"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday, 8 April 2012

 ወይዘሮ ጠለላ ከበደ ወርቁ ላደረጉት አስተዋጾ እውቅና

ተደረገላቸው 
ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት መጠበቅና ለአገር ሉዓላዊነት መረጋገጥ ያላቸውን ጠንካራ እምነት ከፍተኛ 
ግምት በመስጠትና  እንዲሁም ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የኢሕአፓን ትግል በመደገፍ ትግሉ  እንዲጠናከር 
ያደረጉትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድነቅ የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ለታዋቂዋና ተወዳጇ አርቲስት 
ወ/ሮ ጠለላ ከበደ ወርቁ የክብር እውቅናና የምስጋና ስጦታ አድርገውላቸዋል።  ታህሳስ 8 ቀን 2004 ዓ.ም. 
(December 18, 2011) ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢሕአፓ ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ  
በርከት ያሉ የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት  በተካሄደ ስነስርዓት ወ/ሮ ጠላላ ከበደ ለረዥም 
ዓመታት ያካሄዱትን ሕዝባዊ ትግልና ያደረጉትን አስተዋጽኦ  በማድነቅ የክብር የምስክር ሰነድና ሌሎች 
ሽልማቶች ተሰጥቷቸዋል። በዕለቱ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ ፋሲካ በለጠ፣ አቶ ተገኘ ሞገስና 
አቶ ፋንታ ታዬ እንዲሁም ከዋሽንግተንና አካባቢው የኢሕአፓ ኮሚቴ አቶ ግርማቸው ተስፋዬና አቶ 
መንበረ ለማ ወ/ሮ ጠለላ ከበደ ወርቁ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በማድነቅ የተለያዩ ንግግሮች  አድርገዋል። 
በዕለቱ የነበሩት እንግዶች የተሰማቸውን ደስታ በጭብጨባና አስተያየት በመስጠት ገልጸዋል። 
በሰሜን አሜሪካ 
 የዋሸንገተን ዲሲና አካባቢው የኢሕአፓ ኮሚቴ 

No comments:

Post a Comment