥፈቱ መረጃ እንዲሆነው በገንዘብ በርካቶችን መግዛቱ ማርጋገጥ ችለናል ፡፡በተጨማሪ ለመላው የሃገራችን ህዝቦች ኮሚቴዎቹ ሌላ አጄንዳ እንደነበራቸው ለማስመሰል እና ሙስሊሙ ህብረተስብ በኮሚቴዎቹ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበት ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ ፕሮፖጋንዳ በህዝብ ላይ በማሰራጨት የሚታወቀውን ኢ.ቲ.ቪ ን በመጠቀም ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ፡፡
ኢ.ቲ.ቪ ከመንግስት በተሰጠው መመሪያ መሰረት ለወራት ያህል በኮሚቴዎቹ ላይ የሚያጠነጥን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የሚ ነዛ ዶክመንታሪ ፊልም በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡እነሆ በቅርብ ቀንም ይፋ ሊደረግ እንደሆነ ሰምተናል ፡፡ ይህ ዶክመንታሪ ፊልም ኮሚቴዎቻችን ከመታሰራቸው በፊት በአወልያ ቅጥር ግቢ በመንግስት ሃይሎች ከተፈፀመው የግፍ እርምጃ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ የተሰሩ ድራማዎችን አካቶ ይዛል ፡፡
ይህ ዶክመንታሪ ፊልም በአወልያ ግቢ ውስጥ መንግስት ራሱ የቀበራቸውን መሳሪያዎች ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለጅሃድ ያዘጋጃቸው እንደነበር በማቅረብ በማቅረብ ክርስቲያን ውገኖቻችን ለማስበርገግ ታሰቧል ፡፡መንግስት ኮሚቴዎቻችንን ለክሰሰበት ወንጄል ማስረጃ እንዲሆነው ማዕከላዊ እስር ቤት አብረዋቸው ታስረው የነበሩ ሙስሊሞችን በከፍተኛ ሁኔታ በመደብደብ እና በማሰቃየት መንግስት ኮሚቴዎቻችንን የከሰሰበት ክስ ትክክል እንደሆነ እና በኮሚቴዎቻችን ላይ በሃሰት የእምነት ቃላቸውን በመስጠት እንዲመሰክሩ በማድረግ ለዶኩመንታሪው ግብዐት አድርጎታል ፡፡እንዲሁም ኮሚቴዎቻችን በምርመራ ላይ በነበሩበት ስዐት በድብቅ በመቅረፅ ዶኩመንታሪ ፊልም እንዲመች አድርገው ቆራርጠው እንዳዘጋጁት ሰምተናል ፡፡
በተጨማሪ የሃሰት ሰነዶችን በማዘጋጅት እና የሃሰት ምስከሮችን በማዘጋጀት ኮሚቴዎቻችን ከውጭ ሃይሎች ጋር የተቀነባበረ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ይሰሩ እንደነበር ለማስመሰል የተቀናጀ የሃሰት ድራማ እየሰሩ ይገኛሉ ፡፡በመሆኑም ይህንን ድራማ ህዝብ ዘንድ ከመድረሱ በፊት የማሳወቅን ስራ እንድንሰራ በአሏህ ስም እንጠይቃልን ፡፡ ይህ የሃሰት ዶክመንታሪ ፊልም ህዝቡ ዘንድ ከደረሰ ቀላል የማይባለ አደጋ በሙሰሊሙ እና በክርስቲያኑ ህብረተሰብ ላይ ስለሚያደርስ ከወዲሁ ሳንቀደም እንቅደም የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን ፡፡
ሁላችንም ይህንን መልዕክት ካነበብን በሃላ ሌሎችም ኢትዮጵያ እንዲሰሙት በማደረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ ፡፡ እውነት እያደር መጥራቱ አይቀርም እና እውነትን ለማንገስ የበኩላችንን እናድርግ ፡፡
መረጃው የደረሳቸው ኢትዮጵያ ሙ ስሊሞች

No comments:

Post a Comment