"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 14 August 2012

ቻልኩበት የተሰኘው የኩኩ ሰብስቤ አልበም በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ይለቀቃ


ቻልኩበት የተሰኘው የኩኩ ሰብስቤ አልበም በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ይለቀቃ

በለስላሳ ወይንም ትዝታ እየተባለ በሚታወቀው የሙዚቃ ስልት እና በአዘፋፈኖቿ ቅላጼዎቿ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያላት የድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ “ቻልኩበት ” የተሰኘው አልበም በሚቀጥለው ሁለት ሳምንታት ለህዝብ በይፋ ይለቀቃል ።በአዲካ አከፋፋይነት የሚለቀቀው ይኽው የሙዚቃ አልበም በአቢይ አረቃ እንደተቀናበረ የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሰው የቅርብ መረጃ እንደሚያመለክተው ከብዙ ልፋት እና ጥረት በሁዋላ አልበሟን ለመልቀቅ ከፍጻሜ እንደደረሰች ተገልጾአል ። በኢትዮጵያ ውስጥ እና በአውሮጳ እና እንዲሁም በሌሎች አገራት በሚከሰተው የሰው ልጅ ስራ ፈጠራ መብትን ገፈፋ ወይንም የኮፒ ራይት ጥሰትን አስመልክቶ ብዙሃኑ ሙዚቀኞች ስራዎቻቸውን ለህዝብ ከማቅረብ ይልቅ ለማፈን ተገደው የነበረ አስታውሰው ፣ከማፈን ምንም ለውጥ እንደሌለ በመረዳት ስራዎቻቸውን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ገልጸዋል በዚህ ስድስት ወራት ተከታታይ ከሶስት ያላነሱ የሙዚቃ ስራዎች መለቀቃቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁን ሰአት በመላው አለም የሚከናወነውን የሰዎችን የፈጠራ ስራ የሚያስከብር ማህበር በሰሜን አሜሪካ በቺካጎ አካባቢ ፈቃድ ማግኘቱን እና ስራውን በሰፊው በቅርቡ በመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ እንደሆነ ከድርጅቱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይኸው ድርጅት ከአሜሪካ የኮፒራይስ ኦርጋናይዜሽን ጋር ጥምረትን ፈጥሮ በከፍተኛ ደረጃ የሚሰራ ሲሆን ይበልጥ የኢትዮጵያን ኮፒ ራትይ ስራዎችን በሰሜን አሜሪካ ያለማንም ፈቃድ አባዝቶ መሸጥ በስፋት የሚከናወን ሲሆን በተለያዩ የኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ሱቆች ውስጥ እንደሚሸጡ    አጣርቶ መረጃዎቹን የያዘ መሆኑ አክሎ ገልጦአል ። ፈቃዱን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮም ከአሜሪካን ፌደራል ኢንቨስቲጌሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ጥናቶቹን እያደረጉ ክሶችን ማዘጋጀትም እንደጀመሩ ተገልጾአል፣ ።በሌላም በኩል በሰሜን አሜሪካ ለሚከናወነው የፈጠራ ስራዎችን መብት የማስከበር ስራን ለመተባበር እያንዳንዱ ደራሲ ፣ሃያዚ ፣ሙዚቀኛም ፣ሆነ የባለቤትነት መብትን ማስከበር የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ በአፍሪካን አርት ኤንድ ፓተንት ራይት በተሰኘው ድርጅት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ ጥሪውን ለማለዳ ታይምስ ያስተላለፈ ሲሆን ፤ንበረቶቻቸው የተዘረፉባቸውን ሰዎች በሙሉ በድርጅቱ ጠበቆች አማካይነት ወዲያውኑ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል ይገልጻል ።     በቅርቡም በኮሚዲያን ፍልፍሉ ላይ ተፈጽሞብኛል ብሎ በቪድዮ ማስረጃ በዘሃበሻ ጋዜጣ አዘጋጅ ሄኖክ አለማየሁ በኩል የተለቀቀውን የምስል ቅንብር እና የጥያቄና መልስ  በመመልከት ይህንን የመብት ጥሰት ለማስቆም ኮሜዲያኑን ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ሲሆን በሚቀጥለው አምስት ቀናት ውስጥ በቺካጎ ውስጥ ለሚያደርገው የመድረክ ዝግጅት ፕሮግራም ላይ ፍልፍሉን ለማነጋገር መዘጋጀቱን እና እንደ አንድ አባልነት እንዲመዘግበው ጥሪ ሊያቀርብለት እንደሚችልም ገልጾአል። በሌላም በኩል የፍልፍሉን የስራ መብት ጥሰት ያደረገውን ግለሰብ አጣርቶ ያወቀው ሲሆን በአትላንታ ከተማ እንደሚኖር እና ከኢትዮጵያ ጀምሮ እስከ አሜሪካ  በዲጄነት እንደሚሰራ ጭምር አክሎ ገልጾአል ሆኖም ግን ስለ ግለሰቡ ማንነት ከፍልፍሉ ውሳኔ በሁዋላ ወደ ፍርድ ቤት በሚያመራበት ወቅት ሊገልጽ እንደሚችል አክሎአል ።  ይህንን ጉዳይ ከፍልፍሉ ከተቀበኩ ክሱን እስከመጨረሻው ድረስ እገፋዋለሁ ያለው ይኸው ድርጅት የመብት ጥሰትን ለማስቆም አንደኛ አላማችን ስራችንን በተግባር መስራት ነው ብሎአል ። የዚህ ድርጅትን የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ቁጥርንም አያይዞ እንዲገለጽለት አመክሮ ጠቁሞአል.8467233  ኢልኖይ ሲሆን ለምዝገባው በቅርቡ በማለዳ ታይምስ እና እንዲሁም በኮንስትራክሽን ላይ ባለው ዌብሳይት ላይ እንደሚለቅ ተገልጾአል   ።


No comments:

Post a Comment