"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 18 December 2012

የፀጋዬ ግጥሞች 2ኛ

የፀጋዬ ግጥሞች ልክ እንደ ማንኛውም ግጥም ይዘታቸው የተለያየ ነው። ነቢይ መኮንን ከጠቃቀሳቸው
የተወሰኑትን እናያለን። በመጀመሪያ ግን እስኪ የፀጋዬን የእንግሊዘኛ ግጥሞች
8
እንቋደስ።5
« »
A lover love-rejected
With a spirit dejected,
A monk God-forsaken
Whose total faith is shaken,
Are less lost than dreamer
Into whose peace a “question”
Plunged like a knife
And woke him to life,
To search, to find his way
To dodge, to fight his way
Not dream it away!
« ?»
I did not know, oh Sir that I stood on your way
It all happened in chance; argument is unfit,
If we fight, others will benefit,
And as this road is also where my future lay,
Destiny forces me to answer you with “Nay”
Pray lose no temper; lest you commit
A risk to result in a regrettable wit,
For, if there be crime, guilty is just the day;
I am also in yours as you are in my shoes
So do let us shift Sir, to either side
However painful it becomes, we should, though
We realize that it isn’t much to lose
That in spite of us the way is wide 6
And that after all, some day, both of us go.
« »
Showers of anguish
Rain, do not exhaust
Ocean of revenge
Of the innermost
Voice of the betrayed
Comfort of the lost,
Tears torn itself
Blood of the heart.
« »9
I am the first Earth Mother of all fertility
I am the Source I am the Nile I am the African I am the beginning
O Arabia, how could you so conveniently have forgotten
While your breath still hungs upon the threads of my springs
O Egypt, you prodigal daughter born from my first love 
I am your Queen of the endless fresh waters
Who rested my head upon the arms of Narmer Ka Menes
When we joined in one our Upper and Lower Lands to create you
O Sudan, born out of the bosom of my being
How could you so conveniently count down
In miserable billions of petty cubic yards
The eternal drops of my life giving Nile to You
Beginning long before the earth fell from the eyeball of heaven.
