"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 25 August 2015

መታሰር… መፈታት ?!? (መላኩ አላምረw



መታሰር… መፈታት ?!?
(መላኩ አላምረው)

በዚች በሀገሬ
ትላንት እና ዛሬ
ሚደጋገም ወሬ …
አዕምሯያኑ፣
ብዕራውያኑ፣
‹በነውጥ በሽብሩ›
“ታስረው” የነበሩ …
‹‹ተፈቱ! ተፈቱ! ደስ አይልም?›› ይሉኛል፣
እኔ በበኩሌ …
የመታሰርና የመፈታት ትርጉም ተቀላቅሎብኛል፡፡
በአዕምሯዊ ፍጡር - በሰብዓዊ ዓለም፣
መታሰር… መፈታት… ብሎ ነገር የለም፡፡
ወይም ለእኔ አዕምሮ ሐቁ ግልጽ አይደለም!
…..›››
‹‹እግርን በእግረ-ሙቅ - መሄድን ለማስቆም፣
ዓይንን በጨለማ - እይታን ለማድከም፤
እጅን በካቴና - ከብዕር እንዲቋረጥ፣
አናትን በኩርኩም - ላ’ሳብ ጊዜ እንዳይሰጥ፤››
እንዲያው በመመኘት…
እንዲያው በመሞኘት…
ምን ብዙ ቢደከም………
ሰብዕናን ማሰር
እይታን ማሳወር
አዕምሮን ማጣመም
ሂደትንም ማስቆም
ፈጽሞ አይቻልም፡፡
ምክንያቱም….
በአካል ላይ ሚደርሰው ስቃዩ ከፍ ቢልም፣
የነፍስን ባሕርይ - አዕምሮን ማሰር ግን - ለሰው አይቻልም!
በጥበበ አምላክ የአዕምሮ ተፈጥሮ፣
የሚቆም አይደለም እንደ-ሥጋ ታስሮ፡፡
እንዲያውም እንዲያውም…
‹አዕምሮን ራስ› እንጂ ሌላው አያስረውም
እናም እኒህ ሰዎች!
ባለ ህሌናዎች!
ታስረው ነበር አንበል! እስረኞችስ እኛ …
ህሌናችን ክደን፣
ማስመሰልን ለምደን፣
ከሐሰት ተዋልደን… እንቅልፍ የምንተኛ፡፡

No comments:

Post a Comment