"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 9 April 2012

የኢትዮጵያ ሽግግር ወደ ዴሞክራሲና የማንነት ፖለቲካ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ


በኢትዮጵያ ታሪክ ራሱን ይደጋግመዋል


ባለፈው ሳምንት  የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ዘገባ  ከሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በግዳጅ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉትን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከት ነበር፡
፡ በዘገባው መሰረት፤ ከዚሁ ከደቡባዊ ክልል በጉራ ፈርዳ  በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ በርካታ የአማራ ተወላጆች በአካባባዊ ባለስልጣናት ንብረታቸውን ይዘው በአስቸኳይ ከአካባቢው ለቀው ወደ ‹‹ሞት ወረዳ›› የቀድሞ ቀያቸው  እንዲሄዱ ለዳግም ስደት ተዳርገዋል፡፡ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጡት የአቤቱታና የሰሚ ያለህ እሪታቸው በአካባባዊ ባለስልጣናት ተጠርተው የእርሻ ቦታቸውን በመልቀቅ፤ ቤተሰባቸውንና ጓዛቸውን ይዘው አካባቢውን ከጸሃይ ጥልቀት በፊት ለቀው እንዲወጡ መመርያ ተሰጥተዋል፡፡  አብዛኛዎቹ እነዚህ ተፈናቃዮች፤ በዚያው ተወልደው ያደጉና ቀሪዎቹ ደግሞ ለዓመታት ኑሯቸውን የመሰረቱ ናቸው፡፡ ስርአት ያጣው የመፈናቀል ዕጣ የደረሰባቸው ቤተሰቦች፤ መኖርያቸውን አላግባብ ይዘነው የነበረ በመሆኑ አሁን በፈቃደኝነት ለአካባቢው መስተዳደር በፈቃደኝነት  መልሰናል የሚል የመስተዳድሩን ሰነድ በግድ እንዲፈርሙ  መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ እነዚህ የመከራና የግፍ በደል ተሸካሚ ተፈናቃዮች ና ቤተሰቦቻቸው አካባቢውን በመልቀቅ አቤቱታቸውን ለመለስ ዜናዊ ለማሰማትና የአካባቢው መስተዳድሮች የጣሉባቸውን የመፈናቀል በደል እንዲያስነሳላቸው ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል፡፡ ለአቤቱታ አገር ቆርጠው በዜግነት መብታቸው ለመጠቀምና አቤቱታ ለማሰማት ከፓርላማው በር ላይ የተሰበሰቡት አቤት ባዮች፤ አቤቱታቸው በመደመጥ ፈንታ በደህንነት ተከበው ተበድለው እንደበዳይ በመኪና ተጫነው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡ የመለስ ዜናውም ተወካይ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጠችው መግለጫ ስለተባለው ጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ጉዳዩን ለማጣራት ግን ሂደት መቀጠሉን ተናግራለች፡፡ በዚህ በኩል ደህነንት ማዘዝ በአሜሪካን ድምጽ በኩል ደሞ ጉዳይ ማጣራት ምን የሚሉት ቅልመዳ ነው? በቅርቡ በአሰርት ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በአካባቢው ባለስልጣናት ትእዛዝ በጉልበት ከደቡብ ሕዝቦች ማስተዳደር ባንቺ ማጂ ዞን መፈናቀላቸው ይታወቃል፡፡

የሕዝቦች ግዳጃዊ መፈናቀል (<<ሰፈራ>> መንደር ምስረታ›› ‹‹የአካባቢ ለውጥ›› ወ ዘ ተ ር ፈ ………) በኢትዮጵያ አስከፊና ዘግናኝ ታሪክ ያለው ነው፡፡  የመለስ አገዛዝ በመንደር ምስረታ ስም በርካታ ፕሮግራሞችን በማካሄድ፤(ቋሚ የሆነ ከትውልድ ቦታ ንቅለትና ስደት) በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል በጋምቤላ ነዋሪዎችን አፈናቅሎ የሕንድ ስሪት ለሆነው ለካሪቱሪና ለሌሎችም ኢንቬስተሮች በዜጎች ስደት ላይ ያበበ ንግድ ማካሄዱን የመለስ ገዢ መንግሥት ይክዳል፤ የመለስም ከፍተኛ የእርሻ ባለስልጣን ‹‹የስደት እንቅስቃሴ በጋምቤላ ጨርሶ የለም›› ቢልም የዩኒሴፍ የአካባቢ ጥናት ግን የሚከተለውን ይላል

ነዋሪ ዜጎችን ማፈናቀሉ (ከቅድመ ስሪታቸው ማፈናቀል) በጋምቤላ መጠኑን የሳተና ምክንያተዊነቱም የማያሳምን ነው፡፡ በቅርቡም የአኝዋኮች (ሌሎችም በቁጥር አናሳ ዘሮች)ባህል ጨርሶ እንደሚጠፋ አያጠራጥርም፡፡ ባህላዊ  ደህንነት፤ራስን መቻልና ራስን ማስተዳደር፤ ለነዚህ ዜጎች መብታቸውና ሊከበርላቸውም የሚገባ የነሱነታቸው መገለጫ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ህጋግትም ጥበቃ ሊደረግላቸው ቢደነገግም በጋምቤላ ግን ትርጉሙ ጠፍቶ የግፍ መንደር እየሆነ ዜጎችም የግፍ ተጠቂ በመሆን ላይ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን የገዛው የደርግ መንግሥት ኢትዮጵያን ከ1970 እስከ 1991 ድረስ ሲገዛ ሠፈራን ለፖለቲካው መጠቀሚያ በማድረግ ሰርቶበታል፡፡ደርግ ህወሃት በያዛቸው መንደሮች የተገደዱ ሠፋሪዎችን በማሰማራት ለወያኔ ድጋፍ ለማሳጣትና ለሚሰነዘርበት ጥቃት መከላከያ አድረጓቸው ነበር፡፡በ1984 ዓም በተከሰተው ችጋር ሳቢያ ደርግ የ1.5 ሚሊዮን የተገዳጅ ሰፋሪዎችን በወያኔ ከተያዙና ለችጋር ከተጋለጡ ሰሜናዊ  አካባቢዎች ወደ ደቡብና ደቡባዊ ምእራብ አካባቢዎች አሰፈረ፡፡ በዚህም ጊዜ ደርግ ሰፋሪዎቹ ያለምንም ማስገደድ በፈቃደኝነት ሰፈራውን ተቀላቅለዋል ብሎ ነበር፡፡ በዚሁ የሰፈራ ፕሮግራም በህመምና በችጋር በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖች በሞት ተቀጥፈዋል፡፡ከዚህ መከራ ከከበበው ያልተሟላ ሰፈራ መንድርም ለመሸሽ ጉዞ የጀመሩት ኢትዮጵያዊያን ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው ለሞት ተዳርገዋል፡፡

የሚያስገርመው ግን የሰሜኖቹ  የትላንት ተዋጊዎችና ላለፈው 21 ዓመታት ኢትዮጵያን ለመግዛት የበቁት መለሳዊ ገዢዎች ደርግንና የሰፈራ ፕሮግራሙን ‹‹የማፈኛ አስር ጣቢያ›› (“concentration” camps) በማለት ያወግዝና ያንቋሽሽ ነበር፡፡ እነዚህ ሰፋሪዎች ወደ ትውልድ መንደራቸው ጨርሶ እንደማይመለሱና (እትብታቸው ከተቀብረበት)ከመንደራቸው መለያየታቸውን ያናፍስና ያወግዝ ነበር፡፡  በ2012 ደግሞ እነዚሁ የግዴታ መፈናቀልና ሰፈራ ተቃዋሚ የነበሩት የአሁኖቹ ገዢዎች ዜጎችን ከመኖርያ ቀዬአቸው አስገድዶ ለማፈናቀልና ካለፈው በባሰና ነከፋ መልኩ መድረሻ ለማሳጣት የሚካሄደውን እቅድ ቀዳሚ መሃነዲሶች ሆነው በመንደፍና አዲስና እኩይ ዘዴ በመጠቀም ዜጎችን ያለአግባብ በማፈናቀል ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡ ታሪክ በኢትዮጵያ እራሱን ደግሞ ደግግሞ ያሳያል ማለት ይቻላል፡፡ በአርቲክል 7 (d) የሮም ስታቸር መሰረት የሕዝቦች የዓለም አቀፍ ሕግ ከሚፈቅደው ውጪ በግዴታ ማፈናቀል እንደ ኢሰብአዊ ድርጊት የተመዘገበ ወንጀል ነው፡፡

ክልልና ባንቱስታንነት

ላለፉት በርካታ የግዛት ዓመታት መለስ ዜናዊ ጠብ የማይለውን ‹‹የዘር ፌዴራሊዝምን›› በአንጸባራቂ  መጠቅለያ አሳምሮ ለማቅረብ እየጣረ ነው፡፡ የዘር መከፋፈያ አጠራር በመስጠት ኢትዮጵያዊያንን ለያይቶ በፈጠረው የፖለቲካ አጠራር  እንደ ከብት በመደልደል፤ ክልል በማለት መድቧል፡፡ (የዚህም ትክክለኛ ትርጉሙ የተከለለ ማለት ሲሆን ቃሉም ታጥሮ የተከለለ ማለትም ነው፡፡ ክልል በአፓርታይድ ዘመን የነበረውን የዘር ልዩነት ባንቱስታኒዝም ለመፈረጅ የተጠቀሙበት ቃልን ይመሳሰላል፡፡የክልላዊነት ፍልስፍና ከደቡብ አፍሪካው ባንቱስታኒዝም ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሁለቱም ፍልስፍናዎች የተወሰኑ ብሄሮችን ለማግለልና በተከለላቸው አካባቢ ብቻ ተገድበው እንዲኖሩ  በማድረግ በጊዜ ሂደትም የራሳቸውን ግዛት ለመፍጠር እንዲችሉ ለጥፋት የሚያነሳሳ ሂደት ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ሆን ብሎና በቅድሚያ ሊፈጸምና ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚያስችለውን እኩይ ተግባር በማለም አንቀጽ 39ኝን የመገንጠል መብት የሚፈቅደውን አስቀምጧል፡፡ማለትም ክልሎች ቀስ በቀስ የራሳቸው መንግስትን ለመፍጠር ይበቃሉ፡፡ የባንቱስታንም አመሰራረትና ሂደቱመም ይህንኑ ለመተግበር ነበር፡፡

ከዚህ ባለፈም የሚመሳሉበት በርካታ ሁኔታ አለ፡፡ የባንቱስታን ቀዳሚ ፖሊሲም ጥቁር አፍሪካውያንን የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ከማድረግ ይልቅ የአንድ መንደርና አካባቢ ነዋሪዎች ለማድረግና ደቡብ አፍሪካን የነጮች ግዛት አድርጎ ለማስቀጠል የታቀደ ሴራ ነበር፡፡ በዚህም የፖለቲካ መብታቸውን በማፈንና በመንሳት፤ብሔራዊ መብታቸውን በመንጠቅና በማሳጣት፤ በነጻ በሃገሪቱ መንቀሳቀስን፤ ሰብአዊ መብታቸውን በአጠቃላይ የዜግነታቸውን መብት በመግታት፤ ባንቱስታኒዝም ጥቁር አፍሪካውያንን ነጻነት ነስቶ አገቷቸው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት በመካሄድ ላይ ያለው የአስገድዶ ማፈናቀል ተግባር ባንቱስታኒዝም በደቡብ አፍሪካ የፈጸመውን ኢሰብአዊ ተግባር የሚያከናውን ክልል የሚባል ትርጉም የተሰጠው ነው፡፡ ክልላዊነትም ኢትዮጵያን በዘጠኝ ክልላዊ መንግሥት በሚል ቦታ በዘር ድልድል ቆራርጦ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ጥቁር አፍሪካዊያንን አግልሎ ሥላጣኑን እስከዘለቄታው ለማቆየት እንደተጠቀመበት ሁሉ በኢትዮጵያም ለመሰል ግባር ውሏል፡፡ International Crises Group, (a research organization that gives advice to the United Nations, European Union and World Bank):

የህወሃትና የኢህአዴግ አንድ ወቅት ከትግራይ የገጠር ነዋሪ ጋር የነበራቸውን ቅርብ ትስስርና  ግንኙነት እርግፍ አድርገው በመተው አሁን ከሕዝቡ ተለይተው በመግዛት ላይ ናቸው፡፡ይህም አናሳ የሁኑት የፖለቲካ ባለስልጣናት የህወሃት ሥራ አስፈጻሚ አባላትና በተለይም ጠቅላይ ሚኒስተሩ ናቸው የሃገሪቱን የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚወስኑት›› በማለት ያረጋግጣል፡፡

የጎሳ ፖለቲካ ካርታ ጨዋታ ያብቃለት

በኦክቶበር 2011 በሳምንታዊ  መጣጥፌ ላይ  የጨቃኞችና አምባገነኖችና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የመሳርያ ግምጃ ቤት ውስጠ የሚገኘውን የመጨረሻ መሳርያቸውን ከፋፍሎ በግፍ መግዛትን አስመልክቼ ጽፌ ነበር፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት፤በኢትዮጵያ የሥልጣን ወንበር ላይ የተኮፈሱት ገዢዎች እምነታቸው ወይም ዓላማቸው  ‹‹እኛ የሕዝቡ መሪዎች በጣም ጋጠ ወጥ የሆነውን አገዛዝ ለመመስረት…………..›› በግምጃ ቤታቸው ያስቀመጡትን የግፍና የጭካኔ አገዛዛቸውን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ሕዝቡን በዘርና በብሄር፤ በከተማው፤ በመንደር፤ዝቅ ብሎም በጉርብትና መከፋፈል ችለዋል፡፡ የብሔር ፌዴራሊዝም በሚል የተንኮል ድልድል በአካባቢ ሊገድቧቸው በቅተዋል፡፡ሕብረተሰቡን በቋንቋና በሃይማኖት፤ የኖረ ቁርኝታቸውን ለመበጠስና  በሃገር ውስጥና በውጪ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለማለያየት ጥረት አድርገዋል፡፡

ባለፈው ጃንዋሪ መጣጥፌ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ  አንድ እንዲሆኑና ለአንድ ዓላማ በመሰለፍ፤ በገዢዎች የተፈበረከውን ድውይ የሆነ አስተሳሰብ ያዘለውን የዘር የጎሳና የመንደር፤ የሃይሞነትና የብሄር መከፋፈልን አፍርሰን በአንድነት በኢትዮጵያዊነት በመቆም የአንድነት ድልድይ መልሰን በመገንባት ከድህነት ከችጋር ከእርዛት ከመሃይምነት እንድንላቀቅ ጠይቄ ነበር፡፡ ዘወትር የአሜሪካን  ሕገመንግሥት መግቢያው ላይ የሰፈረውን ‹‹እኛ የአሜሪካን ሕዝቦች፤ትክክለኛውንና የማይነቃነቃውን አንድነታችንን ለመፍጠር…….››የሚለውን ሳነብ በዚህ ግዙፍ አባባል ልቤ ይሞላል፡፡

የዘር ፖለቲካን ድል በመንሳት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር

ከዲክተቴርሽፕ ወደ ዴሞክራሲ በሚደረግ ሽግግር ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያጋጠም የሚችለው ችግር፤በላዕላይ መዋቅሩ የተጋረደው የዘር ፖለቲካና የክልላዊነት ድልድል ነው፡፡አንዳንድ ሰዎች የክልሊዝም ፍልስፍና በሃገሪቱ ውስጥ ብጥብጥን ወቅታዊም ቢሆን፤ያለመረጋጋትን ሁኔታ በሽግግሩ ወቅት ብቻ ሳይሆን፤አንድነትን በማጠናከሩና ወደ ቀድሞው ህዝባዊ አንድነትና መግባባት መመለሱንና የኢትዮጵያን የፖለቲካ ነጻነት ሊሞግት እንደሚችል ይገምታሉ፡፡ በኔ ግምት የዚህ ግብግብ የማንነትን ፖለቲካና የዘር ጣያቄ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፤ሰብአዊ ክብርን በረጋ መግባባት ለማጎልበት (በዚህም ግጭትንና ሕገወጥነትን በማስወገድ) የሚያስችል ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡

ለኔ ዋነኛውና መሰረታዊው ጉዳይ፤የመለስ ዜናዊ ‹‹የዘር ፖለቲካ የካርታ ጨዋታን›› መጫወቱ  ውጤታማ ነው ወይ የሚለው ነው፡፡ ካገሪቱን ቅጥና አመራር ለማሳጣትና የራሱን አንድ ሰው አንድ ፓርቲ አገዛዝ ለመምራት ትክክለኛ ነው ብሎ በማመንና ለሱ እስከተስማማው ድረስ ሃገሪቱንና ሕዝቡን ከምንም ሳይቆጥር በማንአለብኝነት ፈላጭ ቆራጭ ስርአቱ ተጠቅሞበታ ል፡፡  ይህን‹‹የዘር ቁማር መጫወቻ ካርታውን›› ተቀናቃኞቹን ለማንበርከክና ለብስጭት ለመዳረግ፤በሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እየናረ ያለውን የኑሮ ውድነት ከሕዝቡ ሃሳብ ለማራቅና ለማረሳሳት፤ (ተቀማጭነቱ በአዲስ አበባ የሆነው አክሴስ ካፒታል የሼር ኩባንያ ባለፈው ዓመት ጥንቅሩ  ኢትዮጵያ በዓለም የዋጋ መዋዠቅ 40.6 በመድረስ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች ብሏል)  የዘር ክፍፍሉን ጨዋታ ለመለስ ተዉን በመምረጥ እኛ በዜጎች መሃል የዕርቀ ሰላምና የመግባባት የብልጽግና ውህደት በመፍጠሩ ላይ እናትኩር ፡፡

የማንነት መገለጫ ይገነባል፤ዳግምም ተሸሽሎ ይገነባል፤እንደገናም ለተሸለ ይገነባል፡፡ ይህንንም የሚያሳዩና ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ ሳይንሳዊና ጥናታዊ ጽሁፎች አሉ፡፡ በሌላ መልኩም የብሄር ማንነት እንደማንኛውም ማንነት ተለዋዋጭ ነው፡፡በስደት፤ በጋብቻ፤በትምህርት በመቀላቀል አንድነት በሚመሰረትበት ሁኔታ፤በኤኮኖሚ እድገትና በመሳሰሉት ሊለዋጥ ይችላል ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜ የህብረተሰብና ሕጋዊ ፍትህ በማይኖርበት ወቅት፤ የህግ ልዕልና በእኩልነት በማይኖርበት፤ደካማ አስተዳደር ባለበት፤ዘረኛነት ይጠነክርና ግጭት ሊከሰት ይችላል፡፡ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ለምሁራንእና ለሌሎችም ትልቁ ፈተና የዘር ፖለቲካንና ባለፈውም ሆነ በአሁኑ ሁኔታ የተፈጠረውን አለመግባባትና የገዢዎች የመኖር ዋስትና ያሉትን ጥላቻ በማሰወገድ በሰበአዊ መብቶች ላይ በተመሰረተ መግባባት ላይ ማተኮር ነው፡፡ በኔ እምነትም ማንኛውንም ነገር ለሃገርና ለሕዝብ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚቻለው በቅድሚያ ልዩነታችንን በመንቀስ ወደእንድነት የምንመጣበትን ውይይት ለማካሄድ የውይይቱን አካሄድና መግቢያና መውጫውን በመስማማት ፈቃደኛነትን በማስቀደም ብቻ ነው፡፡ለዚህም የሚረዳን በቅድሚያ ዘር የሚለውን ለመነጋገርያ በሚጠቅምና በሚያግባባ ትርጉሙ ላይ  መስማማት፡፡

ለማንነት አዲስ ቃል መፍጠር

በኢትዮጵያ ስለተከሰተው የዘረኛነት ሁኔታን በተመለከተ ቀደም ባለው ጊዜ ይህን ሁኔታ ሊያወያይ የሚችል አንድ አዲስ ‹‹ቋንቋ›› እንዲፈጠር ሃሳብና ሊሆን ይገባል በሚልም ሃሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ ለጊዜው (ቃሉንም ኒዎሎጊዝምስ ብዬው ነበር) ዋናው እምነቴም ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝና ጭቆና የበለጠ እየደረጁና እየተንሰራፉ የሚሄዱት ሕዝቡ አንድነት ሲያጣና ሲራራቅ፤ በዘርና በጎሳ ተለያይቶ ጎሪጥ ሲተያይ መሆኑን አመላክቼ ነበር፡፡አንድነት የጠንካሬ፤የአብሮነት፤የሰላም እና የእርቀ ሰላም መሰረት ነው፡፡የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ጭራቃዊ ገዢዎች በዘር መከፋፈልን ከፍፍለው ለመግዛት መጠቀሚያ መሳርያቸው አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡

እኔ ዘረኝነትን እንደ አንድ ሳንቲም የአንድነት ሌላው ገጽታ ነው የማየው፡፡የጎሳዎች ስብስብ የብሔራዊ አንድነት ውበትና ቅርጽ ነው፡፡አንድነት የመበታተን አደጋ የማያጋጥመው በብሔረሰቦች መሃል አለመጣጣምና መግባባት ሲጠፋ ነው፡፡ መለስያዊው የዘር አመለካከት ግን ኢትዮጵያን እንደ 9 የተለያዩ ብሔረሰቦች መመልከትና ክልሎች ብሎ ማስቀመጥ ነው፡፡ ክልል የሚለው ቃል በራሱ መታገትን፤ መገደብን፤ መራራቅን አመላካች ነው፡፡መለስም እንደሚያምነውና እንደሚመኘው ኢትዮጵያ የአንድ ሕዝብ ሃገር ሳትሆን በብሔር ብሔረሰቦች ተገጣጥማ ሲያስፈልግ የምትበታተን፤ ሕዝቦቿም አንድ የሚያደርጋቸው ምንም ፋይዳ የሚሞላ ጉዳይ እንደሌላቸው ነው፡፡(ይህ ደሞ ከፋፍሎ ለመግዛት ዋነኛው ሽፋንና መሳርያም ነው) በኛ እምነት ግን ኢትዮጵያውያን ሁሉም በአንድ ጥላ ስር የሚኖሩ፤ በአንድነታቸው የሚያምኑ፤ የሁሉም የሕግ ጥበቃ ከአድልዎ የጸዳና ሚዛናዊ የሆነ፤ኢትዮጵያም በዳበሩና ብዛት ባላቸው ባህሎች ተሳስሮና ተፋቅሮ የኖረ የሚኖርና በመኖርም ላይ ያለ ሕዝብ ሃገር ናት፡፡ ሕዝቡ በሃገሪቱ ዙርያ ገብ ያለ አንዳች ተጽእኖ፤ገደብ በፍቅር በመግባባት በመተሳሰሰብና በመስራት የሚኖሩ ናቸው፡፡

በሁላችንም ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ አዲስ አይነት አንድነት በመፍጠር ነው ከተጫነብን አረመኔያዊ የፈላጭ ቆራጭ የባርነት አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርአት መሸጋገር ያለብን፡፡ይህም የተለየ አንድነት፤የሚቆምበት ዋናው መደብ የሁላችንም  የጋያ ፕሮፓጋንዳ ከሆነው ዘረኝነት የበለጠ ዋጋ ያለው ሲሆን ነው፡፡ ሁላችንም ለሰብአዊ ክብር ያለብን ቃልኪዳናዊ ግዴታ ቅጥ ካጣውና መላቢስ ከሆነው  የአንድ ዘር ግነትና ጋጠ ወጥነት የበለጠ ዋጋ እንዳለው አምነን መቀበል ነው፡፡ በከፍተኛ መመርያና፤ እምነት ላይ የተመሰረተ ነውና፡፡ አፍሪካዊ በሆነው አባባልና አጠራር ላይ ኔልሰን ማንዴላ እንደሚሉትና የሰውን ልጅ አፈጣጠር በሚያስረዳው መልኩ የአፍሪካን የተለያዩ ዘሮች ዩቡንቱ “Ubuntu” ብለን መጥራት እንችላለን፡፡ ሰው ሰው መሆን የሚችለው ሌሎች ሰብአዊ ፍጡሮች ሲኖሩ ነው፡፡ የሌሎችን ሰዎች ድጋፍና ይሁንታ እስካለገኘን ድረስ አንዳችም ነገር መከወን አንችልም፡፡ዩብዩኒቲ፤ እያንዳንዳችን እንደወንድማማች፤እህትማማች፤አንዳችን ስለአንዳችን ማሰብን መተሳሰብን፤መተማመንን፤ መቻቻልን፤የሞራል ግዴታን  የምናከብርበት ነው፡፡ አንዳችን ሌላውን እየለየ በጎጂ ጎኑ በሚያሳየን የተቀባና በሰዎች ተንኮል የተፈበረከ መነጽር ኦሮሞውን ለብቻ ትግሬውን ለብቻ አማራውን ለብቻ፤ ደቡቡን ለብቻ ጉራጌውን ለብቻ፤ በዘር ሸንሽኖ እንደቅርጫ ስጋ የሚያሳየንን መለሳዊ አመለካከት በመምረጥ ጨርሶ ሊሆን አይችልም፡፡ይልቁንስ ሁሉም በአንድ የሚኖርባትን ሃገርና በፍቅርና በመግባባት ተከባብሮ የሞነር ህዝብ፤ፍትህና እኩልነት የጋራቸው የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ መልሰን መገንባት ነው፡፡

ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የምጠይቀው፤ ለዚህ ልዩ አንድነታችን መቆም እንድንችል ነው፡፡ይህንንም አንድነት እኔ ሁሙኒቲ “humunity”እና ዩዩኒተ  “younity” እለዋለሁ፡፡ሁሙኒቲ በዘር ላይ ተመሰረተ አንድነት ዜግነት ሳይሆን በዓለም አቀፍ ህግጋት ሰብአዊ ክብር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ግዴታ ያለበትናነው፡፡ሰብአዊ መብትን፤ ፍትሀን በእኩልነት የሚያስቀምጥ ለሕግ የበላይነት መገዛትን የሚወስን ነው፡፡የማንኛውም የስልጣን መሰረት ሕዝባዊ ይሁንታና በዚህም የተዋቀረው ሕገመንግስት በመመርያነት የሚተገበርበት፤ ተጠያቂነትን፤ ግልጽነትን፤በግዳጅ የሚያስቀምጥም ነው፡፡ እነዚህን ወደ ተግባር መለወጥ ከቻልን የተበዳዮችን መብት በማስጠበቅ፤የሰብአዊ መብት የተነፈጉትን ብናከብርላቸው፤ ምንጊዜም እንዳይጠሱና እንዳየበጣጠሱ፤ገደብ ብናደርግላቸው፤ሕብረተሰቡን ስለነዚህ ቀዳሚ ተግባራት በሚገባ እንዲያውቃቸውና እንዲንከባከባቸው እንዲጠብቃቸው በማስተማር በእውቀት ብናበለጽገው ፤ ወጣቱን ተተኪ ትውልድም ዴሞክራሲያዊ ለሆነ ሁኔታ ብናዘጋጀው፤ሙስናን፤ በስልጣን አለአግባብ በማን አለብኝነት መባለግን፤ በመታገል በዜጎች መሃል የጠበቀና የማይበጠስ አንድነት በመፍጠር አንድነትን በተግባርና በሃቅ ላይ አስቀምጠን የጋራ ንብረታችን ማድረግ እንችላለን፡፡ እነዚህ ውድ የሆኑ ዋጋዎቻቸው የማይተመን ጉዳዮች ከጎደሉብን ግን መለያየትና አለመግባባት ቤታቸውን ይሰሩብናል፡፡

አረመኔ ገዢዎች  ጥቃቅን ልዩነቶቹን በማጉላትና በማባዛት ሕዝቡን ይከፋፍሉታል፤ ሕዝቡም  በሚገባ ሳያውቀውና ሳያገናዝበው በሚመቱት የመለያየት ከበሮ ድምጽ በመመራት ለዜማቸው ይጨፍራል፡፡ በኔ የሁሙኒቲ “huminity” እምነት  ግን የአመለካከት ልዩነት፤እምነት ሊኖር ይችላል፤የአመለካከት ልዩነት ደግሞ የእምነት ልዩነት ሊሆን አይችልም፡፡ዓለምአቀፋዊውን የሰብአዊ መብት ብንመለከት ስለኛ ዘር፤ ዜግነት፤ቋንቋ ሃይማኖት ወይም ሌላ ጉዳይ ሳይሆን፤ የጭቆናንና የክፉአረመኔያዊ ገዢዎችን  አስኳል በመንቀል የዴሞክራሲ ስርአትን በመገንባት ለሕግ የበላይነት ተገዢነትን ማዳበር ነው፡፡

የ ዮዩኒቲ “younity” ግንዛቤዬ እኔና እርስዎ ነአንድነትና በቆራጥነት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችንና ጭቆናቸውን በህብረት ለመታገል መነሳታችን ነው፡ የእምነታችን መመስረቻም፤እያንዳንዳችን ለጭቆና ማበቃትና ለነጻነት በረጂሙ የተሳሰርን የነዚህ ሁኔታዎች መገናኛ ቁልፎች መሆናችን ነው፡፡  ለነጻነት ያለን ፍላጎትም ከአንደንነት ሰንሰነለት ጋር ያቆራኘንና ጭቆናን ለማጥፋት መንገድ ይሆነናል፡፡ ኢትዮጵያዊያን  የሆንን ሁሉ የሰብአዊ መብትን መከበር፤ በሚገባ አውቀንና አሳውቀን ልንጠብቀው ይገባናል፡፡የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ህብረተሰቡ አመለካከቱ አንድ እንዲሆንና አዲስ የሁሚኒቴ “huminity”  አስተሳሰቡን እንዲያዳብር የማድረግ ሃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡የሲቪክ ማህበረሰቦች ለዚሁ ሁሙኒቲ ጥብቅና መቆም፤ምሁራን የዚህን መንገድና ቋንቋ በማስተማር የተለያየ አመለካከት ያላቸውን ማቀራረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣቱ ትውልድም ለቀደምት ትውልድ የሁሙቲን አስፈላጊነት በማስተማር ለአዲስና ለብሩህ ተስፋ ኢትዮጵያ መመስረት ማዘጋጀት አለበት፡፡ ለዘለቄታው አንድነት ማረጋገጫ ደግሞ ማንኛውም ተራው ዜጋ የሁላችንም በሚሆነው ሰብአዊነት ዩብዩኒቲ (ubunity)  ቋንቋ መነጋር አለበት፡፡

