"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 16 December 2012

በዋልድባ ስቃዩ እና እንግልቱ ቀጥሏል


በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግሥት የተለያየ ሙከራዎችን እያደረገ እንደሚገኝ እና በገዳማውያኑ ላይ ስቃዩን እንደቀጠለ ይነገራል። ባለፈው ወር ላይ የገዳሙን አባቶች ጥቂት የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰብስበው እንዳነጋገሯቸው እና ለጥር ፬ ቀን ቀጠሮ ሰጥተዋቸው እንደተበተነ ይታወሳል። በመጪው ጥር ፬ ቀን ምን ሊመጣ እንደሚችል በገዳማውያኑ ላይ ሊደርስባቸው የሚችሉትን፣ እንደ መንግሥት ባለሥልጣኖች አባባል በጥር ፬ ቀን በሚደረገው ስብሰባ ላይ የመንግሥት ተወካዮች ለገዳሙ አባቶች "ለቦታው ካሳ ተቀበሉ አለበለዚያ ሌላ ነገር ይመጣል" በማለት ገዳማውያኑን ለማስፈራራት ቢሞክሩም፥ ገዳማውያኑም "ሞትም ቢመጣ እኛ የአባቶቻችንን ርስት አሳልፈን አንሰጥም፣ እኛን ገላችሁ ሥራችሁን መስራት ትችላላችሁ" በሚል ሁኔውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት የገዳሙን ይዞታ የቋርፍ (የገዳማውያኑ ምግብ) የሚመረትበትን ቦታ ወስዶ ስላረሰው ገዳማውያኑ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል፥ ከዚህ በተጨማሪ የገዳማውያኑ የሳር ቤት ክዳን ባለው ቤት ላይ ተባይ በማፍራቱ ገዳማውያኑን ለተጨማሪ አደጋ ተዳርገዋል። ከዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት የአንድነት ገዳም ሦስት የመነኮሳይት ቡድን ወደ አዲስ አበባ ተልኮ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለመጠየቅ መጥተው እንደነበር እና ነገር ግን ከቤተክህነቱም ምንም ዓይነት ድጋፍ ሳይደረግላቸው መነኮሳይቱ ወደ ባዕታቸው ለመመለስ ችለዋል። 

በትላንቱ ታሕሳሥ ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በESAT Radio ዘገባ መሰረት፡-
  • በገዳሙ ስቃዩ ተባብሷል፡፡
  • በገዳሙ በስራ ላይ የነበረው የቻይና ኩፓንያ ከቦታው ወጥቶ ሌላ የህንድ ኩፓንያ ተተክቷል፡፡ አንድ ቻያናዊ መሞቱ ተነግሯል፡፡
  • በዋልድባ ገዳም መነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይም እንደ አዲስ አጠናክሮ ቀጥሏል
  • መረጃ ለተለያዩ ሚዲያዎች ሲሰጠ የነበሩትን አባት እየተፈለጉ ነው ያሉት ፡፡ እሳቸውንም ላገኘ በሽልማትነት የኮንዶሚኒየም ቤት መንግስት  እንደሚሸልም አስታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment