"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 20 May 2012

የቴዲ አፍሮና አምለሰት ሙጬ ፍቅር


የቴዲ አፍሮና አምለሰት ሙጬ ፍቅር

Posted by admin on April 22, 20127 Comments
“አምላኬ ሰው በልኬ“
“ከሚገባት በታች ከምችለው በላይ ስወዳት… ስወዳት…“
“እኔን ወዶ በቀላሉ ለመላቀቅ ከማሰብ ይልቅ ዝሆንን በመርፌ ቀዳዳ ለማሾለክ ዘዴ መፈለግ ይቀላል”

አምለሰት ሙጬና ቴዲ ፍቅር አፍሮ
በመላው ዓለም የተለመደ ነው – ዝነኞች ይሳሳባሉ፡፡ ታላላቅ ዝነኛ አርቲስቶች የፍቅር ግንኙነት የሚጀምሩትና ጋብቻ የሚመሰርቱት ከአቻ ዝነኞች ጋር ነው፡፡ የዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮና የእጮኛው አምለሰት ሙጬም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞች የፍቅረኛን ጉዳይ ባነሱበት ቁጥር ከጥያቄው ሲሸሽ የቆየው ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ፤ “ጥቁር ሰው” የተሰኘውን አዲስ አልበም በለቀቀ ማግስት የፍቅረኛውን ማንነት በይፋ ተናግሯል፡፡ ምንጮች እንደሚሉት፤ የ2007 ሚስ ኢትዮጵያ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ከሆነችው አምለሰት ሙጬ ጋር ግንኙነት የጀመሩት ድምፃዊው የ”ያስተሰርያል” አልበም የሙዚቃ ክሊፖችን ሲሰራ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃዊው የፍቅር ጥያቄ ሲያቀርብላት “እሺ” እንዳላለችው ምንጮች አስታውሰው፤ በወቅቱ ሜክአፕ አርቲስቱ ስለነበረች ቅርርባቸው መቀጠሉን ይገልፃሉ፡፡ በእስር ላይ በነበረበት ወቅትም አመልሰት በየሳምንቱ ከቃሊቲ ጠፍታ አታውቅም፡፡

አምለሰትና ቴዲ አፍሮ የፍቅር ግንኙነት የጀመሩት ከእስር ከተፈታ በኋላ ባለው ጊዜ እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ድምፃዊው ከወጣት አምለሰት ጋር ቀለበት ማሰሩንና ለቀለበቱ 750ሺ ብር እንዳወጣ የሚጠቁሙ ወሬዎች የተናፈሱ ሲሆን፤ ጥንዶቹ ከ 4 ወር በኋላ ጋብቻ እንደሚመሰርቱ ድምፃዊው ተናግሯል፡፡
የአምለሰት ዝነኝነት ሀ ብሎ የጀመረው እ.ኤ.አ በ2005 ዓ.ም በቁንጅና ውድድር 3ኛ ስትወጣ ነበር፡፡ በወቅቱ የጋዜጠኝነት ተማሪ የነበረችው አምለሰት፤ 2006 በሚስ ወርልድ ውድድር ላይ የተሳተፈች ሲሆን በ2007 በ“ሚስ ኢትዮጵያ” የቁንጅና ውድድር ተሳትፋ አሸነፈች፡፡ ይሄኔ ዝናዋ የበለጠ ናኘ፡፡ ከዚያም በሞዴልነት ስትሰራ ከቆየች በኋላ ወደ ፊልም ሙያ በመግባት የበለጠ ታወቀች – የቴዲ አፍሮ እጮኛ አምለሰት፡፡
“አይ የፍቅር ጠበሳና ጠባሳ!” በሚል ርዕስ መስከረም 29 ቀን 1997 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ባስነበበችው ወግ እንዲህ ፅፋ ነበር፡-
“መቼም ፍቅር በልቡ ጠንስሶ “ስኩል ላይፍ” ያልቀጨ የለም … የመፅሃፍ ቅዱሱ ጳውሎስ ሲናገር “ከፍቅር ውጭ የሚተለሙ የሰው ልጅ ትልሞች በሙሉ ፍፃሜያቸው ትርጉም አልባ ነው” ብሏል … እናማ፤ ፍቅር ያላንጠባጠበው ሰው አለ ቢሉኝ ባፍንጫዬ ልቁም …”
በረቂቅ ወጐች ላይ ልበ ሙሉነትና ድፍረትም ይንፀባረቅባቸዋል፡፡  “የተማሪ ፍቅር” በሚል ርዕስ ከፃፈችው ወግ ጥቂት መስመሮች ይሄን ያሳያሉ፡- “…አምላክ በቀን መቶ ሴት እንዳላመረተ አንቺን ግን ዓመቱን ሙሉ “ምን ጐደላት?” እያለ ተጨንቆ መስራቱን ሳሳበው ግርም ይለኛል … ስተኛም ስነሳም ለአምላኬ ፀሎቴን የማደርሰው ባንቺ አማላጅነት ነው፡፡ ግን ሰምተሽኝ ይሆን? የምሬን እኮ ነው፡፡ አንቺ’ኮ ለማርያም ሩብ ጉዳይ ነሽ … ምናምን እያለ ሲያንቆለጳጵሰኝ ሲያንቆለጳጵሰኝ … ምን ማለቂያ አለው? የእጅ ፅሁፉም የፖስታው ንጣቱም ያምር ነበር፤  የተገዛ የፍቅር ደብዳቤ ቢሆንም …”
አምለሰት በወግ ፀሃፊነቱ ባትቀጥልም ከኪነጥበብ አልወጣችም፡፡ በሰይፉ ፋንታሁን “ይፈለጋል” የተሰኘ ፊልምና በሌሎች የአማርኛ ፊልሞች ላይ በተዋናይነት የሰራችው አምለሰት፤ “ስለ ፍቅር” የሚል ሮማንቲክ ኮሜዲ ፊልም ፅፋ ፕሮዲዩስ አድርጋለች፡፡
በኒውዮርክ የፊልም አካዳሚ የፊልም አሰራርን የተማረችው ወጣቷ፤ በፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ህይወት ላይ ያጠነጠነ ዶክመንተሪ ፊልም ለመስራት ቀረፃ አከናውና እንዳጠናቀቀች በድረ ገጿ ላይ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
(ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

No comments:

Post a Comment