"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 21 August 2012

ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሪሞት የሚሰሩ” ጊዜያዊ ጠ/ሚ/ር ሆኑ


ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሪሞት የሚሰሩ” ጊዜያዊ ጠ/ሚ/ር ሆኑ



ሃይለማርያም ደሳለኝ በብርሃኔ ገብረክርስቶስናእና በስዩም መስፍን የሚንቀሳቀሱ ባለሪሞት ኮንትሮሉ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ተሾሙ። በሕወሓት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ ከመግባቱም በላይ የስልጣን ሽኩቻውም እያየለ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። ኢትዮጵያም በታሪኳ በሶስት ቦታ ሪሞት ኮንትሮል ሆኖ የሚያገለግል ሰው አግኝታለች።
ከአንድ ቀን በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን፤ ከውጭ አገር እንዲገባ ተደርጎ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ እንደቆየ የኢትዮጵያ ሚድያ መድረክ EMF አጋለጠ። ኢቲቪ አቶ መለስ የሞቱት ትናንት እንደሆነ አድርጎ መዘገቡ ዳግመኛ ውሸት መሆኑንና መለስ ከሞቱ መቆየታቸውን በርካቶች እየገለጹ ይገኛሉ።
እንደ ኢትዮጵያ ሚድያ መድረክ ዘገባ የመለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ከተሰማ በኋላ፤ ልጆቻቸውን በመለስ አስተዳደር የተነጠቁ ወላጆች፤ ፍትህ አጥተው በእስር እና በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደስታቸውን ሲገልጹ፤ ቀኑ የጨለመባቸው የኢህአዴግ ወገኖች ደግሞ ሆድ ብሷቸው ሲያለቅሱ ውለዋል።

በአሁኑ ወቅት. የመለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ የተደረጉት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆኑ፤ የጠቅላይ ሚንስትርነቱ ቦታ ወደ ሌላ ብሄር መሄዱ በዘረኝነት አጥር ውስጥ የሚገኙትን በተለይም፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራር እና የጦር አዛዦችን ያስኮረፈ ይመስላል። በአሁኑ ወቅት ጄነራል የሳሞራ የኑስን ህመም ተከትሎ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት በመንታ መንገድ ላይ ይገኛል። በአጠቃላይ የአየር ኃይል እና የምድር ጦር ሰራዊቱ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መስመር ውጪ በህወሃት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም አመራር ስር መውደቁ ይታወቃል።
አቶ ሃይለማርያም ለስሙ በዚህ ስልጣን ላይ ይቀመጡ እንጂ የሚያንቀሳቅሷቸው አቶ ስዩም መስፍን እና ብርሃኔ ገብረክርስቶስ እንደሆኑ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመዋል።
የአባ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስር ዓት የፊታችን ሃሙስ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወን ሲሆን፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስር ዓት የት እና መቼ እንደሚከናወን አልታወቀም።
Related Posts:
ጀነራል ሳሞራ የኑስ በጠና ታሞ ለህክምና ከኢትዮጵያ ውጭ ወጣ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባት እና የፖለቲካው አሰላለፍ – ከተመስገን ደሳለኝ
አምባሳደር ስዩም መስፍን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ተክተው እየሰሩ መሆኑ ተጠቆመ
ም/ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ ሱቅ እቃ ገዝተው $10 ሺህ ዶላር ከፈሉ
አቶ መለስ መግለጫ ሳይሰጡ ቀሩ

inShare

Short URL: http://www.zehabesha.com/?p=9791
Posted by zehabesha on Aug 21 2012. Filed under Amharic. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. You can skip to the end and leave a response. Pinging is currently not allowed.
Abiy Ethiopiawi Segawi/wemenfesawi
August 21, 2012 - 2:28 am

እንደገና ጥሪ የቀረበው ሕዝብን በመክዳት የመሸባችሁ ልብ እንድትገዙ ሳይሆን ወደሕዝቡ እንድትመለሱና በአደባባይ ወደመሬት አጎንብሳችሁ ይቅርታ እንድትጠይቁ የቀረበ ጥሪ ሲሆን በባንዳነት ለአጋዚ ወሬ እና መረጃ ስታቀርቡ እንደነበረ ሕዝብ የሚያውቅ ሲሆን ማን የት እና ምን እንደሆነ በዝርዝር መረጃ እንዳለን ከወዲሁ እንገልጻለን::እስከዚያው በቀድሞው ትንብታዊ የስነግጥሜ አሳስባለሁ::
ዝም አይልም ሕዝቡ፤ በቃ ወዮላቸው!
ዐብይ ኢትዮጵያዊ | January 31st, 2011 at 1:10 pm | |
ከ አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወ-መንፈሳዊ
እንደ ክቡር ደራሲው ከበደ ሚካኤል፦
***”ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፤
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት፤
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ፤
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ።”***
ብለው እንደተረጎሙት፤
ይኑር ብዕራቸው ለዘላለም አይሙት።
ሕዝቡ ዝም አይልም ፦በቃ ወዮላቸው!!!
ያጋዚ-ወያኔን
ጠርጎ እስኪፈጃቸው።
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!
እናም፦
እኔም እንደአቅሚቲ ለዘመኑ ብዬው፤
በደም ለታጠቡት ትዕቢተኞች ይሄው።
ኢትዮጵያን ያረዱ የፈጁ ሕፃናትን፤
ሕዝቧን በአደባባይ ገድለው ያስገድሉትን፤
በጊዜ በሥልጣን በገንዘብ ቢ-ገዙ፤
የስጋ-ትል ሆነው ሺህ መግደል ቢያበዙ፤
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሥርፅ ነው መዘዙ፤
በሞት-ሲቃ ትግል በጣዕር እስኪያዙ።
አይጠፋም እሣቱ የተቀጣጠለው፤
ደሙ “ዋይ!!! ዋይ!!!” ይላል፦
ሲቃ ነው ያጀለው።
እቶን ነው እሣቱ ጠርጎ እስኪፈጃቸው፤
ሲዖል ነች ኢትዮጵያ ለመጨረሻቸው።
ከተሸሸጉበት ሳይጎለጉላቸው፤
በደም እንዳጠቧት እሷም ሳታጥባቸው፤
እንደሲዖል ማንጉግ :-
ሕዝቡ ሳይበላቸው፤
ዝም አይልም ቀልቡ
ያውቀዋል ውስጣቸው።
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሥርፅ ነው መዘዙ፤
በሞት-ሲቃ ትግል በጣዕር እስኪያዙ።
ቱኒሲያ ቢነድ
ትግሉ የመን ቢነጉድ
ግብፅ ቢቀጣጠል
ከኤርትርያ ቢዘል
እግዚአብሔርም ሰምቶ ለሕዝቧ ይሰጣል፤
ኢትዮጵያን የነካት የሞት ሞት ይቀጣል።
የኢትዮጵያ አምላክ:-
እንዲያ ሲታገሳቸው፤
ዝም አይልም ሕዝቡ



No comments:

Post a Comment