"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 5 December 2012

VOA የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትና ፖለቲካ




ከዋና ዋና የአፍሪቃ ቀንድ አጥኚዎችና ታዛቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት Rene Lefort የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ “መለስ ከመቃብራቸው እየገዙ ነው። ግን ይህ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ጽሁፍ አውጥተዋል።

ፒተር ሃይንላይን, ቆንጂት ታየ

Rene Lefort ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይን ላይን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሰሞኑን የተሰጠውን ሶስት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ይገመግማሉ። በአስተዳደሩ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች እንደገና የመንግሥቱን ስልጣን እየተቆጣጠሩ ናቸው ያሉትንም ያብራራሉ። ስለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ዕድገት አሃዝና የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አንድምታ በተመለከተ አውስተዋል።

Lefort ከሰሃራ በታች ያሉትን የአፍሪካ ሀገሮች በተመለከተ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1970ዎቹ ጀምረው Le Monde – Le Monde Diplomatique እና በመሳሳሉት ጋዜጦች ጽሁፎችን ሲያወጡ ቆይተዋል። በ1982 ዓም Ethiopia A Hretical Revolution የተሰኘ መጽሐፍም ደርሰዋል።


“ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሃት ውስጥ በኦፊሴል ሁለተኛው ሰው ናቸው። ሐቁ ግን ዋናው የፓርቲው መሪ እሱ ነው ምክንያቱም አባይ ወልዱ በጣም አቋመ ጥብቅ ሰው አይደሉም። አሁን ደብረጽዮን የምጣኔ ሃብት ዘርፍ ጠቅላላ ኃላፊ ሆኗል። ይሄ እንግዲህ የደህንነት አገልግሎቱ አንዱ ዋና ባለልጣን ከመሆኑ በተጨማሪ ነው።” የሚሉት Lefort “ከህወሃት እጅ ውጪ ያለ አንድም ዋና የስልጣን ቦታ አይታየኝም፤” ይላሉ።

የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አጥኚው Rene Lefort በዚሁ የቅርብ ጊዜ ጽሁፋቸው መነሻነት ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።

ቃለ ምልልስ ከአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች አጥኚ Rene Lefort ጋር

http://realaudio.rferl.org/voa/AMHA/manual/2012/12/04/f55d3c92-4297-4181-88e5-6b44c4b1ab9f.mp3

No comments:

Post a Comment