"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 16 January 2013

የፖለቲካ እስረኞችን ለማነጋገር ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያመራው የሽማግሌዎች ቡድን በተቃውሞ ተመለሰ።

 
  • ርዕዮት አለሙን ያነጋገሩት ፓስተር ዳንኤል ‹‹የእስከዛሬው ተግባርህ የሚያስረዳው ኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ ክንፍመሆንህን ነው፡፡ ስለዚህም በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደለሁም›› የሚል ያልጠበቁትን መልስ በማግኘታቸው የይቅርታ አጀንዳውን ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡

  • · የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በበኩላቸው ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ ‹‹ይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነንም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› የሚል መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡


  • · እስክንድር ነጋን ሳያነጋግሩት ተመልሰዋል፡፡


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በግል የፌስ ቡክ ገጹ ላይ ያሰፈረው ማስታወሻእንደሚያስረዳውሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 . በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎች ውስጥ የተዘጋጀ ሶስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡ ከቡድኑ አባላት ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ ለታሳሪዎቹ ‹‹ጉዳያችሁበፍርድቤትእየታየነው፤ስለዚህምክሱአሁንባለበትደረጃሊቋረጥአይችልም፡፡እናምክርክራችሁንአቋርጡናጥፋተኛነንበሉ፣ከዛምፍርድቤቱከፈረደባችሁበኋላይቅርታጠይቃችሁእናስፈታችኋለን››የሚል መደራደሪያ አቅርቦ ነበር፡፡ ሆኖም የሙስሊሙ መሪዎችይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ጥፋተኛነኝምአንልም፣አላሁአእለም!ይቅርታአንጠይቅም››ሲሉ በድፍረትና በቁርጠኝነት መልሰውላቸው ወደ እስር ክፍላቸው መመለሳቸውንና በተጠቀሰው ዕለት እስክንድር ነጋ ዘለው አንዱአለም አራጌን ነጥለው ማናገራቸውን የጋዜጠኛ ተመስገን ማስታወሻ ያስረዳል፡፡ ተመስገን ጨምሮ የሽማግሌ ቡድኑ ለሙስሊሙ መሪዎች ‹‹የመጣነው አንዱአለምን ፈልገንነው፣እናንተንእግረመንገዳችንንሰላምእንበላችሁብለንነው››ሲሏቸው፣ ለአንዱአለም ደግሞ የዚህን ግልባጭ ምክንያት መስጠታቸውን አስታውሷል፡፡

በሌላ በኩል ከ5 ቀናት በኋላ ትላንት ጥር 7 2005 ዓ.ም ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን እንዳነጋገሯት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በማረሚያ ቤት ያለውን አያያዝ አስመልክቶ አስተያየቷን እንድትሰጣቸው በመጠየቅ ውይይታቸውን የጀመሩት ፓስተር ዳንኤል ከርዕዮት አለሙ ‹‹በቅድሚያ አንተ እኔን የምታየኝ እንደ አሸባሪ ነው ወይስ እንደ ፖለቲካ እስረኛ?›› የሚል አጸፋዊ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ ፓስተር ዳንኤል በበኩላቸው ጥያቄውን ለመመለስ ብዙ ደቂቃ የፈጁ ቢሆንም ሁሉንም ታራሚ በአንድ አይን ነው የምናየው የሚል የተድበሰበሰ መልስ መስጠታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመልሱ ያልተደሰተችው ርዕዮትም ‹‹ሁሉንም ታራሚ በአንድ አይን የምታይ ከሆነ እኔን ለይተህ ማነጋገር አያስፈልግህም፡፡ መንግስት አሸባሪ ናት ብሎኛል፡፡ እኔ ደግሞ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ እያልኩ ነው፤ ህሊናህ የአንዳችንን እውነት እንደተቀበለ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ነገር ግን ልትናገረው ስለማትፈልግ ታድበሰብሰዋለህ፡፡ በቴሌቪዥን እየቀረብክ የኢህአዴግን ጥፋቶች ስታድበሰብስም ብዙ ጊዜ ተመልክቼሀለሁ፡፡ ስለዚህ ስለማረሚያቤቱ አያያዝ የምሰጥህ አስተያየት የለኝም፡፡››በማለት መልሳለች፡፡ ፓስተር ዳንኤልም ይህንን መልስ ሲሰሙ ጥንካሬዋንና ድፍረቷን እንደሚያደንቁ በመግለጽ ‹‹የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቆራርጦ የሚያሳየውን ነገር ተመልክተሸ እንዲህ አይነት ድምዳሜ ላይ መድረስ ትክክል አይደለም›› በማለት ሊሞግቷት የሞከሩ ሲሆን ርዕዮትም ‹‹ስለ ማረሚያ ቤቶች የምትሰጣቸው ምስክርነቶች ተቆራርጠው መቅረባቸውን ተቃውመህ መግለጫ ስትሰጥ አንድም ቀን አልታየም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ከእስከዛሬው አጠቃላይ ተግባርህ የምረዳው የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ ክንፍ መሆንህን ስለሆነ በምንም ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ ባለመሆኔ አዝናለሁ፡፡››በማለት ወደ ክፍሏ መመለሷን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ የተነሳም ፓስተሩ ምንም አይነት የይቅርታ አጀንዳ ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡


  1.  


No comments:

Post a Comment