"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 4 August 2012

ወያኔ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባዳ ሆነውብን ይዘልቃሉ



ዋለልኝ መኮንን
የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር ከሞቱ/ከታመሙ ጀምሮ የህወሃትና ወይም ኢህአዴግ( ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጭበርበር የወጣ ስም መሆኑን እንዳትዘነጉ) ምን ያህል ከአንድ ጎጥ የተውጣጣ የበሰበሰና የተበላሸ የፓርቲና የግለሰቦች ስብስብ እንደሆነ ግልዕ አድርጎልናል:: በጣም አስገራሚው ደግሞ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች/ የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም የኢትዮጵያን ህዝብንም እናንተንም ጋዜጠኞቹን ምንም አያገባችሁም አይመለከታችሁም የግል ጉዳይ ነው በለውን እርፍ አሉት::
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች/ የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መሞት፣ የሬሳ ሳጥኑ ምን አይነት ነው ፣ መታመም፣ ምን እንዳመማቸው “ካሁን በሁዋላ የሚያሳትም የሚፅፍ የሚያወራ በአሸባሪነት ሊከሰስ እንደሚችል” የሚል ያዘለ መልዖክት አስተላልፈዋል::የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም የኢትዮጵያን ህዝብንም እናንተንም ጋዜጠኞቹን ምንም አያገባችሁም አይመለከታችሁም የግል ጉዳይ ነው በለውናል እዚህ ጋር በረከት ስምዖን አንድ እውነት አለው ይህም የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ህዝብ የጠቅላይ ሚንስቴሩን ስልጣን አላገኙም::
ሌላው የመለስ ዜናዊ መሞት/መታመም የት እንዳለ የሚያውቁት ወያኔዎች ብቻ ናቸው ሊያውም ጥቂት አድዋዎች:: ከፍተኛ የደህዴን ፣ የኦህዴድ፣ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች አይደለም የመለስን መሞት/መታመም ይቅርና ትላልቅ ሀገራዊ ውሳኔዎችን የሚሰሙት ልክ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመጀመሪያ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ባሉ የህዝብና የግል ሚዲያዎች ሲሆን ከዛም በሁዋላ በወያኔ የሚዲያ ማሰራጫዎች እንደማስተባበያ ሆኖ ሲቀርብ ነው:: በዚሁ ሳልናገር የማላልፈው ከፍተኛ የደህዴን ፣ የኦህዴድ ፣ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች የወያኔውን ጠቅላይ ሚንስቴር መሞት ፣ መታመም እና የወያኔን እርቃኑን መቅረት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ህዝቡ የሚያደርገውን የዲሞክራሲ የፍትህና የኩልነት ትግል እንዲቀላቀሉ እመክራቸዋለው::
ሀወሃት/ኢህአዴግ/ ወያኔ ምንም ድርጅታዊ አሰራር መዋቅር መንፈስ የሌለው የጥቂት በሰፈር የተቡዋደኑ ፣ ለአራት አስርት አመት ያህል አመለካከታቸው መቀየር ያቃታቸው ፣ ጥቂት የሰባዊነት ስሜት በውስጣቸው የሌለ ማፊያ ግለሰቦች ስብስብ እንደሆነ በቀላሉ አስረድተዉናል:: አሁን ልክ እንደጠንቁዋያቸው የሚያዩትና የሚሰግዱለት መሪያቸው መሞት/መታመም በሰፊው ከተነገረ በሁዋላ እንኩዋን የታየባቸው ባህሪ ይሉኝታ የሌላቸው ፣ የሃገር መፍረስ የህዝብ መራብ መቸገር ሳይሆን የወያኔ/የአድዋ አምባገነናዊ ሰልጣን የሚያሳስባቸው የቀን ጅቦች ናቸው:: ወያኔ በህግ መተዳደር የማይፈልግ ፣ የበታችነት መንፈስ ያናወዛቸው ፣ የስግብግብነት ስሜት ደማቸው ውስጥ የሚሮጥባቸው ፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ፣ በጠብመንጃ እንጂ በዕውነቶች ዙሪያ መደራደር የማይችሉ ስለመሆናቸው ያለፈው ስራቸው አስገንዝቦናል::
ዲሞክራሲያዊ ስርአት ስም ኢትዮጵያውያንንና የአለምን ህዝብ ያጭበረበሩበት የወያኔን ስልጣንና ጥቅም ብቻ የሚያስከብረው ፧ በአለም ላይ የምርጦች ምርጥ ብለው የሚፎክሩበት ፧ በወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ማሻሻል የሚሞከረው ህገ መንግስታቸው በሁሉም መልኩ ቀዳዳ የበዛበት ነው:: ጠቅላይ ሚንስቴሩን ዘላለማዊ አድርጎ አስቀምጦዋቸዋል :: እነዚህን ቀዳዳዎች ወያኔ እስካሁን ለማሻሻል ለመድፈን አልፈለገም እንደውም ለማጭበርበርና ለማምታታት በሰፊው ሲጠቀምባቸው ተስተውሎዋል ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቶቼ ተጥሰዋል ህገ መንግስቱ ይከበር ብሎ ሲጠይቅ ወያኔ ደግሞ ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ ብሎ ይከሳል :: ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ህገመንግስቱ ላይ “መያኔ ብቻ ህገ መንግስቱን መጣስ ይችላል” ተብሎ የተፃፈ ይመስል በየቀኑ መጣስ ብቻ አይደለም እየቀደደው ኖሮዋል ::
የኢትዮጵያን ህዝብ የዋህነት ፣ ታጋሽነት ፣ ጨዋነትና ታዛዝነት ልክ እንደ ፈሪነት፣ ሞኝነትና መሃይምነት ቆጥረውት በጠራራ ዐሃይ በሬ ወለደ ውሸት እየዋሹ ምንም እውነተኛ መረጃ እንዳያገኝ እያፈኑ በጠብመንጃና ኢትዮጵያውያንን እንደፈለጉ እስርቤት በሚያጉሩበት በአራዊት ህጋቸው እያስፈራሩ የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለማረጋገጥ አቅማቸው የቻለውን ሁሉ እያደረጉ ነው:: አሁን ጠቅላይ ሚንስትራቸው ሞቶም/ታሞም ሁሉም የወያኔ አባላቶች ፧ ደጋፊዎች ፧ በዘር የተዛመዱዋቸውና በስርዐቱ አላግባብ የከበሩ እያሰቡና እየሰሩ ያሉት እንዴት ወያኔ የበላይ ሆኖ እንደሚቀጥል እንጂ እንዴት አገራዊ መግባባት እንደሚፈጠር ፣ የህግ የበላይነት እንደሚሰፍንና ፣ አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ቀውስ በምን መልኩ መውጣት እንዳለባት አይደለም::
ወያኔዎች ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: እነዚህን ሁሉ በወያኔ እምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍትህአዊ ድርጊቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሱትን የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ትግሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተባበርና መሳተፍ ይጠበቅብናል::ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የሚይዘው የሚጨብጠውን ያጣውን የወያኔን የማፊያ ስርአት እናስወግድ::

No comments:

Post a Comment