"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 15 August 2012

ዋልድባ ጉድ እያፈላች ነው፤ አቡነ ጳውሎስም ሆስፒታል ገቡ




Share

(ዘ-ሐበሻ) ዋልድባ ገዳምን የተዳፈሩ ሁሉ እግዚአብሄር እየቀጣቸው እንደሆነ በርከት ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ያምናሉ። የተከበረውን ገዳም የስኳር ማሳ ለማድረግ የወያኔ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፤ እነ አቡነ ጳውሎስም ገዳሙ አይነካም፤ ልማት ነው እያሉ ሲከራከሩ ነበር። ያን ጊዜም የሚከተለው ግጥም በዘ-ሐበሻ ላይ ቀርቦ ነበር።
እያንገራገረ ህዝቡ እያባባ
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ
እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ
ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ
አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ
አባቶ ች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ
በውሳኔ ጸንቶ
ኸረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝቡ ቢበደለም
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድ የለም
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ
ጸሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ
በዋልድባ 4 የፌደራል ፖሊሶች በጅብ የመበላታቸው ዜና ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። ገዳሙን ለመጠበቅ ከሄዱት መካከልም የሚታመሙ ብዙ ናቸው። የአቶ መለስ ዜናዊ ሕመምም እንዲሁ ከዚሁ ዋልድባ ገዳም ጋር ተያያዞ የገዳሙ አባቶች ‹‹እናንተ ምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡›› እየተባሉ ሲዋከቡ ነበር። ዛሬ ደጀሰላም ድረ ገጽ እንደዘገበው ደግሞ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸውን ዘግቧል። ይህን ተከትሎ የዋልድባ አባቶች ጸሎት እየተሰማ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በየቦታው በርክተዋል።

እንደ ደጀሰላም ድረ ገጽ ዘገባ አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደ ነበሩ የተናገሩት የዜናው ምንጮች÷ የፓትርያርኩን አጣዳፊ ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡ ይኹንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን ተነግሯል፤ ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አባ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል ያለው ድረ ገጹ ጨምሮም እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ጤናቸውን ለመከታተል የሚያደርጉት ሳምንታዊ ወጪ ከስድሳ ሺሕ ብር በላይ ማሻቀቡን መዘገቡን አስታውሷል።
ዋልድባን የነኩ ምን እየሆኑ ነው? አስተያየታችሁን እንጠብቃለን። 

No comments:

Post a Comment