O Nile, that gush out from my breath of life 7
Upon the throats of the billions of the Earth’s thirsty multitudes,
O World, how could you so conveniently have forgotten
That I, your first fountain, I your ever Ethiopia
I your first life still survive for you?
I rise like the sun from the deepest core of the globe
 I am the conqueror of scorching pestilences
I am the Ethiopia that ‘stretch her hands in supplication to God’
I am the mother of the tallest traveler on the longest journey on
Earth
...
ለአባይ ቅኔ ያልዘረፈለት ተቀኚ፣ ስንኝ ያልቋጠረለት ገጣሚ፣ ቃላት ያልደረሰለት ደራሲ፣ ያላዜመለት ድምፃዊ፣
ያልተጠቀሰለት ምሳሌ፣ ወዘተ ...  የለም። ሲሻገሩት አድንቀውታል። አምላኪዎቹ ሰግደውለታል -  ጪዳ
ገብረውለታል። በምንጩ ምንነት ተከራክረውብታል -  ሁሉም አወድሰውታል።
10
ግና ማን እንደ ፀጋዬ።
እንዲያው እንግሊዘኛውን ትተነው የአማርኛ የአባይ ግጥሙን እስኪ እንይለት። ትንግርት ነው የፀጋዬ አባይ። 
«አባይ»
አባይ የምድር ዓለም ሲሳይ 
የቅድመ - ጠቢባን አዋይ 
የኢትዮጵያ ደም የኩሽ እናት 
የዓለም ስልጣኔ ምስማክ 
ከጣና በር እስከ ካርናክ 
በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ 
ለራህ ለጸሐዩ ግማድ ፣ ለጣህ ለከዋክብት አምላክ 
ከጥንተ ፍጡራን ጮራ፣ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ :: 
አባይ የምድረ- ኩሽ መኩሪያ 
በቅድመ ታሪክሽ ጥርጊያ 
ከደም-ቢያ እስከ ኑ-ቢያ 
ከሜምፊስ እስከ ሜሮኤ 
በስልጣኔሽ ትንሳኤ 
ከዴልታሽ እስከ ዴር- ሱልጣን 
ከኡመ-ራህ እስከ ኡመ-ዳርማን ፤ 
አባይ የአቴስ የጡቶች ግት 
ለአለም የስልጣኔ እምብርት ፤ 8
ጥቁር አባይ የጥቁር ምንጭ 
የካም የስልጣኔ ፍንጭ ፤
አንቺ የምድረ ዓለም ሲሳይ 
በረሀውን ጥለሽ ግዳይ 
ሰሀራን እንዳክርማ ተልም 
ሰንጥቀሽው በወዝሽ ደም፤ 
በጥበብሽ ስርወ - ፍና 
አንቅተሽ ባንቀልባሽ አዝለሽ፣  የቅድመ ታሪክን ዝና 
የራምሴስን አበ -ሲምቦል፣ የመነስን ልዕልና 
በአልፋ የአልሙጋን ሐውልት፣ የቢያ-ሀንኬን ፍልስፍና 
በኮማምቦ የሶባቃን፣ በናፓታም የኤዛና 
ፈላኤ የአቴስን ምኩራብ፣ በልቅጾር የአሞንን ዜና  
አባይ ታላቅ ቅድመ ተስፋ 
የኪነት ጉባኤ አልፋ 
ረቂቅ አባይ ያንቺ መገን 
ምጥቀትሽ አይተነተን
የእጅ ማስነሻሽ በረከት 
ግብርሽ ከአድማሳት ሲከትት 
መንጣለያሽ ከእለት እለት 
መሻገሪያሽ ካመት - ዓመት 
በመስዋዕት ሲወድቅልሽ 
በዝማሜ ሲፈስልሽ 
በመመለክ በመመስገን 
ጽላትሽ ከዘመን ዘመን 
በአዝርዕት አበቅቴሽ ሲታጠን 
አቤት አባይ ላንቺ መገን፤
አባይ ረቂቅ የጠቢብ ዘንግ 
የክዋክብትን ሰልፍ ደርግ 
የጨረቃን ጉዞ ፈለግ 
አስቀምረሽ በጠቢብ ዘንድ 
በፍሳሽሽ ውጣ ውረድ 
በሙላትሽ ሚዛን ረገድ 
የሰማይን ጥርጊያ መንገድ 
የጊዜ መለኪያ ሰዓት፣ ዚነት ባንቺ ተቀምራ 
ከቴቢስ እስከ ዳንዳራ 
ብስራትሽን እንደ ደመራ 
ስልጣኔሽ እንዳበራ  
የመጽሀፈ ሙታን ዜና 
አድርጎሽ ቅድመ -ገናና 
ዛሬ ወራቱ ራቀና  9
