"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 1 August 2012

ዜና በጨዋታ፤ “አይ ሲ ጂ” የኢሳትን መረጃ “እኔ አላልኩም” አለ

አቤ ቶኪቻው
በትላንትናው እለት ኢሳት ራዲዮ “አይ ሲ ጂ” የተባለውን ተቋም ምንጮች ጠቅሶ መለስ መሞታቸውን አረጋግጫለሁ። ብሎ የዘገበ ዚሆን ዛሬ ደግሞ “አይ ሲ ጂ” በድረ ገፁ ላይ “እኔESAT Radio, Ethiopian Satellite Television አላልኩም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ሞትም ሆነ ህይወት የማውቀው ነገር የለም” ብሏል።
ኢሳት ከ “ኤይ ሲ ጂ” በተጨማሪ ታማኝ የዲፕሎማት ምንጮችም ነግረውኛል “ሰውዬው ከዚህ በኋላ እቃ አይሆኑም አክትሞላቸዋል የርሳቸው ነገር ከእንግዲህ ኦሮማይ ነው!” ብሎ በልዩ የዘገባ ፕሮግራሙ ሲነግረን በአንክሮ ነበር።
ያው ትላንት እኔም ይሄንን ወሬ ሳቀብላችሁ እስቲ የአቅሜን ያኽል ወሬ ፍለጋ ዞር ዞር ብዬ አካፍላችኋለሁ ባልኩት መሰረት ስለቃቅም ካገኘሁት መሀከል፤ በትላንትናው እለት በራዲዮ ፋና ላይ “የህግ ጉዳይ” በሚወራበት ፕሮግራም ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም እና በእንዲህ ያለው ጊዜ ማነው የሚተካቸው? የሚለው ጉዳይ ላይ በቀጥታ ስርጭት ውይይት ሲደረግበት እንደነበር “ሶሊያና” የተባለች ወሳኝ ወዳጃችን በፌስ ቡክ ግድግዳዋ ላይ ለጥፋልን ነበር። በነገራችን ላይ ይቺው ወዳጃችን ከዚህ በፊት ሚሚ ስብሀቱ “የመነኩሴዎች ፀሎት እያለ እሳቸውማ አይሞቱብንም” ብላ በራዲዮ ፕሮግራሟ ላይ መናገሯንም ነግራን ነበር። “ሶሊን” አመስግነን “ሚሚን” ደግሞ ቆይ እንገማገማለን! እንላታለን። የሆነ ሆኖ የሁለቱ ራዲዮ ጣቢያዎች እንደዚህ መብከንከን ስንሰማ “ኢሳትማ የሆነ የደረሰበት ነገር አለ” የሚያስብል ነው።
እና ወዳጄ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዴ ሲሞቱ አንዴ ሲነሱ አንዴ ህክምና ላይ ሲሆኑ ሌላ ጊዜ እረፍት ሲያደርጉ እርሳቸው ጠቅላይ ሆነው ሳለ፤ ነገራቸው ግን አሁንም ድረስ አልተጠቀለለም ማለት ነው።
ድሮ አባቴ ሲያጫውተኝ በምድር ላይ ክፉ ስራ የሰራ ሰው ቶሎ አይሞትም ብሎ ነግሮኛል። “አልጋው ላይ ሆኖ ሞተ ሲባል ሲድን፣ ዳነ ሲባል ሲሞት፤ ሰውም ያንገላታል እርሱም ይሰቃያል”። ይለኝ ነበር። አባቴ በተለይ አራጣ አበዳሪዎች እንዲህ አይነት ስቃይ እንደሚገጥማቸው ነግሮኛል። እንዴት ነው ነገሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አራጣ ያበድሩ ነበር እንዴ…!?


No comments:

Post a Comment