"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 3 August 2012

የርዮት አለሙ 14 ዓመት ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደረገ!

 



በተከሰሰችበት የ “አሸብረሽናል” ክስ 14 አመት እና ብዙ ሺህ ብር ቅጣት ተበይኖባት የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ፤ የሚያስፈርድብኝ አንዳችም ማስረጃ አልቀረበብኝም እናም  “አቤት ክቡር ፍርድ ቤት” ብላ ይግባኝ ጠይቃ እንደነበር ይታወቃል። የማይታወቅም ከሆነ ይኸው አሁን ተናግሬያለሁ።
የርዕዮት ይግባኝ በቀጠሮ ሲንከባለል ቆይቶ በዛሬው እለት “ውሳኔ” አግኝቷል።
በውሳኔው ርዕዮት፣ ቤተሰቦቿ እና ጠበቀዋ ደስተኛ እንዳልሆኑ ምንጮቼ ነግረውኛል። እንደ ምንጮቼ ከሆነ የርዕዮት ቤተሰቦች እና ጠበቃዋ “የይግባኙ ውሳኔ አቃቤ ህግ ምንም ማስረጃ ባለቀረበበት ሁኔታ የተወሰነ በመሆኑ ፍትሃዊ ውሳኔ ነው ለማለት አያስደፍርም።” ብለዋል በመሆኑም ውሳኔውን ርዕዮት እና ጠበቃዋ በመካከር ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊወስዱት እንደሚችሉ ምንጮቼ ሹክ ብለውኛል።
በዛሬው ዕለት የርዕዮትን ፍርድ ከአስራ አራት አመት ወደ አምስት አመት ዝቅ እንዲል የወሰኑት ዳኛ ርዕዮትን፤ “አንቺም ብትሆኚ በጋዜጠኝነት ስትሰሪ ደህና ደህና ነገር መፃፍ ይገባሽ ነበር!” ሲሉ “መክረዋታል” ይህንን የታዘቡ አንዳንድ አሽሙረኞችም “ደህና ደህና ነገር አለመፃፍ አምስት አመት ያሳስራል ማለት ነው!” ሲሉ ማሸሞራቸውን ሰምቻለሁ!

No comments:

Post a Comment