ምድረ -ዓለም ያንቺን አድናቆት 
ፈለጉን መሻት ተስኖት 
እንዲህ ባንቺ መንከራተት 
ታሪክ ወሮታሽ ጠፍቶበት 
ትላንት በባዕድ ጩከት 
ዛሬም ባላዋቂ ሁከት 
ቋንቋ ለቋንቋ ቢራራቅ 
የቅድሚያሽ ንድፍ ላይፋቅ 
እዚህ ደማም እዚያ ተማም 
መባልሽ ብቻ ባይበቃም 
የቅርስሽ ጭብጥ ይዞታ 
ሆሄታሽ እስካልተፈታ 
አባይ ፋናሽ የሕልም ሩቅ 
ፈለግሽም ቢሆን ደቂቅ 
እንዴት እንዴት ነበር ብለን 
ካልደረስንበት ፈልፍለን 
የጥንትዋ አባይ እንዴት ትሆን 
አባይ -አቢይ አባይ -ግዮን 
ከምንጭዋ የጥበብ ሳሎን 
ግሪክ ፋርስና ባቢሎን 
ጭረው በቀዱበት ሰሞን፤ 
አባይ የአማልክት አንቀልባ 
የቤተ -ጥበባት አምባ 
ከኩሽ የቅድመ -አበው ብሂል 
ከተራራሽ አናት ቁልልቁል 
የሰው ዘር የታሪክ -ፊደል፣ ገና ከጽንሱ ሲረቀቅ 
ሊሰይምም የእትብቱን ቆባ፣ ምጥቀቱን ለማንጸባረቅ 
ዘለዓለሙን ለማሳወቅ 
እስከሜዲተራኒያ፣ ጢስ እሳትሽ ሲፍለቀለቅ 
አባይ አቢይ፣ አባይ ግዮን 
ለአማልክቶች አምላክ ለአሞን 
የኪነት ምንጩ እምትሆን፤
ለአሩስ ርቱእ አክናፋት 
ለነዳዮናይሶስ አባት 
ከእምብርትሽ የጸሀይ አምላክ ; ተቀስቶ በሰማያት 
ያረበበብሽ እንደ እሳት 
ጥቁር አባይ የጥቁር ምንጭ 
የካም የስልጣኔ ፍንጭ 
የቅድመ ታሪክሽ ጥርጊያ 
ከደም -ቢያ እስከ ኑ -ቢያ  10
የኢትዮጲስ ደም የኩሽ እናት 
አባይ የጥቁር ዘር ብስራት 
የዓለም ስልጣኔ ምስማክ 
ከጣና በር እስከ ካርናክ 
በጡትሽ እቅፍ እንዲላክ 
ለራህ ለጸሀዩ ግማድ፣ ለጣህ ለክዋክብት አምላክ 
ከጥንተ -ፍጡራን ጮራ፣ የመነጨሽ ከኩሽ አብራክ 
ሰሀራን እንደ ምሁር ተልም 
ያለመለምሽ በወዝሽ ደም 
የቅድመ -ጠቢባን አዋይ 
አባይ የምድር ዓለም ሲሳይ :: 
ሲያሻው በእንግሊዘኛው ሲያሻው በአማርኛ ግጥም ለፀጋዬ ተገርቶለታል እዚያ አምቦ ጠበል ሲጠመቅ የቋንቋ
አማልክት ተገልጠውለት ይሆን።
ፀጋዬ በግጥሞቹ ይዘት ማህበረሰብ ነክ ችግሮችን እንዲህ በምናባችን ይዶላቸዋል። «ይድረስ ይድረስ  ለወንድሜ   ለወንድሜ  
ለማላውቅህ» አይነተኛ ምሳሌ ነው።
ለሩቅ ገጠሬ ለገባሩ
ለማላውቅህ ለዳር ዱሩ
ከሁመራ ነህ ከመረብ
አኙአክ ነህ ወይስ ገለብ
ማነህ?
አጋው ነህ ወይስ ሺናሻ
ቅማንቴ ነህ ወይ ፈላሻ
ስምህ የሆነብን ግርሻ
ግራ ጎንደር ነህ መተከል
ባላዋቂ የምላስ ቅርስ
የዘር ንፍገት ስትቀበል
ያለእዳህ ስምህ ሲበከል
እምትችል እምትቀበል፤ እማትሞት 
እማትነቀል
ማነህ
ቆለኛ ሸክላ ሰሪ ነህ
ያገር እድር ያገለለህ...
ይለናል።
የፀጋዬ ብሶት ፀፀት ለኢትዮጵያውያን ግፉአን ብቻም አይደል አፍሪካዊ ታጋዮችንም ቢሆን ግብግብ ነው
የሚልላቸው። « ነውነውነው » የተሰኘው ግጥሙ ታንዛኒያ ውስጥ ለተገደለው የሞዛምቢኩ ኢ-
ቅኝ አገዛዝ ታጋይ ለኤድዋርዶ ሞንድላንድ ሙሾ ነው።
11
«እንቅልፍ ነውነውነው የሚያስወስድህ»
«ዝም አልኳቸው ዝም ይበሉኝ
ትቻቸዋለሁ ይተውኝ11
አልነካቸውም አይንኩኝ
ብለህ፤ ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተውኛል ብለህ 
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?...
ተስፋ አርገህስ ምን ልትሆን፤ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ?
እንቅልፍ እንጂ የሚያስወስድህ።
«አልጠራቸውም አይጥሩኝ
አይንኩኝ ስሜን አያንሱኝ»
ብለህ እንዴት ትመኛለህ እንደማይተውህ ስታውቀው
የተወጋ በቅቶት ቢኛ የወጋ መች እንቅልፍ አለው
የጅምሩን ካልጨረሰው?
... 
