"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 10 April 2012

 ‹ የገዳሙ አባቶች ‹አሳ ማጥመድ ይችላሉ ›› ይህን ስላቅ ምን ይሉታል ?                      
 

  (አንድ አድርገን መጋቢት 14 2004 ዓ.ም)፡-                                                                                                                                                                                                     - ቤተክህነቱ ዋልድባ ገዳምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝበ ክርስትያኑን ጨጓራውን ያሰረረ ነበር ፤ መንግስት እንኳን ከጥቅሙ አኳያ ስኳር ፋብሪካ እገነባለው ቢል መጀመሪያ መቃወም ያለበት ቤተክህነት ሆኖ ሳለ ከመንግስት ጋርም ወግኖ መንቀሳቀሱ ቤተክርስትያኗ ደህና የሚባል መንግስትን የሚቃወም አካል እደሌላት በግልፅ ያሳያል ፤ በመጀመሪያ የዋልድባ አባቶች ገዳማቸው ሳይታረስባቸው ታረሰብን አይሉም ፤ ሳይነካባቸው ተነካብንም ለማለት አይደፍሩም ፤ የመንግስት ባለስልጣናትን የታረሰው ቦታ ላይ ኑ እና እንወያይ መጀመሪያ ስራችሁን እዩት ሲሏቸው ቀድመው የሰሩትን ስራ ያውቁታልና ሽሬ ላይ ካልሆነ ብለው ባለስልጣናቱ እምቢ አሉ ፤ አባቶችም በቃ የሰራችሁትን ስራ ላለማመን እና አላደረግንም ለማለት ስለሆነ በምትጠሩት ስብሰባ ላይ አንገኝም ብለው በአንድነት ተነስተው ወጡ ፤ መንግስት ደግሞ እያለ ያለው የፖለቲካ አላማ ያላቸው የገዳሙ መነኮሳት ብሎ አስተያየት በኢቲቪ ሲሰጥ ስመለከት በጣም ተበሳጨው ፤ ሰው የፖለቲካ አላማ ለማረመድ ገዳም ምን ሊሰራ ይገባል ? የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እኮ ከተማ ነው ተመራጭ ፤ እንዴት እደሚያስቡ ራሱ ግራ የሚገባ ነገር ነው ፤

         ቤተክህነት እኛን ወክሎ ወደ ዋልድባ ያቀናው ሰው እና የመንግስት ስኳር ኮርፖሬሽን ሀላፊ አባይ ጸሀዬ  ሁለት አይነት መልስ መስጠታቸውም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ፤ አቦይ ስብሀት የሚነሳ መቃብር አለ ፤ እሱን ሌላ ቦታ ላይ የማስፈር ስራ ይሰራል ፤ በቤተክርስትያን አባቶች ቦታው ተባርኮ የነበሩትን አስከሬኖች በማንሳት ቦታ የመለወጥ ስራ ይሰራል ብለው አስተያየት ሲሰጡ ፤ አቶ ተስፋዬ  የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ደግሞ ምንም ነገር እንዳልተከናወነ እና የስኳር ልማቱ እና ገዳሙ በጣም የተራራቁ መሆናቸውን ገልጸዋል ፤ በነገራችን ላይ ይህ ሰው ከጀነራል ዊንጌት ኤሌክትሪሲቲ ዲፕሎማ እንዲሁም በገበያ ጥናት አስተናደር ሌላ ዲፕሎማ ያለው ሲሆን አሁን ከሚሰራበት ቦታ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው አቡነ ጳውሎስ ቢመልሱ መልካ ነው ፤ ባይሆን እንደኛ ሀሳብ የገበያ ጥናቱ ትምህርት የዋልድባን መሬት ከመንግስት ጋር በመደራደር ለመሸጥ የረዳው ይመስለናል ፤ ባለን መረጃ መሰረት ለዋልድባ ገዳም አባቶች ሀሳባቸውን በአግባቡ እንዳይገልጡ  እንደ እርጎ ዝንብ እየገባ ሲበጠብጣቸው የነበረውም ይህ ሰው ነው ፡፡ ገዳሙ ከግድቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አማራጭ እንዳለውም ገልጿል ፤ በተጨማሪ በጣም የገረመን አስተያየት የሸንኮራ ልማቱ ሲካሄድ በሚገደበው 138 ሜትር ግድብ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ የሚል አስተያየት መስጠቱም ጭምር ነው ፤ ቋርፍ የሚባል ገዳሙ የሚጠቀምበት ተክልም ብሎ ዘባርቋል ፡፡ ይህ ሰው በዚህ ብቃቱ እዚህ ቦታ ላይ መቀመጥ ይገባዋል ብለው ያስባሉ ?  እኛ እንደምናስበው ይህ ቦታ የቤተክርስትያኒቱን አማኞች ለመምራት በመንፈሳዊ ሆነም በአስተዳደራዊ ትምህርቶች ለቦታው የሚመጥን ሰው መሆን አለበት የሚል አስተያየት አለን ፤ አሁን የኛ ትልቁ ችግር የማይገባቸው ሰዎች ቦታን በዘመድም ይሁን በገንዘብ ይቆናጠጡታል ፤ ኋላ የሚመጣውን የቤተክርስትያን ችግር ሲመጣ ደግሞ ቤተክርስትያኒቷን አሳልፈው ይሰጧታል ፤ትክክለኛው ሰው ትክክለኛ ቦታ ላይ ቢቀመጥ ግን ይህን የመሰለ ችግር ለመፍታት መንፈሳዊ ሆነ አስተዳደራዊ ብቃት ስለሚኖረው ችግሮችን ሊጋፈጥ እና መፍትሄ ሊያመጣ የመጀመሪያው ሰው ይሆናል ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው የተገላቢጦሽ ነው ፡፡

እኛ የአሳ ናፍቆት የለብንም ፤ እኛ ርስታችንን አትንኩ ነው የምንለው ፤ አሳ ለማግኝት በመኪና ሀዋሳ መውረድ ይቻላል ፤ የአባቶችን ርስት ፤ መቃብር በዶዘር አትፈንቅሉብን ነው የምንለው ፤ አቶ አቦይ ስብሀት ስለ ሚያነሱት አፅም በቂ እውቀት ላይኖራቸው ይችላል ይህ ግን ከቤተክህነት ተወክሎ የሄደ ሰው ከሰውየው ዘቅጦ መገኝቱ ያሳፍራል፡፡ ልሳነ ዘተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ በየወሩ የምትታተም መፅሄት ላይ የ2004 ዓ.ም የአብይ ፆም እትም አቡነ ጳውሎስ ይህን ሰው ከፍተኛ ብቃት ያለው ሰው በማለት አሁን ላለበት ቦታ ሹመውታል፡፡

እኛም እንደ አባቶች ይግባኝ ለክርስቶስ ብለናል ፤ ቅን ፈራጅ እሱ ስለሆነ ለእሱ አሳፈናል ፤ ቤተክርትያን ጦር ሲነሳባት አብረው ከውስጥ ለሚወጓት ሰዎች ጊዜው ሲደርስ ባለቤቱ ይፋረዳቸው ፤ የአባቶችን ጸሎት አምላካችን ይሰማል ፤ በፍርድ ቀን መጽሀፉ እንዲህ ይላል ‹‹እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤›› ማቴዎስ ወንጌል 12 ፤36 እናንተም ስለ ስራችሁ ትጠየቁበታላችሁ ፤ የአምላካችን ቃል አይታበይም ፡፡

                                                                                                                   

No comments:

Post a Comment