አፍሪካውያን ቅኝ ገዢውን ስርአት እና አፓርታይድን በጨቋኝ ስርአት ላይ ግንባር ሲፈጥሩ አሸነፉትና ጣሉት፡፡በቅርቡም የግብጽ፤ የቱኒዚያ፤ የሊቢያ፤ ዜጎች ‹በሕብረት ጸንቶ የቆመን ሕዝብ የሚያሸንፈው ሃይል የለም›› የሚለውን በተግባርና በቆራጥነታቸው አረጋግጠዋል፡፡ ሕብረትና አንድነት የማጣት ዋጋው ደግሞ ለመከራ መጋለጥ፤ለብዝበዛ መዳረግ፤ለመለያየት መንገድ መክፈት፤ መሳርያ መሆን ነው፡፡ ምርጫችን ሁልጊዜ ማልቀስ፤ ዘወትር ማውራት፤ በየቦታው ለችግር መጋለጥ፤ በፍርሃት መታሰር ሊሆን ይችላል፡፡ እርስ በርሳችን በመናቆር፤ አንዳችን አንዳችንን በማጥላላት፤ ለጥቅምና ለቁራሽ ስንል ወገንን ማሳለፍ፤ እራሳችንን ለማቆየት ብዙዎችን መክዳት የሚያስከትለው ውጤት ግን መብትን በማጣት ለባርነት መዳረግን ነው፡፡ አለያም ዩብዩኒቲ፤ ሁሙኒቲ፤ እና ዮዩኒቲ የአንድነትን ጎዳና መምረጥ ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእህትማማችነትና በወንድማማችነት መንፈስ መሰባሰብ አለብን፡፡የዘርን የሃይሞነትን፤የቋንቋን እና ሌሎችንም ልዩነታችንን በመቻቻልና በማስወገድ ተቀናጅተን የጥንቱን አንድነታችንን በመከባበርና በመተሳሰብ መመለስ ይኖርብናል

የመለስን የዘር ፖለቲካ ካርታ ለመጫወት ፈቃደኛ መሆን ማለት ለጥፋት ወደሚዳርግ ልዩነት፤የዘር ፖለቲካ፤አለመግባባትና መናቆር፤መዳረግ ነው፡፡በጉራ ፈርዳ፤ በጋምቤላ፤በቤንች ማጂ፤እና በሌሎችም ቦታዎች መለስ ላስከተለውና በሕዝቡ ላይ ስለጫነው የግፍ ቀንበር ደጋግመን ልንረግመውና ልናወግዘው እንችላለን፡፡ ግን ከዚያ ባለፈም ከዘር ፖለቲካ ተገልለን፤ የአንድነታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን መገንባት እንችላለን፡፡ ግን እንዴት………?

ከቁጡነት፤ ከጥላቻ፤ ከክፋት የጸዳ አዲስ ብሔራዊ ግንኙነት መፍጠር

አዲስ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ቀጥተኛውና አመቺው መንገድ፤የቆየውንና ጊዜው ያለፈበትን በጥላቻና በጀብደኝነት ላይ ተመስርቶ የነበረውን አንድነት በመተው ነው፡፡የአፍሪካ አንድነት  ቋሚ ጸ/ቤት በሜይ 1963 በአዲስ አበባ በተመሰረተበት ወቅት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአፍሪካ አንድነት ያስፈለገበትን ዋነኛ ምክንያት አስረድተው ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ከግማሽ ምአት በፊት የተሰነዘረው አስተያየት አሁን መልሶ በኢትዮጵያ ላይ እያጉረመረመ ነው፡፡

ስለአፍሪካ አንድ መሆን ስናስብ ስለነጻነት ብቻ ሳይሆን ስለአንድነትም ነው፡፡ይህ አዲስ ፈተና ሲቀርብልን ከአለፈው ትምህርት በመውሰድ ተስፋና መበረታታት ይሰማናል፡፡በመሃላችን ልዩነት እንዳለ አይታበልም፡፡እኛ አፍሪካውያን የተለያየ በሃልን እናስተናግዳለን፡፡……………. እንደ ነጻ ሰዎች የእኛ ጥረታችን አዲስ ግንኙነት ለመፍጠር መጣር ሊሆን ተገቢ ነው፡፡…….ብለው ነበር፡፡

ጎሰኛነትን ወይም ዘረኝነትን በማግለል፤ በግልጽ የጠበቀ አንድነታችንን በማሳወቅና በማረጋገጥ ባጋጠመን እድልና ቦታ ሁሉ የኢትዮጵያዊነት እምቢልታችንን ከፍ አድርገን በማሰማት በኢትዮጵያችን ሰብአዊነትን ባረጋገጠ መልኩ ኢትዮጵየዊነትን መገንባት ነው፡፡ ከጥርጣሬና ከጥላቻ የጸዳ  አዲስ አንድነትና ግንኙነት እንገንባ……….

(ይቀጥላል)

No comments:

Post a Comment