ፍቅርም ቢሆን ለፀጋዬ ባይተዋር አልነበረም። በ«ወል»
12
አፃፃፍ ዘይቤ ከፃፋቸው መካከልም ሁለቱ፤«መሸ መሸ  መሸመሸ ደግሞ  ደግሞ  
አምባ  ልውጣ  ልውጣ»(1951 ቢሾፍቱ)
13
 እና «ተወኝ ተወኝ» (1957 ኒውዮርክ)
14
 ይገኙበታል።
«መሸ መሸ  መሸመሸ ደግሞ  ደግሞ  አምባ  አምባ  ልውጣ  ልውጣ»
አምባ ወጥቼ እኩለ-ሌት፣ ስለት ገብቼ በስሟ
ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ፣ ልገላገል ከሕመሟ
ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ፣ ደጋግሜ፣ ማሕሌት ቆሜ
ሆዴ ቃቶት ባር ባር ብሎ፣ እርቃኔን ከሷ ታድሜ
ደጀ ሰላሟን በአራት እግር፣ ተንበርክኬ ተሳልሜ
በሥጋዬ እሚነደውን፣ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ
እፎይ ብዬ አመስግኜ፣ ውዳሴዋን ደጋግሜ...
ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል፣ ደሞ ይምጣ የቁም ሕልሜ?
ሌት በጥምቀቷ የነጣው፣ ነጋ፣ ደፈረሰ ደሜ።
ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፣ አዬ የስለት አታምጣ!
በውጣ ውረድ በጠበል፣ ባሣር ወዜ ቢገረጣ
ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፣ መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ!
«ተወኝ ተወኝ»
ላታስታምም አትመመኝ
ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ
ይቅር፣ አንጀቴ ቁረጠኝ
ጋሽዬ፣ አልወድሽም በለኝ
እጅ እጅ አልበል አታባክነኝ
ባክህ፣ ወንድ ነው ቆራጡ፣ እንትፍ እርግፍ አርገህ ተወኝ
አየህ፣ እንዳንተ አባት አለኝ
ሴት በወለድኩ ተዋረድኩ፣ ረከስኩ፣ ቀለልኩ እሚለኝ
እኔም እንዳንተ እህት አለኝ 12
ስጋሽን ሳይሆን ልብሽን፣ ከፍተሽ ጥለሽ እምትለኝ
እና ተወኝ፣ ባክህ ተወኝ
እንዳንተ እኔም አለኝ እናት
የሴት ቁንጮ እምመስላት
ጎረቤት ፊት እምታፍር፣ እንዲህ ሆነችልሽ ሲሏት!..
እና አልሆንሽም በለኝ
ባክህ አንጀቴን ቁረጠኝ...
ፍቅር እንደሁ የኔ ይበቃል፣ ላንተም ለኔም እኔው ልውደድ
ከዘመድ ግንባር ደብቄ፣ እኔ ብቻዬን ልንደድ
ብቻ፣ ከወጥመድህ ለየኝ
አልችልህም፣ ንቀህ ማረኝ
ካንተም፣ ከስሜም ከቤቴም፣ ያጣሁ ብኩን አታድርገኝ
ባክህ፣ አንጀቴን ቁረጠኝ
ተወኝ፣ ተወኝ፣ ተወኝ።
የፀጋዬ ግጥሞች ፍቅርን ብቻ ሳይሆን የቁጣ ረመጥና መራር ይሆናሉ። «እንደ እንደ  እንደእንደ መትፋት   መትፋት  ያስነውራል   ያስነውራል»
15
አይነቶቹ።
«መትፋት መትፋት  ያስነውራል  ያስነውራል»
እፍ አንቺ መብራት ጨልሚ!
እፍ አንቺ መብራት ክሰሚ!
ጥፊ፣ ጨልሚ፣ ውደሚ!...
አለ አሉ ሼክስፒር ቄሱ
መቸም አያልቅበት እሱ...
መድረክ ላይ ኩስ ከሚተፉ
አዎን ሕይወት ራሷ ትጥፋ...
...አዎን መትፋት ያስነውራል
ኪነት የህሊና ጽዳት፣ አስቀድሞ ይጠይቃል
ታዲያን በኛስ መድረክ መቅደስ፣
ለምን አጉል ኩስ ይጣላል?...
ይኸ በመድረክ ላይ መድረቅ
መራቆት እርቃን አፍ መንጠቅ
«ለእንጀራዬ ብዬ» ብሎ፣ በሰበብ ነብስ መሸብለቅ
ስሜት አልባ ሀፍረተ-ቢስ፣
እድፍ ቃል ደርሶ መሰንጠቅ
ለሆድ ብሎ ሐቅን ማነቅ
በጥበብ ስም አጉል ቅሌት፣
መዋረድ ፋንፉር መደለቅ
ህዝብ ፊት በየአዳራሹ፣ 13
ርካሽ ትርዒት ማስገምገሙ
በመጠጥ እየታጠኑ፣ ቃለ-ህሊናን ማጨለሙ
መቼም አትሉት የላችሁ፣
ኪነት ነው አላችሁ ስሙ?...»
የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ባህላዊ እሴትም ቢሆን ከፀጋዬ እይታ የተሰወረ አልነበረም። በ«የየት  የትየትት አባቱ   አባቱ! ! ሞትም ! ! ሞትም  
ይሙት!» የዶርዜ ባህላዊ ሥርአት በሞት ላይ ድል መጎናጸፍ መሆኑን ያበስረናል።
1
16
«የትየት  የትየት አባቱ  አባቱ! ! ሞትም ! ! ሞትም  ይሙት  ይሙት!»
1
17
እባካችሁ ዘመዶቼ፣ ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት
በሳቅ በደስታ ግደሉት
በሃሴት በዕልልታ ውገሩት፤
እባካችሁ ዘመዶቼ፣ ለሞት የልብ ልብ አትስጡት
ናቁት አጥላሉት አውግዙት
በሙሾ ግነን አትበሉት
በሞቴ፣ እንዳታስደስቱት።
እንደ ዶርዜ ወንድሞቼ
በሳቅ ታጅቤ ኮርቼ
ሞቴን በዘፈን ሞልቼ
በዳንኪራ ሰበቃና፣ በዘፈን ሆይታ አካትቼ
በሠርጌ ብቀበር ሞቼ
እፀድቅ ነበር ባትረሱ
በእንባ ውሌን ባታፈርሱ።
እባካችሁ ዘመዶቼ፣ በሳቅ ጉዞ ፍታት ፍቱኝ
በሙሾ ዋይታ አታጅሉኝ፤
እናቴም ፊትሽ አይክሰል
በእልልታ ብርሃን ይንበልበል፤
በእረፍቴ እንዳታፌዥብኝ
በሠርጌ እንዳታለቅሽብኝ።
ገጽሽ በጭንቅ አይወረስ
ልብሽ በኅዘን አይላበስ
በሆድሽ ሞት አይፀነስ
ዕንባ በአይንሽ አይቋጠር
የሞት ቅስሙ እንዲሰበር።
አዎን፣ አደራ፣ አደራችሁ፣ የሙት ውሌን ተቀበሉኝ
ደስታዬን ተካፈሉኝ
ለንስሃ ሞት አይደለም፣ ለፍሠሐ እረፍት አብቁኝ፤
ደስታዬን ተካፈሉኝ
ለንስሃ ሞት አይደለም፣ ለፍሠሐ እረፍት አብቁኝ፤ 14
በዶርዜ እስክስታ አስቀብሩኝ
በእልልታው ጉዞ አሳጅቡኝ
በጦሩ ችቦ አሳጥሩኝ፤
ጭብጨባችሁ በስልቱ ይውረድ
ዛፍ ቅጠሉም አብሮ እስኪረግድ፤
ሀገር ምድሩም ያቅራራ
ሀሴት ነው ይበል፣ ጆቢራ
ሠርጌ ነው፣ ይምታ ዳንኪራ
እንዲህ ስሜት ሲፍለቀለቅ፣ ሲፈነድቅ ሲግል ሃሞት
ቱማታው ሲዋጥ በላቦት
ሆይታ በሆይታ ሲራኮት
ማሳለፊያ መግቢያ ሲያጣ፣ ፍርሃት ገበናው ሲራቆት
መቃረቢያ ፍንጭ ሲያጣ፣ በእልልታ ሲወገር ብሶት...
ብቻ ነው፣ ሞት እራሱ የሚሞት።
እባካችሁ ዘመዶቼ፣ ሞትም አብሮኝ ይሙት!
