"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 22 October 2012

የትግሉ ነው ሕይወቴ

እለቱ ቅዳሜ ነው፤ በጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ  እንደወትሮው እንቅልፍ አልተጫጫነኝም፤ መንፈሴም ነቃ ነቃ ብሎዋል። እንደወትሮው ስል ትንሽ ለማብራራት ያህል የምኖረው በስደተኛ መጠለያ ስለሆነ በጠዋት የሚያስነሳ ስራም ሆነ ጉዳይ ስለሌለኝ ሁል ጊዜ ከእንቅልፌም ነቅቼ ቢሆን ድብት አድርጎ  አትነሳ አትነሳ እያለ የሚጫጫን  በዘልማድ እንደሚባለው  ዱካክ ሲያገላብጠኝ ስለ ማረፍድ ነው።[ለኖርዌ መንግስት እግዛብሄር ይስጥልኝ]ይሰመርበት ፨ጥሩ ተኛ በሎ በመጠለያ አስቀምጦ እንዳልሰራም እንዳልማርም  ጥሩ ሰውነትና ጭንቅላቴን እንዳልሰራበት ኧድርጎ ለምግብ የምትሆን ትንሽ  ብር  እየወረወረ ተማርሪ እራሴን እንድገል ወይም የመናገር ፤የመጻፍ፤ የመሰብሰብ ፤ የመቃወም ፤ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና የመኖር ነጻነትን የሚገፍ መንግስትን ይቅርታ ብዬ ወደ አገር ቤት እንድመለስ እየገፋኝ ስለሚገኝ ነው እግዜር ይስጥልኝ  ያልኩት  በምጸት።እና  እንዳልኳችሁ የቅዳሜው ጠዋት ነቃ ነቃ  መንፈሴም እንደ ወትሮው ሳይሆን የሆነ ደስ ደስ የሚል ሰሜት ነው እየተሰማኝ ነው  ከአልጋዬ ላይ የተነሳሁት። መቼም እስካሁን ምን አግኝቶ ነው ሳትሉኝ አትቀሩም ነገሩ እንደዚ ነው።                                                                                              የኢሕአፓ 40ኛ ዓመት በዓል የምናከብረው ዓመት እየቆጠርን ራሳችንን ከፍ ከፍ በማድረግ ለመመጻደቅ ወይም ድግስ ደግሰን ለመደሰት ሳይሆን የሀገራችን ጠላት የሆነውን የወያኔን አገዛዝ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት፣ የወደቁትን ጓዶች፣ አካላቸውን ላጡና በየእስርቤቱ እየማቀቁ ያሉ አባሎቻችንንም ለመዘከር ነው።

ውድ የኢሕአፓ ቤተሰቦችና ወዳጆች!  ያለንበት ሁኔታ የቦታ ርቀት የኑሮና የቤተሰብ ሁኔታ እያልን የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከተፈጥሮ ጋር አጣምሮ መደርደር ይቻላል። ክረምቱም መምጣቴ ነው እያለ ነው ዶፍ ዝናብና በረዶም ሊያወርድብን ይችላል። ይህን ሁሉ ስንዘረዝር  ለኢሕአፓ ሰማዕታት ክብር ለሀገርችን ነፃነት ካለን ቁርጠኝነትና ፍላጎት፤ የትግል አጋርነትን ለማሳየት ለቆረጠ ችግሮቹ ከቁብ የማይቆጠሩ ናቸው።

ስለዚህም በቦታውና በሰዓቱ በመገኛት በዓላችንን ከእኛ ጋር በማሳለፍ ለደርጅታችን ያለንን ድጋፍ ለትግላችን መጠናከር ለሀገራችንና ለሕዝብ እየተደረገ ላለው ትግል አጋዥነታችሁን እድትገልጹ በታላቅ አክብሮት እጠየቃለሁኝ!!

 የትግሉ ሰማእታት በህሊና ጸሎት ሲታወሱ።   ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለኢሕአፓ ሰማዕታት!!
የእራት ፕሮግራም
አቶ አርጋው ፕሮግራሙን ሲያስተዋውቁ
                                                                                                                                              ይህ ከላይ ያለው ጽሁፍ እንደሚገልጸው  ብርታትና ጥንካሬን የሚሰጥ መንፈስን የሚያድስ ትግስትን የሚያስተምር ሆኖ ፤እንዴ ምን አድርጌ   ምን ሰርቼ  ነው  እንዲህ የምማረረው፤ በማለት እራሴን  በማበረታታት የትግሉ ነው ህይወቴ  የሚለውን የትግል መዝሙር  እያንጎራጎርኩ አንዳንድ የራሴን ዝግጅት በማድረግ ከእጄ ያማትለየውን ክራር በመያዝ 40ኛውን ዓመት የኢሀአፓን ምስረታ በዓል ወደ ሚዘከርበት ቦታ  ጉዞዬን አቀናው። እንዳይደርስ የለም ሰዓቱ  ደርሶ ከድርጅቱ  አባላት ውጭ ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች በቦታው  ተገኝተው ስፍራ ስፍራችውን እንደያዙ የእለቱ ፕሮገራም በአቶ አሳየህኝ ጥላሁን ንግግር አድራጊነት ተጀምሯል። አቶ አሳየህኝ በዕለቱ  ንግግራቸውን የጀመሩት በትግል ወቅት ለዓላማቸው ሲሉ  ሂወታቸውን ላጡ የትግሉ ሰማዕታት የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው። ይህንን በዓል  የምናከብረው ዓመት እየቆጠርን ራሳችንን ከፍ ከፍ በማድረግ ለመመጻደቅ ወይም ድግስ ደግሰን ለመደሰት ሳይሆን የሀገራችን ጠላት የሆነውን የወያኔን አገዛዝ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት፣ የወደቁትን ጓዶች፣ አካላቸውን ላጡና በየእስርቤቱ እየማቀቁ ያሉ አባሎቻችንንም ለመዘከር ነው። በማለት የበዓሉን አስፈላጊነት አፅንኦት በመስጠት አሳስበዋል።በአቶ አሳየህኝ ጋባዠነትበመቀጠል አቶ ጌትነት  ንግግር አድርገዋል በትግል ወቅት ምን ያህል መከራና ስቃይ እንደተጋፈጡ ስንት ችግር እንዳሳለፉ እንባ እየተናነቃቸው በማስታወስ ተናገረዋል።በመቀጠል ዶክተር ሀብታሙ የኢህአፓ የወክንድ ትግል ምን መሆን እንዳለበት ከበፊቱ የኢህአፓ የወጣት ትግል ተሞክሮ በመጥቀስ ታሪኩንም በማውሳት ንግግር አድርገዋል።በመቀጠል አቶ  አሳየህኝ ቀጣዩን ፕሮገራሙን ለተግባር ኮሚቴው ሰበሳቢ ለአቶ አርጋው ሰተዋል በዚ መሀል ግን በእንግድነት ከተጋበዙት ውስጥ አንድ ድምጽ ተሰማ አዎ አቶ ማተቤ ናቸው እሳቸውም አሉ እናንተ እንድናገር እድል ትሰጡኛላችሁ ብዬ ነበር አልሰጣችሁኝም ግን እኔ እናገራለው በማለት ስለ ኢህአፓ ያላቸውንጥሩ ምስክርነት አስቀምጠዋል ።አቶ አርጋው የዕለቱን ፕሮገራም በማሰተዋወቅ የመጀመሪያው እራት በማንሳት ተጀመሯል።እንደ ቅደም ተከተሉ የተለያዩ ፕሮገራሞቹ ተደርገዋል።በተለያዩ ጊዜ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለድርጅቱ አገልግሎት በማበርከት ላይ የሚገኙ ሶስት ተሸላሚዎችም   በዕለቱ ከዶክተር ሀብታሙ እጅ ከኖርዌይ ሀገራዊ ኮሚቴ የተላከላቸውን ሰጦታ  በቅደም ተከተል ተቀብለዋል ተሸላሚዎቹም  አቶ አርጋው፦አቶ ቴዎድሮስ እና አቶ ግርማቸው ናቸው።በመቀጠል ሁሉም የበዓሉ ታዳሚ ከመቀመጫው በመነሳት በአቶ እንዳለ  [እኔ] ክራር ተጨዋችነት ፤በአቶ ጌትነት፤አሳየህኝ እና ግርማቸው መሪነት የትግሉ ነው ህይወቴ የሚለውን መዝሙር ከልብና በስሜት ሞቅ አድርገን በመዘመር የትግል ተነሳሽነታችንን አሳይተናል።http://www.youtube.com/watch?v=fZhmRrAjjmw
እንዳለ ጌታነህ ለመዝሙር ሲዘጋጅ
ዶክተር ሀብታሙ ንግግር ሲያደር
 ከመዝሙሩ በመቀጠል የበዓሉን ትልቅነት ለማስታወስ በትግል አንጋፋ ከሆኑ አሁን ላለነው አባላት ሁልጊዜ  ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያላቸውን የትግል እና  የዕድሜ ልምዳቸውን ከማካፈል ወደ ኋላ በማይሉት  በአቶ ታደሰ አማካይነት የ40ኛውን ዓመት ማስታወሻ ሻማ ተለኩሷል።ቀጣዩ  ፕሮግራም የጨረታ ሲሆን የጨረታው ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ማርቆስ በጥሩ ሁኔታ እድምተኛውን  በሚያስደስት ኪሱ ውስጥ ያለውን ሳይሰስት እንዲያወጣ እና እንዲፎካከር በማድረግ ቦታውን ሰላማዊ ጦርነት አድርገውት አምሽተዋል። የእለቱ ፕሮግራም ባማረና በደመቀ  ሁኔታ እንዲከበር ጊዜያቸውን መስዋት በማደረግ ጥረት ላደረጉ በሙሉ ምስጋናዬን በማቅረብ ያለኝን የራሴን የኔን የምወደውን እና ትወዱታላችሁ ብዬ ተስፋ የማደርገውን ዜና አቀርባለው።እናቸንፋለን ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ።

No comments:

Post a Comment