"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday, 20 May 2012

ቴዎድሮስ ካሳሁን አዲካን ይቅርታ ሊጠይቅ ነው አዲሱን ማናጀሩን በቅርቡ በጋዜጣዊ መግለጫ ያሳውቃል


ቴዎድሮስ ካሳሁን አዲካን ይቅርታ ሊጠይቅ ነው አዲሱን ማናጀሩን በቅርቡ በጋዜጣዊ መግለጫ ያሳውቃል

SHARE THIS
     
TAGS


ቴዎድሮስ ካሳሁን አዲሱን ማናጀሩን በቅርቡ በጋዜጣዊ መግለጫ ያሳውቃል maledatimes

ከአዲካ ጋር እና በቴዎድሮስ ካሳሁን የጥቁር ሰው አልበም ጉዳይ ላይ አወዛጋቢ ነገሮች ተፈጥረው ጉዳዩቹ  በሽምግልና መፈታታቸው መዘገባችን ይታወሳል ። በዛሬው እለት በተለይም ለማለዳ ታይምስ ከቴዎድሮስ አፍሮ የቅርብ ምንጮች እንደተገለጸው ከሆነ ባለፈው 3 ሳምንታት በፊት የተከሰተውን የአዲካን እና የቴዎድሮስ ካሳሁንን አለመግባባት አስመልክቶ በቴዎድሮስ ካሳሁን እና በአዲካ በኩል ለተደረገው ትልቅ ስህተት ይቅርታ ለመጠየቅ በቅርቡ ጋዜጣዎ መግለጫ ሊሰጠ እንደሚችል እና ከዚህም ባልተናነሰ ሁኔታ ከአዲካ ጋር ቀጣዩን የወደፊት ስራቸውን አጠናክረው ሊሰሩ እንደሚችሉ ሊገልጽ እንደሚችል ታስቦአል ።

በሌላም በኩል በዚሁ ባሳለፍነው ሶስት ሳምንታት ከቀድሞው ስራ አስኪያጁ ጋር በመጋጨት ከስራ ቦታው እንዲፈናቀል የተደረገው አዲስ ገሰሰ የቁርጥ ቀኑ ያወቀው ሲሆን በአሁን ሰአት ቴዎድሮስ ካሳሁን አዲሱን ማናጀሩን ለማሳወቅ ጋዜጣዊ መግለጫውን ከአዲካ ጋር የተከሰተውን ሁኔታ አስታኮ ለህዝብ ሊያሳውቅ እንደሚችል ሪፖርቱ ደርሶናል ።
የቴዎድሮስ ካሳሁን ቀጣዩ ስራ አስኪያጅ ተብሎ የተሰየመው የቀድሞው የሰሜን አሜሪካ የህዝብ ግኑኝነት  እና ለረጅም ዘመን በሚኒያፖሊስ ስቴት ነዋሪነቱን አድርጎ  የነበረው በተለይም  የሰሜን አሜሪካን ስፖርት ማህብረሰብን በህዝብ ግኑኙነት ሲያገለገል ቆይቶ  ቀጣዩን ህይወቱን በትውልድ ሃገሩ  ከ5አመታት በፊት አድርጎ የነበረውን ዘካርያስ ጌታቸውን ማድረጉን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ። በዚሁ ሳምንት አንዳድን የተዛቡ መረጃዎች ለዝግጅት ክፍላችን የደረሱን ሲሆን ይኸውም ቴዲ አፍሮ ከእጮኛው አምለሰት ሙጬ በተመረጠ ሰው የስራ አስኪያጅ ይቀጥራል ተብሎ ታስቦ ነበር ይኸውም ግለሰብ ዜግነቱ አሜሪካዊ ነው እየተባለ እንደነበር ለማለዳ ዝግጅት ክፍል ደርሶት እንደነበር ዝግጅት ክፍሉ ከመግለጽ ወደ ኋላ አላለም ። ይህም ሆኖ በሚቀጥለው ሳምንት በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሁሉም ነገር የሚለይ ሲሆን በኢትዮጵያ ያደርጋል ከሚባለው የሙዚቃ ኮንሰርት ቱር ዝግጂት ይበልጥ በአስቸኳይ ሁኔታ በጊዮን ሆቴል ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጾአል ።ይህንንም ካደረገ በሁዋላ በሰሜን አሜሪካ ያደርጋል እየተባለ የሚባለውን የሙዚቃ ዝግጅት በምን አይነት ሁኔታ ሊያደርግ እንደሚችልም ሊያሳውቅ ይችላል ተብሎ ይታሰባል ። በሌላም በኩል ጥቁር ሰው ከተሰኘው አልበሙ ውስጥ አለበም መለቀቅ በሁዋላ የመጀመሪያው የሙዚመጠሪያነቱን ያደርገውን ጥቁር ሰው የሚለውን ዜማ ከፍተኛ ወጭ በማውጣት ቪዲዮ ስራ በሚቀጥለው ሳምንት በአልበም ሪሊዝ ሰአት እና ጋዜጣዊ መግለጫውን አስመልክቶ ሊለቀቅ እንደሚችል ተጠቁሞአል ፣የዚህን የቪዲዮ ስራ የአበበ ቢቂላን የህይወት ታሪክ በፊልም ቀርጾ ያቀናበረው አንተነህ ወንድማገኘሁ የፊልም ጥበቡን የተጠበበት ሲሆን የሙዚቃውን ስራ እና ተወዳጅነት ያጠናክረዋል ተብሎአል ይህም የቪዲዮ ስራ ከጥቁር ሰው መለቀቅ በሁዋላ የመጀመሪያው የቪዲዮ ስራ ነው። በሌላም በኩል  በሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ኮንሰርቱን በማዘጋጀት የሚታወቀው የኤም ፕሮዳክሽን ኮንሰርቱን በማዘጋጀት ጉዳይ ምንም ምንጭ ሊጠቅስ አልቻለም ።ሆኖም ግን የሰሜን አሜሪካውን ስፖርት አስመልክቶ የቴዎድሮስ ካሳሁንን ሙዚቃ ዝግጅት ኤም ፕሮዳክሽን ያደርገዋል ተብሎ ይገመታል ይህንን ኮንሰርት  አስመልክቶ ከኤም ፕሮዳክሽን ጋር የተጠናቀረ ዘገባ  ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን ።

Share this:


Facebook
in

No comments:

Post a Comment