በእልልታችሁ ግደሉት
በዳንኪራችሁ ዉገሩት
ከአጥንቴ በታች ቅበሩት።
ፀጋዬ ዝነኛ በሆነበት በመልከዓ ምድራዊ ይዘት ግጥሞቹም ይዘከራል። እንደ «መርካቶ መርካቶ»፤ «አምቦ አምቦ»፤ «ድሬድሬ  ድሬድሬ 
ዳዋ»፤ «አንኮበር ዳዋዳዋዳዋ አንኮበር»፤ «አዘቦ አዘቦ»፤ «አባይ አዘቦአዘቦ አባይ» እና «ሊማሊሞ ሊማሊሞ» ተጠቃሾች ናቸው።
በነቢይ መኮንን እይታ ፀጋዬ በ«ሊማሊሞ ሊማሊሞ» ግጥሙ ልዩ ልዩ እኩያን እየፈጠረ ሊማሊሞን እሱ ባየበት ዐይኑ
ሲያሳየን እናገኘዋለን። ሊማ ሊሞ የምድር ኬላ ነው። ሊማሊሞ ለምድር ዘብ የቆመ ነው። ሊማሊሞ ለጠፈሩ
ደግሞ ዋልታ ሆኖ የቆመ ነው። ሊማሊሞ የማይበገር የአለት ጣራ ነው። መከታና ጋሻ  ነው። ሊማሊሞ
በዐይናችን የምናየውን ሰፊ አድማስ ሰብሮአል። ግና ምን ያደርጋል ሥልጣኔ የማይረታው የተፈጥሮ አካል
የለም ነው የሚለን ፀጋዬ። በላዩ ላይ መንገድ ወጣበት ነው ያ ግዙፍ አይበገሬ አካል የሚለን ፀጋዬ።
«ሊማሊማ  ሊማሊማ -  - -- ሊሞ  ሊሞ»   ሊሞሊሞ
የሰማይ የምድሩ ኬላ፣ የየብስ የጠፈሩ ዋልታ
አይበገር የአለት ጣራ፣ አይመክተው መከታ
ሊማ - ሊሞ የቁም እርሙ፣ ሰማይ - አዘል ሊማ - ሊሞ
ክንፉ ከነካስማው ዘሞ
ከጠፈር ውሃ ገድቦ ለየብስ እንደማገር ቆሞ
ተጠማዝዞ ተጠምጥሞ
ከጽንፍ ጽንፍ አረምሞ
ከደባርቅ እስከ አዲ አርቃይ
አለት ከደመና በላይ
አዘንብሎ እንደ ሰማይ 15
እንደጠፈር ሽቅብ ሲታይ፤
ጉም አጥልቆ እንደቀሚሱ
ፀሐይን እንዳንገት ልብሱ
ተከናንቦ ተሸላልሞ
ተንደላቆ ሊማ- ሊሞ፤
ጨረር ባደመቀው ጭጋግ
ዙሪያ ዘርፉን እንደኅዳግ
በንዳድ ሀሩር ምድጃ
ፍም አንጥፎ እንደ ሥጋጃ፤
ሰማዩን ቁልቁል ዘንጥፎ
በብብቱ ጉም ታቅፎ
የአድማሳቱን ፍንጣቂ፤ ለእግሩ መርገጫ አርከፍክፎ
እንደ ፍካሬ ኢየሱስ ቃል፤ እንደ ሙታን የግዞት ሕግ
ተውተብትቦ ተጥለፍልፎ፤ ተቆላልፎ እንደዛር - ድግ
በምድር በሰማይ ዳር ድንበር፣ በሕዋው አለም ክልል ጥግ
በሲዖል ጠፍር መሰላል፤ የብስ ከጠፈር ታድሞ
ጥጉን እንደራእዩ አውታር፤ ከነአክናፉ ቁልቁል ዘሞ
እንደእንጥርጦስ በር አጥር፤ በአለት ናዳ ተረምርሞ
የጉም ክናዱን እንደጣር፤ ወደ ምድር ማኅፀን ቆልሞ
እንደባቢሎን ግንብ አጥር፤ ቋንቋ ለቋንቋ አሳድሞ
አልበገር አልደፈር፤ አልሰበር ያለን ከርሞ
ሊማ-ሊሞ የቁም-እርሙ ጠፈር አዘል ሊማ-ሊሞ
ዛሬ እንደስለት ሃጅ ፈለግ፣ በግብረ-ጉንዳን ተተልሞ
ሰማይ ከምድር ተደላድሎ፤ ተኮትኩቶ ተከርክሞ
በዲማሚት ተፍልፍሎ፤ ድልድይ ይሁን ሊማ - ሊሞ?
