"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 25 February 2014

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው” ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!

musevini


የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ  ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
uganda 1ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ግብረሰዶማውያን “አጸያፊ ሰዎች ናቸው፤ ምን ዓይነት ድርጊት ይፈጽሙ እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በቅርቡ የሰማሁት ግን በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ጸያፍ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሲቀጥሉም ሰዶማውያን ሲወለዱ ጀምሮ እንደዚሁ ናቸው ስለተባለ ሁኔታውን እውነት አድርገው በመውሰድ ቸል ሊሉት እንደነበር ሆኖም ግን እስካሁን ምንም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተናግረዋል፡፡
ሙሴቪኒ ሕጉን እንዲያጸድቁ ያደረጋቸውን አንዱን ምክንያት ሲጠቅሱም፤ ግብረሰዶማዊነት ከጄኔቲክስ ጋር በተያያዘ ከውልደት ጀምሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው በማለት ይገምቱ እንደነበር ሆኖም የአገራቸው ሳይንቲስቶች ይህንን መከራከሪያ ውድቅ ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ከጸደቀ በኋላ ወዲያውኑ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ግብረሰዶማዊ ወሲብ ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ዕድሜ ይፍታህ በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በወንጀሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ በ14ዓመት እስር ይቀጣል፡፡ በተደጋጋሚ ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ፣ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ጋር እንዲሁም ከአካለ ስንኩል ወይም ከኤችአይቪ ተጠቂ ጋር ወንጀሉን የፈጸሙ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ያዛል፡፡
ናይጄሪያም ከአንድ ወር በፊት ተመሳሳይ ሕግ ያወጣች ሲሆን የዑጋንዳው ሕግ በረቂቅነት ከወጣ የዛሬ አራት ዓመት ጀምሮ ምዕራባውያን ከፍተኛ ተጽዕኖ በማድረግ ሕጉ ተግባራዊ እንዳይሆን፤ ከሆነም በአብዛኛው የህጉ ክፍል እንዲሸራረፍ በርካታ ሙከራዎችን፣ ማስፈራሪያዎችንና ውስወሳዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡no homosexual
በአሜሪካ የፕሬዚዳንት ኦባማ አፈቀላጤ የህጉን መጽደቅ “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ዑጋንዳ ባስቸኳይ ሕጉን እንድትሰርዝ የጠየቁ ሲሆን አሜሪካ ከዑጋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና እንደምታጤነውም ተናግረዋል፡፡ አውሮጳውያንም በበኩላቸው የሕጉን መጽደቅ የኮነኑ ሲሆን የተወሰኑ የአውሮጳ አገራት ለዑጋንዳ የሚሰጡትን ዕርዳታ እንደሚያቋርጡ ዝተዋል፡፡ ሌሎች አገራት ግን እንዲህ ዓይነቱ የዕርዳታ ማቋረጥ ውሳኔ ዑጋንዳውያንን የሚጎዳ በመሆኑ እርምጃው መወሰድ የለበትም ይላሉ፡፡
የዑጋንዳ ሕግ አውጪዎች ያረቀቁትን ሕግ በፈረሙበት ጊዜ ሙሴቪኒ እንዳሉት ምዕራባውያን በዑጋንዳ ጉዳይ በግልጽ ጣልቃ እየገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ “አፍሪካውያን በሌሎች ላይ የራሳችንን አመለካከት አንጭንም” ያሉት ሙሴቪኒ ምዕራባውያን እስካሁን ያደረጉት ጣልቃገብነት ትክክለኛ እንዳልነበረ እና ይህም ደግሞ “ማኅበራዊ ኢምፔሪያዝም” ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡ ግትርና ግዴለሽ ምዕራባዊ ድርጅቶች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፋፋት እየጣሩ መሆናቸውንና ለዚህም ሰዶማዊነት ተግባር የኡጋንዳን ህጻናት እየደለሉ ወደ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል እንደሚያስገቧቸው ከሰዋል፡፡ በምዕራቡ ዓለም ያሉ ሰዶማውያን ደሃ ዑጋንዳውያንን ዒላማቸው በማድረግ በገንዘብ በመደለል ለግብረሰዶማዊነት እንደሚጋብዟቸውና ቀጥሎም ለግብረሰዶማዊ አዳሪነት እንደሚዳርጓቸው ሙሴቪኒ ተናግረዋል፡፡
የዑጋንዳን ውሳኔ አስመልክቶ የማኅበራዊ ጉዳይ ባለሙያ የሆኑ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል በሰጡት አስተያየት “ኢህአዴግም ከየምዕራቡ ለሚለቃቅመው ዕርዳታ ብሎ የአገርን ባህልና ማኅበራዊ እሴት ከሚያጠፋ ይልቅ ተመሳሳይ ተግባር ሊወስድ ይገባዋል፤ የተቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት በጸረ አሸባሪ ህግ ስቃዩን ከሚያሳይ የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በማውጣት ይህንን በአገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ወረርሽኝ መላ ሊለው ይገባል” ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment