"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 25 February 2014

ከበዕውቀቱ መጣጥፎች ውስጥ ሁለቱን ጀባ ልበላችሁ\\

ኢትዮጵያ እመ-መከራ
የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ…

አጤ ካሌብ የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባንድ ወቅት በቅድመ-እስልምና የመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች ባንድ ያይሁድ ገዥ መዳፍ ስር መማቀቃቸው አስቆጥቶት ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ተበቅሎላቸዋል። የዛሬውን አያድርገውና ፣ እንኳን ለቤት ለጎረቤት ጥቃት የሚቆረቆር ንጉሥ ማፍራት ችለን ነበር፤ አንኳን ለቤት ለጎረቤት እርዳታ የሚበቃ ጉልበት ማካበት ችለን ነበር ። ዛሬ ግን ጊዜ ከካሌብነት ወደ ከልብነት ደረጃ አውርዶናል። (“ከልብ” በግዕዝ ውሻ ማለት ሲሆን በአማርኛ ዘይቤ አንድ ሰው ያለ ካሳ ያለ ጉማ ደሙ ፈሶ ሲቀር ደመ ከልብ ሆነ ይባላል)።
አቅመ-ቢስ ሕዝቦች በጉልቤ ሕዝቦች መዳፍ ስር ገብተው መከራ ማየታቸው በታሪክ ብርቅ አይደለም። እኔን የሚገርመኝ በፋንታችን መከራ ማየታችን አይደለም ፤ እኔን የሚገርመኝ ከዚህ ሁሉ መከራ በሁዋላ ከመከራ የሚታደገን የኑሮ መላ አለማፍለቃችን ነው። ከመከራ መደራረብ በሁዋላ ያፈለቅነው የስልጣኔ ፍሬ የሙሾ ግጥም ብቻ መሆኑ ያስደንቃል።
አይሁድ በሁለተኛው ያለም ጦርነት ግፍ ከደረሰባችው በሁዋላ አንሰራርትው በርትተዋል፤ እንደ ኒቼ “ጨርሶ የማያጠፋኝ ሁሉ ያበረታኛል” ብለዋል። ዛሬ በነዳጅ መስክ ላይ የበቀሉ አረሞችን (አረቦችን) ያርበደብዳሉ ። ጀርመኖች በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማክተሚያ ላይ በጠላቶቻቸው ከስክስ ጫማ ደቀዋል። ግን በአጭር ጊዜ አንሰራርትው ሃይላችውን እንደ ንስር አድሰዋል፤ እኛስ ይሄን ማድረግ ያቅተናል? አያቅተንም። ያገራችን አስተዳዳሪዎች ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ፣ የሃይማኖት መሪዎች ፣ ሀያል መንግስቶች ከመከራ ዶፍ የማይታደጉን ነዳላ ጃንጥላ መሆናችውን አይተናል። የራሳችን አዳኞች ራሳችን መሆናችንን አንርሳ ፤ ጎበዝ የዳይኖሰርን ፈለግ ከመከተላችን በፊት ትንሽ መላ እንምታ::

                                                                                                                                                                                                                                                          - በእውቀቱ ሥዩም (November 11, 2013)ገንዳው

እዚህ አሜሪካ - በሀገረ ማርያም - በጊዚያዊ ቤቴ - ጊዚያዊ በረንዳ 
ቆሜ ሳነጣጥር 
አየሁኝ መንገድ ዳር - ተገትሮ ያለ የቆሻሻ ገንዳ 
ዳቦው እንደ ጉድፍ 
ወተቱም እንደ እድፍ 
ልብሱም እንደ ቅጠል 
በገንዳው ከርስ ውስጥ ይረግፋል እንደ ጠል ::
ያሜሪካ መልኳ 
አይደለም ህንፃዋ ሰማይ የሚነድለው
አይደለም መንገዷ - እንደ ቆለኛ ቅል የተወለወለው
አይደለም ፖሊስዋ - ዝሆን የሚያህለው
ያሜሪካ መልኳ ጎልቶ የተሳለው
በገንዳዋ ላይ ነው እመንገድ ዳር ባለው
ባገሬ ሰማይ ስር
ሰው ጠኔ ገፍትሮት ሲውድቅ በመደዳ
ያሜሪካ ንስር
ላንዲት ስኒ ሆዱ በጋን እያስቀዳ
እዚያ ማጣት እዳ
እዚህ ማትረፍ እዳ
እዚያ ባዶ መሶብ
እዚህ ሙሉ ገንዳ
ከእለታት አንድ ቀን
በሰማያት እና በምድሪቱ ድንበር
ከእኛ ጎታ አጠገብ የቆሻሻ ገንዳ ተቀምጦ ነበር
የሰማይ አማልክት አላጋጭ ቀልደኛ
“ራበን መግቡን” ስንላቸው እኛ
ብዙ መና ጋግረው ሲያዘንሙ ከሰማይ
የእኛን ጎታ ስተው ከተቱት ገንዳው ላይ::
ከቶ ለምን ይሆን
ያፍሪቃ ህፃናት በደቦ ሚያልቅሱ
የወተቶች አዋሽ - የርጎ ሚሲሲፒ - በበዛበት ዓለም - ጤዛ የሚልሱ
የሹራብ ተራራ - የቡልኮ ጋራ - በበዛብት ዓለም - ጭጋግ የሚለብሱ
የምድር ጠቢባን
ለዚህ ግዙፍ ምስጢር - መልስ አገኝ ብላችሁ - ጠፈር አታስሱ
አሜሪካ ያለው - የቆሻሻ ገንዳ - ግጣሙ ሲከፈት - ወለል ይላል መልሱ::
- በእውቀቱ ሥዩም

No comments:

Post a Comment