 
እነዚህ ርእሰ ጉዳዮች በሌሎችም ገጣሚያን ተዳስሰዋል። ዋናው ፍሬ ነገር እና የተመራማሪዎች ጥያቄ መሆን
የሚገባው  ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕንን ገንኖ ያወጣው፤ ከሌሎቹ የሚለየው ከምርታማነቱ ከፈጣንነቱ
በተጨማሪ ምንድን ነው የሚለው ይመስለኛል።
ከህልፈተ  ሕይወት  ሕይወት  ማግስት፦  ማግስት፦  
ከብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድሕን ህልፈተ ሕይወት በኋላ አንዳንድ መዘክራዊ  እንቅስቃሴዎች
ታይተዋል።
የፀጋዬ  ምሽቶች፦  ምሽቶች፦ የመጀመሪያውን ሙት አመት አስመልክቶ የባለቅኔው የፀጋዬ ገብረመድሕን ምሽት ለአራት
ሳምንታት (በDecember 2007) በሀገር ፍቅር ትንሿ አዳራሽ በመንፈስ ልጆቹ  አበበ ባልቻ፣ ፈቃዱ
ተ/ማርያምና ነቢይ መኮንን አስተባባሪነት ተካሂዷል። ከነዚህ ምሽቶች በአንደኛው የተገኘችው የዋርካ ድረ ገጽ
ተሳታፊ እይታዋን እንዲህ ትገልጽልናለች። “በሀገር ፍቅር ትንሿ አዳራሽ “የፀጋዬ ገ/መድሕን መዘከሪያ ምሽት”
ነበር። ያለፉትን ሶስት ሳምንቶች የመግቢያ ትኬት ለማግኘት ባለመቻል ችግር ማየት አልቻልኩም ነበር። በብር
አይደለም የሚገባው በግብዣ ብቻ ነው። በምሽቱ የፀጋዬ ምርጥ ስራዎች ቀርበዋል። ስለሱ ግጥም አጻጻፍም 16
አስተያየት በነቢዩ ቆንጆ ተደርጎ ተተንትኗል። ደስ ያለኝ ደግሞ ከዚህ በፊት የትም ሚዲያ ላይ ያልቀረበ ፊልም
ታይቶ ነበር...ፀጋዬ አሜሪካን ሆኖ የተቀረጸው... ደስ የሚልም የሚያሳዝንም ምሽት ነበር። እኔማ አንዳንዴ
ለማልቀስ ሁሉ እፈልግ ነበር። ዝግጅቱ ላይ አበበ ባልቻ ከኦቴሎ ፍቃዱ ተ/ማርያም ደሞ ከቴዎድሮስ ትያትር
ቀንጭበው አቅርበው ነበር...ፍቃዱ የቴዎድሮስን የመጨረሻ ንግግር ሲል ለራሴ እስኪገርመኝ ድረስ አፌ አብሮ
ያነበንብ ነበር...እንዲህ እንደተቀረጸብኝ አላውቅም ነበር...መጨረሻ ላይ መነባንቡን ሲጨርስ ሰዉ ብድግ ብሎ
ጭብጨባውን ማቆም አልተቻለም ነበር።ያኔስ እንባዬን ለማቆም አልታገልኩም።”  
 
የፀጋዬ  ስራዎች   ስራዎች  ህትመት   ህትመት፦ የፀጋዬ ቤተሰቦች በ1999 «እሳት ወይ አበባ»ን እንደገና አሳትመው ለሕዝብ
አቅርበዋል። ጅምርም ነው እንቀጥላለን ብለዋል አሉ። መልካም ሀሳብ ነው ቢቀጥሉበት።
የፀጋዬ  ድረ  ድረ  ድረድረ ገጾች  ገጾች፦ሁለት የፀጋዬ ድረ ገጾችን ጅምር አይቻለሁ ( ገጾችገጾች www.tsegaye.se) እና ደብተራው እናት ድረ
ገጽ ውስጥ። ሁለቱም ጅምሮች ናቸው መጠናከር ይገባቸዋል። የመጀመሪያው ድረ ገጽ የኮፒ መብት ችግር
ገጥሞኝ ነው ያለ መሰለኝ በጅምር የቀረው፤ እሱም ቢሆን የማይፈታ ችግር አይደለም የቤተሰቡ መልካም
