"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 18 May 2012

የሕሊና ዳኝነታችን አሁን መሆን ያለበት በሙዚቃ ጥበብ ለነፃነት ፍቅር ወይስ ለሥጋ ክብር??? በአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወ-መንፈሳዊ



March 26th, 2012 ይመይሉ ይመይሉ ያትሙ ያትሙ
የገዛኽኝ ተሾመ [[Ethiopian...Gonder]] “ትዝ አለኝ” እና የጎሳዬ ቀለሙ [[''Gosee ( Jacky ) - Chirash ጭራሽ']]’”ጭራሽ” የሙዚቃ ጥበብ ለየቅል ሆኖ የተኮተኮቱበት ብቻ ሳይሆን የጠጡበት ባሕላዊ የቅላፄ ጥበብ አንድ ዓይነት ቋንቋ ነው፦አማርኛ ከጎንደርኛ።ሁለቱንም ድምፃውያን በሙያቸው የማከብራቸው ናቸውና የሰው መውደድ አንድዬ በላይ በላዩ ጨምሮ እንዲያጎናፅፋቸው እመኝላቸዋለሁ።ይህም ጦማር ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ይህን ድህረ-ገፅ ለሚያነቡ አገር-ወዳዶች በሙሉ ነውና ተረዱልኝ።የመንገነዘበው ጥበብን ይምሰል እንጂ በነፃነታችን ትግል ምክንያት እንኳን ሰልፍን ሙዚቃዎቻችንንም ማሸማቀቃችንን እንድንገነዘብ ነው።
ወደዋናው ርዕሴ ስመጣ ሰዎች አንድ የተመረተን የሙዚቃ ጥበብ ለመኮምኮም በጆሯቸው ጠልቀው በዓይነ-ህሊናቸው ሲምጉ ጣዕሙ ከብርንዶ የበለጠ ሕሊናን ያጣፍጣልና የሥጋዊ ልቦናን ከመንፈሳዊው መንጥቆ እንደ አቅሙ ይፈታተናል።የዚህ ፅሁፍ መነሻ ምክንያቶችም ሁለት የተለቀቁ እና የተለያዩ በጥበብ ግን አንድ የሚመስሉ የሥጋዊ ዘፈኖች ናቸው። በመሠረቱ ጀግና እንኳን ሥጋው ወኔው በፍቅር የሚጦዝ ግለት አለውና ጀግና አያፈቅርም ብለው የሚናገሩ አይደለም:- በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያስቡ ሰዎች ካሉ ሥጋ እና መንፈስን ጠንቅቀው የማያውቁ ናቸውና ደጋግመው ስለፍቅር ሊያስተውሉ ይገባል እላለሁ።የእኔም የሕሊና ዳኝነት ጠልቆ በረቂቅ የተመለከተው በዘፈኖቹ የጥበብ ሥራ ብቻ ሳይሆን የዘፈኖቹ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት አድርጎ እንደሚያጣጥማቸው ነው።የእኔን አመለካከት በቀናነት ተገንዘቡልኝና እስኪ እንደ እኔ ሕሊና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘፈኖቹ ላይ ያለውን አንድምታ ልብ በሉልኝ።                                                lerefte yahel yehenen musica yadametu

በመጀመሪያ የገዛኽኝ ተሾመ “ትዝ አለኝ” “ከ ዩ ቲዩብ” ላይ æ [[Ethiopian...Gonder]] ስሙት አላልኩም፦ በሕሊናችሁ አኝኩት።የመይሳው ካስን የመረረ ትግል እና ለነፃነታችን የከፈለውን የሕይወት ዋጋ እየተረከ ያመላክተናል።ልብ በሉልኝ ለኢትዮጵያ አንድነት ብሎ በድንኳን ውስጥ እድሜውን ስለአሳለፈው ጀግና ነው የሚዜመው። ||| የዛሬ ሃያ አመት በሰላም ሥም የእያንዳንዱን መሳሪያ ከሕዝቡ ሰብስቦ መሳሪያ ስለያዘ ብቻ ዛሬ እኛ ነፃነት ጠምቶን ዘረኛ የጉጅሌ ቡድን ሲያስታውክብን በጊዜው ጀግና ነኝ ብሎ ዛሬ ዛሬ ይፎልላል፦ቀኑ እንዳለቀባቸው ግን አምግንባገንኖች አያውቁምና እንደ ጋዳፊ የጉጅሌው ቡድን መሪ ለገሰ ዜናዊም በቅርቡ ዋጋውን ያገኛል።|||
በተለይም “ትዝ አለኝ”የሚለው ዘፈን ምን ያህል ወቅታዊ እና አስፈላጊ እንደሆነ ልንረዳ የምንችለው ለነፃነት ካለን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አንጻር ነው።ሃያ ዓመታት በሙሉ ኢትዮጵያ ጀግና አጥታ በጦር ሙያ ቢያንስ ሊከላከልላት የሚችለው የሠራዊት አባል በየጓሮው አትክልት ሲያጠጣ በየመንደሩ ንግድ ቤት ከፍቶ በመሽቆጥቆጥ ዕድሜውን ሲገፋ እነታማኝ በየነ ከጎንደር ተወልደው የሰብዓዊ መብት ካባ ደርበው ያገር ያለህ እያሉ ይጮሃሉ።አንዳንዴም ታማኝ በየነ በሙያው እያስፈገገ”ምነው ጎበዝ ነውር አይደለም…?”እያለ ሐቁን ሲያግት እነሻምበልም ሆነ አበበ በለው ዳዊቶችም ሆኑ ተክሌዎች ከፕሮፌሰሮች ጋር ተሰልፈው በቆረጠ የትግል መስመር በደፈጣ እና ባደባባይ ሲሟገቱ እነሆ ዓመታት ነጎዱ።እናም ገዛኸኝ የዘፈነው በቅላፄ ጥበብ የተከሸነው”ትዝ አለኝ”ዘፈን የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይኮረኩር ወይም እንዲኮረኩር ሆኖ ስላልተጋበዘ ከአጥንት ተራ ወጥቶ እንደ ሌላው ዘፈን”ላሌ-ጉማ” እንደ የሺ ሐረጊቱ ወደ አሮጌ መጋዘን መንደር ተወረወረ።ይሁን እንጂ የሙዚቃውን ጥበብ ጠልቆ በማየት ያስተዋለውም ይሁን አጋዦቹ ቆፍረውለትወጣቱ ጎሳዬ ቀለሙ ዘፈኑን በፍቅር ግጥም አሟሸና በዘመናዊ ውዝዋዜ እና በዳንስ እያስነካ ደረት በሚያስገለብጥ እስክስታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነሆ ብሎ ባደባባይ ተጠበበት።ይሄኔ ከሙዚቃው ጠበል ይድረሰን ለሚሉ የሕዝብ ልጆች ሁሉ ንዋይ አፍቃሪዎች አይናቸውን በለጠጡና በተቀመጡበት የነፃነታችን ትከሻ ላይ ንግዳቸውን አጧጧፉበት።ለጃኪ(ጎሳዬ ቀለሙ)አኪር ገባለት ነው የሚባል።ኢትዮጵያ አልቀረውም እስራኤልን አልፎ ኤሮፕ ተሸልሞ አሁን ደግሞ አሜሪካን ሊያስሥ ነው፦እንኳን አደረገለት።እነዚያም ተወዛዋዦች ዋጋ ያጣሉ ብዬ አልገምትም፦ይሁንላቸው።
ወደ ተነሳሁበት የጥበብ እይታ ልመልሳችሁና በሙዚቃ ሕይወት ውስጥ ሲኖር ዜማን ማጣጣም ግጥምን ማላም ውህደታቸውን መመረመር ቅላፄአቸውን መፈተሽ ግዴታ ነውና ሁለቱንም ዘፈኖች እናነተው በሰከነ ልቦና አዳምጧቸው።ምን ዓይነት አንድነት እና ልዩነት እናዳላቸው ሰምታችሁ አይታቸሁ ፍረዱ።በእኔ በኩል ግን ሁለቱም ለፍቅር ያዜማሉ፥ገዛኸኝ ስለአገር ፍቅር ለተቃጠለው እና ጃኪ(ጎሳዬ ቀለሙ)ደግሞ የሥጋ ፍቅር ላቃጠለው።በጭፈራውም ባሕላዊው ውዝዋዜ የገዛኸኝ ነው፦በአንፃሩም የሚያምረው ዘመናዊ-ባሕላዊው ውዝዋዜ ደግሞ የጃኪ ነው።ሁለቱም ግን የተሰሩት ለኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያውያን ነው።ጥያቄው ግን እውን ነፃነት በሕሊና ዳኝነት ፀይን ዋጋው ከሥጋ ፍቅር ያንሳል???
ዕውነት ነፃነት የሚያንስ ከሆነ በፍፁም ጀግንነት አይኖርም፦እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ጀግኖች ነበረን።
መረጃችን መጽሐፍ ቅዱስ:- መዝሙረ ዳዊት ፷፰-፴፩ ታሪክ ደግሞ ምሥክራችን ነው።

No comments:

Post a Comment