"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 3 November 2012

በመከላከያ የጀኔራሎች ፍጥጫ


በመከላከያ የጀኔራሎች ፍጥጫ(እየሩሳሌም አርአያ)
በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል።በአንጻሩ ጄ/ል ሞላ ወደ አየር ሃይል አዛዥነት ከመምጣታቸው በፊት የላቀ ጀብዱ እንደፈጸሙ ምንጮች ጠቁመዋል። በሻእቢያ ጦርነት ወቅት ኰ/ል ማእረግ የነበራቸው ሞላ በባድመ፡ አስመራ፡ተሰኔ….በመሳሰሉ ከባድ ውጊያዎች ላይ የጦር ጄቶችን በማብረር ሻእቢያን ድባቅ የመቱ ኢትዮጵያዊ ጀግና ናቸው።
ጄ/ል ሞላ ለአቶ መለስና ለሳሞራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበራቸው ሲታወቅ በተለይ በጦርነቱ የተፈጥጸመው ሴራ፡ አሰብ ወደብን ለመያዝ የተነደፈው ፕላን መኮላሽትን ጨምሮ ባድመን እንስጥ የሚለውን ባለ 5 ነጥብ የክህደት አጀንዳና ሌሎች የነመለስ - ሳሞራ ሕገ ወጥ አካሔዶችን አጥብቀው ያወግዙ እንደነበረ ተጠቁሞል። « በራሱ እምነት የሚጉዝ ጠንካራ ሰው» ተብለው በባልደረቦቻቸው የሚሞካሹት ጄ/ል ሞላ ያራምዱት በነበረው አቁዋም በነመለስ- በረከት ጥርስ ተነክሶባቸው ቆይቶዋል።ከዚያም ባለፈ « የአንጃ ደጋፊ» በሚል ተገምግመዋል። ቢሆንም ግን ከአቖማቸው ዝንፍ ሳይሉ ቖይተዋል።

      ከጄ/ል ሞላ ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበሩትና የአየር ሃይል ባልደረባ የነበሩት ኰ/ል ክብሮም በ1996ዓ.ም የመለስን - ባድመን አሳልፎ የመስጠት አጀንዳ በመቃወም ሰራዊቱን ሰብስበው እንዲያወግዝ የማነሳሳት ጥሪ በማድረጋቸው አንዲባረሩ ተደርጎዋል። በ1999 ዓ.ም  ማእረጋቸው ተገፎ እንዲባረሩ የተደረጉት የቀድሞ የአየር ሃይል አዛዥ ጄ/ል አለምሽት ደግፌ ፡ መጀመሪያ ያራምዱት የነበረውን - መለስን የመደገፍ አቁዋም በመተው መቃወም በመጀመራቸው ውሳኔው ሊተላለፍባቸው ችሎዋል። ጄ/ል አለምሽት ከስልጣን ከመነሳታቸው በፊት አንድ አስገራሚ ነገር ሰርተዋል፤ በ1993 ዓ.ም የአቶ መለስን ተሃድሶ በማውገዝ ጥለው የወጡት ጄ/ል ታደሰ በርሄ (ጋውና) እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « መታሰር አለባቸው » ሲሉ በወቅቱ የተከራከሩት ጄ/ል አለምሽት ከጊዜ በሁዋላ ለሁለቱም የቀድሞ ባለስልጣናት ስልክ ደውለው ይቅርታ መጠየቃቸው ነበር። « በናንተ ላይ ሳራምድ የነበረው ተግባር አሳዝኖኛል፤ የመለስን አካሄድ ያወቅኩት ዘግይቶ ነው።ይቅርታ አድርጉልኝ።» እንዳሉዋቸው ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል። በነገራችን ላይ አለምሽት ቦሌ አካባቢ በየእለቱ መጠጥ ሲጎነጩና ሲበሳጩ ይታያሉ።
በአለምሽት ቦታ የተተኩት ጄ/ል ሞላ ለ4 አመት አየር ሃይልን ሲመሩ ከቆዩ በሁላ መነሳታቸው ከጀርባ ያለውን ከባድ የፖለቲካ ሽኩቻ
ወደከፋ ጫፍ እንደሚያሽጋግረው የቅርብ ምንጮች ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ጄ/ል ሞላ በአየር ሃይልና በመከላከያ በርካታ ደጋፊዎች  እንዳላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
    በሌላም በኩል ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ በአንድ የአየር ሃይል አንጋፋ መኮንን ላይ የፈጸሙት አሳዛኝ ድርጊት ይገኛል። መ/አ ለማ ይባላሉ፤የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ለ25 አመታት በአየር ሃይል አገልግለዋል። በኢትዮጵያ በግራውንድ ስኩል እንዲሁም በሩሲያ ከፍተኛ ስልጠና ወስደዋል። ኤል-39 የመለማመጃ አውሮፕላን ሴፍቲ ሃላፊ ነበሩ። ከተግባርድ ጀርባ ኪራይ ቤቶች በሰጣቸው መኖሪያ ተከራይተው ይኖሩ ነበር። በ1996ዓ.ም ለውሽማቸው ቤቱን መስጠት የፈለጉት ጄ/ል መሃሪ መ/አ ለማን ቤቱን ይጠይቃቸዋል፤ « ለምን እለቃለው?» በማለት እምቢ ይላሉ። ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ለማስፈራራት ይሞክራሉ። ለማ ግን አልተበገሩም። ጄኔራሉ የአየር ሃይል ኤር-ፖሊሶችን በማሰማራት መ/አ ለማ በመኖሪያ ቤታቸው በምሽት ያስደበድባሉ። በአጋጣሚ ፓትሮል የሚዞሩ ፌደራል ፖሊሶች ደርሰው ያስጥሉኣቸዋል።
        መ/አ ለማ ለደታ ፍ/ቤት ይከሳሉ፤ ደብዳቢዎቹ ፍ/ቤት ቀርበው ሲጠየቁ « ወዲ ዘውዴ ነው የላከን » ይላሉ። ከዚያም ጄ/ሉ ተከሰሱ፤በአስገራሚ ሁኔታ ፍ/ቤቱ ክሱን በማቓረጥ «ጉዳዪ በወታደራዊ ፍ/ቤት ነው መታየት ያለበት» አለ። መ/አ ለማ በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ አንድ ጆሮቸው አይሰማም፤ኩላሊታቸውና እግራቸው ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበረ፤ የሃኪሞች ቦርድ « መስራት እንደማይችሉ  በመግለጽ ቦርድ እንዲወጡ ወሰነ።
             ሜ/ጄ ሞላ ኃ/ማርያምይህን ተከትሎ ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ባሳለፉት ቀጭን ትእዛዝ መ/አ ለማ እስር ቤት ተወረወሩ፤በየቀኑ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸው ነበር።ክእስር ቤት በተደጋጋሚ ደብዳቤ ጽፈዋል፤ በወቅቱ የመከላከያ ሚ/ር ለነበሩት አባዱላ ገመዳ ጭምር የአቤቱታ ጥሪ አሰምተዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።መጀመሪያ በአየር ሃይል ከዛም በታጠቅና ናዝሬት እስርቤቶች የታሰሩትና ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የተፈራረቀባቸው መ/አ ለማ መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም።
                                                                                   ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
                                                                                  November 2, 2012

No comments:

Post a Comment