ፈቃድ ካለ።
የፀጋዬ  ፌስ  ፌስ  ፌስፌስ ቡክ  ቡክ፦ ( ቡክቡክ http://www.facebook.com/home.php?#/pages/laureate-tsegaye-gebremedhin/)
የፀጋዬ 1370 አድናቂዎች የፌስቡኩ አባላት ሆነዋል። አንዳንድ ውይይቶችም ያካሂዳሉ።አንድ ሲያንሸራሽሩ
ያየሁት ሃሳብ በስሙ ቤተ መጻህፍት ለማቋቋም ነው። ማለፊያ ሃሳብ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ
ከደራሲያን መካከል በኢትዮጵያ ምድር ሀውልት የቆመላቸው አንድ ብቻ ናቸው «ኦኖሲሞስ ነሲብ» በትውልድ
ቀያቸው። ሀውልት ማቆምም ወይንም ደግሞ እንደበአሉ ግርማ ት/ቤትም በስሙ መሰየምም ሊሆኑ የሚችሉ
ሃሳቦች ናቸው። የቀድሞው ኢትዮጵያ መጻህፍት ድርጅት (ለበአሉ ግርማ) እና የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር
ተቋም (ለመንግስቱ ለማ) እንዳደረጉት ኤግዝቢሽኖችም ማዘጋጀት ይቻላል።
የፀጋዬ  ሽልማት  ሽልማት፦ የፀጋዬ መታሰቢያ ሽልማት በቤተሰቦቹና በወዳጆቹ ትብብር ተቋቁሞ ለሁለት የመጀመሪያ
አሸናፊዎች ሽልማት መሰጠቱም ከዚህ በፊት በዜና ተዘግቧል። ይበል የሚያሰኝ ነው።
 
የፀጋዬ  አመታዊ  አመታዊ  የቲያትር  የቲያትር  ፌ  ፌስቲ ፌፌስቲቫል ስቲስቲቫል፦በኄራን ሠረቀ ብርሃን እና ከአስር በላይ የፀጋዬን ቲያትሮች በማዘጋጀት  ቫልቫል
የሚታወቀው አባተ መኩሪያ እና ሌሎች በጎ ፈቃደኞች በትብብር ይህንን አመታዊ የትያትር ፌስቲቫል
ማዘጋጀት ጀምረዋል።
እንደማሳረጊያ  
ይህች ጽሁፍ ፀጋዬን እንዲህ ዘክራዋለች። ሞቱን ልደቱን ግጥሙን እያነሳሳች። ዘንድሮ የብላቴን ጌታ ሎሬት
ፀጋዬ ገብረመድሕን የሞተበት አራተኛ አመት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማሕበር የሚከበርበት አምሳኛ አመት
ነው። የፀጋዬ ቤተሰቦች ስራዎቹን ሳይደክሙ እንደ 1999 እሳት ወይ አበባ ለሕትመት ቢያቀርቡ፣ የብላቴን ጌታ
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድሕን ቀዌሳን ሶስት አስርት የዘለቀ የ«ካባራ አፍራካ» ጥናት እልባት አስገኝተውለት የህትመት
ብርሃን ቢያሰገኙለት፣ ማሕበሩም ስራዎቹን በማስታወስ ቢዘክረው እኛም በአቅማችን የፀጋዬ ፋን ክለብ አባል
በመሆን  ስራዎቹን ብንዘክር መልካም ነው እላለሁ። 
የብላቴን  ጌታ  ጌታ  ጌታጌታ ሎሬት  ሎሬት  ፀጋዬ  ፀጋዬ  ፀጋዬፀጋዬ ገብረመድሕን  ገብረመድሕን  ነብስ  ነብስ  ይማር  ይማርልን ልን!  ልንልን! መንግሥተ ! ! መንግሥተ  ሰማያት  ሰማያት  ያዋርስልን  ያዋርስልን!

No comments:

Post a Comment