"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 17 April 2012

የቴዲ አፍሮ የቀለበት ስነስርአት እና የዘመኑ የዘረኝነት ጣጣ                                                                                   በሳለፈነው ሳምንት  እሁድ  የቀለበት ስነርአቱ ያደረገው ወጣቱን ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁንን አስመልክቶ

በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ  እስከዛሬ ድረስ ማለዳ ተነስቶ እንደማያውቅ እና ከቀለበት ሰነ ስርአቱ ጀምሮ መነሳት እንደሚጀምር እና የማህበራው ኑሮውን በሰፊው እንደሚጀምር ገልጾአል ሆኖም ግን ከህብረተሰቡ የቀረቡ አንዳንድ ትችቶች የቀረቡ ሲሆን በአሁን ሰአት በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን እውቅናውን ለመግፈፍ የሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ የተስተዋለ ስለመሆኑ ተገንዘበናል ::ይሀውም ባለፉት ሃያ አመታት ማንኛውም ሰው ዘሩን ሳይጠየቅ ጋብቻ ይፈጸም የነበረው የኢትዮጵያዊነት ባህርይ ዛሬ ተበርዞ እና ተከልሶ  ይህ ከየትኛው ዘር የመጣ ነው እየተባለ የሚዘባበቱበት ጊዜ ላይ እንደንደርስ የገዢው መንግስት ትልቅ ተጽእኖ እና  የአስተዳድራዊ አሉታዊ እና አወንታዊ ባህርያቶች እንደሆኑ ያመላክታሉ ።ይህም ሆኖ ማንኛውም ሰው አመጣጡን ሳይሆን ለትዳር  ተስማሚነቱን እና ፍቅር በውስጡ ሰርጾ ሃያልነቱን ሲያስመሰክረው የወደፊት የህይወት ፍሬውን ለማግኘት ሲባል ይደረግ የነበረው የጋብቻ ስነ ስርአት ዛሬ ግን ዘር ተለይቶ ማንነት ተጠንቶ እና ምን አለው ተብሎ የሚገባበት አለም መፈጠሩን አንዳንድ ግለሰቦች የጠቆሙ ሲሆን  
 ለእረጂም ዘመናት የሴት ጓደኛውን ለመግለጽ ተቸግሮ የነበረው እና ባለማወቅ ብዙ አይነት የስም ማጥፋት ዘመቻ የተካሄደበት ቴዎድሮስ ካሳሁን (አፍሮ)  ዛሬ ደግሞ ለምን ትግሬ አገባ በሚል የህብረተሰብ አስተያየት እና እሰጣ ገባ ከፍተኛውን የወሬ መናፈስ በሰሜን አሜሪካም ሆነ በኢትዮጵያ እየተዛመተ መምጣቱ የግለሰቦችን አለመብሰል እና ዘመን አመጣሽ የዘር ልዩነት በወያኔው መንግስት መፈጠሩ እንዲያባብሰው እና ህዝቡን በቁርሾ እንዲኖር ያደረገው መሆኑ ሲታወቅ በሌላም በኩል ደግሞ የገዢው መንግስት ቴዲ ካሳሁን (አፍሮ )ከህዝብ እይታ ርቆ እንዲወጣ  የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ስልት እንደሆነ እና ትዳሩንም ከጅምሩ ለማፍረስ እንዲሁም ህዝብ በዘር ምክንያት ጥላቻውን እንዲያተርፍ የሚያደርገው የገዥው መንግስት ወስጣዊ ደባ ወይንም ሴራ ነው ሲሉ አንዳንድ ሰዎች ገልጸዋል
። ይህንን ዜና እስካጠናቀርንበት ሰአት ድርስ ሙሉ ቀን በተለያዩ የሶሻል ኔትዎርኮች እና የምስል ስራዎች በሚካተቱባቸው የቪዲዮ ምህዳር ውስጥ የተሰጡ አስተያየት ለመቃረም ሞክረን የነበረ ሲሆን ከማለዳ ታይምስ ጀምሮ እስከ ድሬ ቱዩብ  የተሰጡትን በከፊል ለጥቆማ ብንገለጻቸው” ቴዲ አፍሮ ወያኔን ቀንደኛ መልእክተኛ እንጂ ዘፋኝ አይደለም አይነት መልእክት ያዘለ ሃሳብ ያቀረቡ ሰዎች ሲኖሩ በሌላም በኩል ደግሞ ለምን ጺላ ያገባል እንዴት ከትግራይ ይጋባል የሚሉ መስተጋብር ተፈጽመዋል እነዚህን አሳዛኝ እና ከአንድ ሰው የማይጠበቁ አስተያየቶችን ለመተቸት ብንሞክርም በመልካም ጎናቸው ደግሞ እንኳን ደስ ያለህ እኛንም ደስ ብሎናል የሚሉም አልታጡም በሌላም በኩል አምለሰት በአንቺ ቀናሁ ቴዲ አፍሮን ከልቤ አፈቅረው ነበር የሚሉ ኮረዳዎችም አልታጡም ! ሆኖም ይህንን አጠር ያለ ዜና መጣጥፍ ለማቅረብ የተገደድነው የህብረተሰባችን አመለካከት እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ ከመሄድ ይልቅ እንደ ዘመኑ ስልጣኔ ወደፊት ቀድሞ በመገኘት ዘረኝነትን አጥፍቶ አንድነትን አልምቶ በአንድ ጎዳና ለፍቅር ተገዢ ሆኖ “ፍቅር ያሸንፋል “በሚለው በቴዲ አፍሮ አባባል  እጅ ለእጅ ተያይዞ መጓዙ ይመረጣል  በአዲስ አበባችን ስልጣኔ በርክቶአል እየተባለ የሚወራውን አይነት ዲስኩር ከመደስኮር ይልቅ ስልጣኔ የአእምሮ ብልጽግናን ይበልጥ አንቱ የሚያሰኝ እድል ያሰጣል እና ከጠበበ የአመለካከት እና የጠበብተኘነት በሄር ወጥተን መኖር መቻል አለብን  ይህ ካልሆነ ግን እኛው እራሳችን የወያኔ ኢህአዴግ የሃሳብ መልእክተኞች አድሃርያን ሆነን ልንገኝ እንችላለን እና ከዚህ ሁሉ ልንቆጠብ እና ዘረኝነታችንን ልንገታ ይገባል እንላለን ።  የቴዎድሮስን አዳዲስ መረጃ ለማግኘት ለምትፈልጉ በሶሻል ኔት ዎር ማለትም በፌስ ቡክ ይህንን ሊንክ እየተጫናችሁ ትክክለኛውን ፌስ ቡክ ልታገኙት የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ  ላይክ የሚለውን ተጫኑት በወደ ማህበሩ ያስገባዎታል እስከዛሬ በስሙ የተከፈቱት ሁሉ የሶሻል ኔትዎርክ በሙሉ የእርሱ እንዳልሆኑ በዚሁ አጋጣሚ እንጠቁማለን::http://www.facebook.com/pages/Teddy-Afro/138825359518274

ማለዳ ታይምስ መልካም ትዳርን እንመኝላችኋለን                                                                                                                                                                                                                                                                                                                 

No comments:

Post a Comment